STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም በሚሰጠው የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት ፈተና ይጠናቀቃል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች / የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ከመስጠትም ባሻገር የተለያዩ ተቋማት ፈተናውን #በደህንነት_ካሜራ ጭምር ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ለመመለከት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስርዓትን እንደመከታተሉ ይሄ ፈተና ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በተለይም በፈተና ስርቆት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #ቀድሞ ማሰራጨትን #በመከላከል በኩል እጅግ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ሆኖ አግኝቶታል።

ነገር ግን በዚህኛውም " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅትም ሆነ በባለፈው " የማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት በጥብቅ የተከለከለውን ስልክ / ሌላ የመገናኛ ዘዴ / ይዘው ወደ ክፍል በመግባት ፈተና በሚሰጥበት ሰዓት የፈተናውን ወረቀት ፎቶ በማንሳት በ " ቴሌግራም " ሲያሰራጩ የነበሩ ተፈታኞችን ተመልከተናል።

ይህንን ድርጊት ለመቆጣጠር ይመስላል ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት " ቴሌግራም " እንዲገደብ እየተደረገ የሚገኘው።

በፈተና ተቋማት ውስጥ ስለነበረው ጠንካራ ጎን፣ ክፍተት / ችግር ደግሞ የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ከተፈታኞች ፣ ወላጆች ፣ ፈታኝ መምህራን አስተያየቶችን አሰባስበን እንክላችኃለን።

NB. ከብሔራዊ ፈተናው ጋር በተያያዘ እየተገደበ ያለው " ቴሌግራም " ከዛሬ ፈተና መጠናቀቅ በኃላ ሙሉ አገልግሎቱ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
[TIKVAH]
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#BahirdarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በጊዚያዊነት ከትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች #ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ቀሪ ኮርሶችን ሲወስዱ የነበሩ ተማሪዎች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ #ቀድሞ ወደ ነበሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ መሆኑን በመግለጽ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጥሪ እነኚህን ተማሪዎች የማይመለከት መሆኑን አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot