STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ETA

የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሁሉም የግል የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማት አሁን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ አሳሰበ።

ባለሥልጣኑ አሁን በግል የከፍተኛ ትምህርት ቋማት በመማር ላይ የሚገኙ  ተማሪዎች የተመዘገቡበትን አግባብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኝቱ እውቅና በሰጣቸው የትምህርት መስኮች በትምህርት ላይ የሚገኙ የተማሪዎችን  የስም ዝርዝር የያዘ መረጃ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማጠናቀር በ30 ቀናት ውስጥ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡

የሚላከው የተማሪዎች መረጃ  #በፕሬዝዳንት ወይም #በበላይ_ኃላፊ ተፈርሞ መውጣት እንዳለበት ከዚህ ውጪ ፈራሚ አካል ካለ  ስምና  ኃላፊነት የሚገልጽ ደብዳቤ  በነዚሁ የበላይ ኃላፊዎች እንዲገለጽ  እና  የተማሪዎችን መረጃ  በተናጥል በሚልኩ  ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot