STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#አማራ

የክልሉ ትምህርት ቢሮ እየተተገበረ ላለው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን መጻሕፍት ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡

አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ ለማድረስ ከ31 ሚሊየን 668 ሺህ 812 በላይ መጻሕፍት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን መጻሕፍቱን በአንድ ጊዜ ለማሳተም ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ ቢያንስ አንድ መፅሐፍ ለሦስት ተማሪዎች እንዲሆን እና በዙር እንዲታተም እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡

ከ5 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት በውጭ ሀገር የታተሙ ቢኖሩም በውጭ ምንዛሬ እጥረት መረከብ እንዳልተቻለም ተነግሯል፡፡

በውጭ ሀገር ከታተሙት 8 ሚሊየን 888 ሺህ 169 መጻሕፍት ውስጥ እስካሁን 1 ሚሊየን 425 ሺህ 502 መጻሕፍት መሰራጨታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የታተሙ 944 ሺህ 882 መጻሕፍት መሠራጨታቸውን ነው የተነገረው።

#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል 7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ አዳዲስ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለተማሪዎች እየተሰራጩ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
በኦሮሚያ ክልል ለተዘጋጀው የቅድመ መደበኛ እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዲስ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት በፍጥነት አሳትሞ ለተማሪዎች ለማሰራጨት በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል።
 
በዚህ መሰረት የመምህራን መምሪያ መጽሐፍትን በቅድሚያ በማሳተም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ መደረጉም ተነግሯል።
 
አሁን ላይም ከ7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሐፍት መታተማቸው የተገለጸ ሲሆን ከታተሙት መጽሐፍት ውስጥም 5 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች መሰራጨታቸውን ተገልጿል።

ምንጭ፦ FBC

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#አማራ_ክልል

በ2016 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች በተለይ (በአማራ ክልል) 2ኛ ዙር ፈተና ከመስከረም 13-15/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT