STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) ️
35.2K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ስሚኝማ ወ/ሮ አሜሪካ😡

የመጣ ይመጣታል የፈለገ ነገር ይሆናል እንጂ በሀገሬ ሉዓላዊነት ብትመጪ ግን አልሰማሽም😡 መስሚያዬ ጥጥ ነው😎
እርግጥ ነው😒 አንዳንዶቻችን መሪዎቻችንን አንወድም ይሆናል🤦‍♂
አንዳንዶቻች ደግሞ ይሄኛውን ወይም ይሃንን ጎሳ አንወደውም ይሆናል🤦‍♂
አንዳንዶቻችን ደግሞ ስራ አጥነት ወይም ትምህርት መርሮን ኑሮ ሰልችቶን ይሆናል🤦‍♂

አፈር ከደቼ ትበያለሽ እንጂ 🇪🇹 ኢትዮጵያን 🇪🇹 ግን መቼም አንጠላም😍 መቼም❗️

የቀረው ይቀራል እንጂ… እንደፈለግሽ ትደነፊያለሽ እንጂ…የሀገራችንን ክብር አሳልፈን አንሰጥሽም❗️አንቺ የሆንሽ የመንደር ጎረምሳ 😳 🤷‍♂❗️

ለወይዘሮ ግብጽም ንገሪያት😏 አንቺ ፈሪ ሴትዮ መጋጠም ከፈለግሽ ፊት ለፊት ነይና ይዋጣልን በያት💪 በማንም የመንደር ጎረምሳ ተማምነሽ የራስሽን ጥቅም ብቻ ለማስከበር መሞከሩን ተዪና ፊት ለፊት ግጠሚን ተብለሻል በያት😒

ሁለታችሁም ካላመናችሁ ጣልያንን ጠይቋት ሁሉንም ፍርጥርጥ አድርጋ ትነግራችኋለች😎

ወ/ሮ ግብጽ ደግሞ ባለፈው እማማ ኢትዮጵያ ከኋላሽ አደብቃ "አጼ ዳዊት" ስትልሽ እንዴት ደንግጠሽ እንደሮጥሽ ዘነጋሺው እንዴ😳🤔🤔 ወይ ከረሳሺው ታሪክን ጠይቂው ይነግርሻል😏

የአጼ ዳዊትን እናት ሀገር ደፍረሽ አባይን በጉዲፈቻ ለመውሰድ ወ/ሮ አሜሪካንን ተመክተሽ አጎል ራስሽን ጣራ ላይ መስቀሉ አያዋጣሽም❗️❗️ አይ ካልሽ ደግሞ አሁንም ብዙ አጼ ዳዊቶች እንዳሉ እወቂ❗️ ያን ጊዜ ልክ እንደዛ ቀን ወርቅ እና አልማዝ በስጦታ አስመጥተሽ ብትለማመጪያት እማማ ኢትዮጵያ አትሰማሽም😎😍 ላሽ በዪ ነው የምትልሽ😎

ነገ ደግሞ የአድዋ በዓል ስለሆነ እማማ ኢትዮጵያ ኑ ቡና ጠጡ ብላችኋለች😎

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@INFONERCBOT
#SHARE #SHARE አድርጉት✌️
FB ላይም አጋሩት😉
Fx| ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለደብረ-ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ውጤታቹህ ከ1.25 እስከ 1.99 ለሆነባቹህ አንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ


ከ1.25 እስከ 1.74 ሴሚስተር ግሬድ ያላቹህ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ማለትም 'F' and/or 'D' የመጡባችሁን ሁለት ኮርሶች በድጋሚ ተፈትናቹህ ውጤት ማሻሻል ትችላላቹሁ ተብላቹሃል

ከ1.75 እስከ 1.99 ሴሚስተር ግሬድ ያላቹህ ተማሪዎችም 'F' የመጣባቹህ ኮርስ ካለ ወይም ሁለት የፈላ ኮርስ ካላቹህ በድጋሚ ፈተና ማስተካከል ትችላላቹሁ ተብላችኋል።

ፈተናው የሚሰጠው የካቲት 28 እና 29 ነው

ዝርዝር መረጃውን እንዲሁም የፈተናውን ቀን ከማስታወቂያው ማግኘት ይቻላል።

ቻናላችንን ተቀላቀሉን👇
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT

Contact us👇
@INFONERCBOT
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ፌዴራለዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የአሜሪካ የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት ሴክሬታሪ በየካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ28 ፌብሩዋሪ 2020) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትን ስብሰባ ተከትሎ የወጣውን የፕሬስ መግለጫ በከፍተኛ ቅሬታ ተመልክተውታል። ስብሰባው የተካሄደው ኢትዮጵያ አስቀድማ ለግብጽ፣ ለሱዳን እና ለአሜሪካ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አሳውቃ እያለ ነው፡፡

የግድቡ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በመርሆዎች መግለጫ ስምምነቱ መሰረት የግድቡን ሙሌት ከግንባታው ትይዩ በፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች መሰረት የምታከናውን ይሆናል።

ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል በሚል የተሰጠውን መግለጫ አትቀበልም።

በዋሽንግተን ዲሲ የግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ ፈርሞበታል የተባለው “ረቂቅ” የሶስቱ ሀገራት የድርድርም ሆነ የሕግ እና ቴክኒክ ቡድኖች ውይይት ውጤት አይደለም።

የቴክኒክ ጉዳዮች ድርድሩም ሆነ የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅቱ ላይ የሚደረገው ድርድር አልተጠናቀቀም፡፡ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ የሚዘጋጀው በሶስቱ ሀገራት ብቻ እንደሆነ አቋሟን ቀድማ አሳውቃለች።

ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በሚያውቁት እና በተስማሙበት እንዲሁም በመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መርህ አንቀጽ ስምንት አድናቆታቸውን በሰጡት ሂደት መሰረት ሁሉንም የግድብ ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮች በዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሰጡትን ምክረ-ሃሳቦች መፈጸሟን ትቀጥላለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብን ለማዘጋጀት ቀሪ መሰረታዊ ልዩነቶችን ለመፍታት ኢትዮጵያ ከግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ እና ከሱዳን ሪፐብሊክ ጋር የጀመረችውን ሂደት ለመቀጠል ቁርጠኛ ናት።

የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ

#SHARE #SHARE #SHARE

ቻናላችንን ተቀላቀሉን👇
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዜሮ ተቆረጡ ህግ😓🤦‍♂

በጣም ብዙ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ( ወንድሞቻችን ብለው ይሻላል) ጸጉር በ "0" ካልተቆረጣችሁ😳 ወደ ጊቢ አትገቡም በመባላቸው እና ድሬ ካለው ሙቀት የተነሳ ደግሞ ጸጉራቸውን በዜሮ መቆረጡ የሚያስኬድ ስላልሆነላቸው ብዙዎቹ እንዳልተቀበሉት እና በር ላይ ካሉ ፌደራሎች ጋር ደግሞ የትገባለህ አትገባም ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት እንደታከታቸው ነግረውናል።
ፌደራሎቹ ይሄ አሪፍ ስራ እንደሆነላቸውም የሚናገሩ አሉ😔


በድሬ ሙቀት ላይ በዜሮ ተከርክሞ መማር አስባችሁታል😢😓😓😓


ሴቶች ሳቁ😒 ጸጉር ተቆረጡ እንደው የለባችሁ🤦‍♂


ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
አድዋ| ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የአድዋ በዓል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኪነጥበብ ስራዎች ታጅቦ ተከብሯል፡፡

©Na

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
ማስታወቂያ

#ሴታዊነት

አለኝታ ነፃ የስልክ መስመር ፤ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ላይ የስነ-ልቦና ምክር፣ መረጃ እንዲሁም የሪፈራል አገልግሎት በየትኛውም ፆታ እና እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ደዋዮች ይሰጣል፡፡ በፆታዊ ጥቃት ዙርያ መረጃ ወይንም የስነልቦና ድጋፍ የምትፈልግ/የሚፈልግ  ሰው በስራ ሰዓታችን (ከበዓል ቀናት ውጪ) ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 10፡30 በ 6388 ደውለው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

☎️ 6388 📞 6387


የአለኝታ ነፃ የስልክ መስመር አገልግሎቱን ከዛሬ ጥር 18,2012 ጀምሮ ስራ ጀምሯል።

#አለኝታ #alegnta #6388
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የቱንም ያህል የሚያሳፍር ብዙ ታሪኮች ቢኖሩንም #አድዋ ግን አባቶቻችን ዘር እና ቀለም ሳይለዩ በአንድነት መንፈስ ስለ ሀገር ነጻነት ስለ #ኢትዮጲያ ደማቸውን ያፈሰሱበት የሁላችንም ኩራት የሆነ የጋራ ሀብታችን ነው፡፡

ሰዎች #አድዋ ባትኖር ይሄኔ አሁን በጣሊያንኛ ነበር የምጽፍላችሁ😒

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
😍😍😍አድዋ😍😍😍
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#SHARE #JOIN #SHARE

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
"ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ!"

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው። ይህ ድል ያደረግንበት እንጂ ነፃ የወጣንበት ቀን አይደለም።
እንኳን አደረሳችሁ!
@nationalexamsresult
Happy victory day
📌ስለ ዓድዋ ጦርነት አንዳንድ እውነታዎች

ቀን: የካቲት 23, 1888
ቦታ: አድዋ፤ ኢትዮጵያ
አሸናፊው ሀይል: ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
አጤ ምኒልክ
እቴጌ ጣይቱ
ተክለ ሀይማኖት
ራስ መኮንን
ራስ ሚካኤል
ራስ መንገሻ
ፊታውራሪ ገበየሁ
ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ
ፊታውራሪ ዳምጠው
ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ
ኒኮላ ሊዮንቴቭ

በጣልያን በኩል የነበሩ የጦር አዛዦች
ኦሬስቴ ባራቴሪ
ቪቶሪዮ ዳቦርሚዳ
ጁሴፔ አሪሞንዲ
ማቲዎ አልቤርቶኒ
ጁሴፔ ኤሊና

በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
80,0000 መሳርያ የታጠቅ
20,000 ጦርና ጎራዴ የታጠቀ
8,600 ፈረሰኛ


በጣልያን በኩል የተሰለፈ የጦር ብዛት
24,804 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቅ ወታደር
56 ረጅም ርቀት ተወርዋሪ መሳርያዎች

በኢትዮጵያ በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
3867 የሞቱ
ከ8000 በላይ የቆሰሉ

በጣልያን በኩል የተሰዉ ጦረኞች ቁጥር
6394 የሞቱ
1428 የቆሰሉ
ከ3000 በላይ የተማረኩ


[መልካም 74 Radio]


ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አድዋ ምንድነው?"

"ተደባደቡና..." 🤛🤜

😳🤣🤣🤣🤣😂😂😍

©ኤሊያስ መስረት

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
Hawassa university

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ከተቀበላቸው ተማሪዎች ውስጥ ከታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ያህል ተማሪዎች መባረር አስደንግጦናል

# academic dismissal and forced withdrawal students

1.Natural science ..733
2.Social science ..590
Total ....1323 ተማሪዎች ተባረዋል፡፡


ይህ ቁጥር የተመዘገበው ግቢው ለፍሬሽ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ከ1.00 በላይ አድርጎ መሆኑን ስንሰማ ደግሞ ይበልጥ እንድንደመም አድርጎናል


ቆይ ግን ማለፊያ ዝቅ ባይል ኖሮ ማን ነበር የሚቀረው ?

በነገራቹህ ላይ ከዚህ አስደንጋጭ የቁጥር አሃዝ ጋር የትምህርት ሚኒስተር ታሪካዊ ስህተት በእጅጉ ይጎላል ፤ የአምናው ሀገር አቀፍ ፈተና በመሰረቁ ምክንያት ብዙ ሺህ ተማሪዎች የማይገባቸውን ውጤት ታቅፈው በአጉል ግብዝነት እንደ ትምሮ ሚኒስተር ሃዋሳም በለስ የሚቀናቸው መስሏቸው ገብተው ...... (ይቅርታ ግን እናንተ አይደላችሁም ጥፋተኞቹ ትምሮ ሚኒስተር ነው ካቅማቹህ በላይ እንድትመኙ ያደረጋቹህ )
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
👋ሰላም ኪራ። M ነኝ ከ DTU.😳እንዴ ኪራ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይቺን ምታክል ተማሪ ስለጫረ ነው ምትደነግጠው! እረ ኡኡ😭 ቆይ የኛን ድምፅ ማን ይስማልን ርብሻ ሲነሳም ሚሰማዉ ካለቅን በሗላ የኛ ጊቢ ታዋቂ ያልሆነበት ምክኒያትም ሁሌም ስለሚደብቅ ነው።

እኛ ውስጥ ምንማር ተማሪዎች ብቻ ነን ጉዳችንን ምናውቀው ብናወራ ለራሱ ሚያምነን የለም 😭 በ ዚህ ሴሚስተር ብቻ 1400 ከ 1.5በታች አምጥተዉ የተጫሩ፣ከ 900 በላይ በ warning ምክኒያት withdraw ሞልተው የሄዱ እና አሁን ጊቢ ውስጥ ያለ ምንም warning ያለፍን ተማሪዎች 600ተማሪዊች በብቻ ነን እና ሰምተህ ከሆነ በቅርቡ ጊቢያችን በትምህርት ጥራት ተሸልሟል።

እና አሁን ከ COC በሗላ field መርጠንነበር እና ብዙ ተማሪዎች 4 እያላቸው እንኳ medicine አልመረጡም። 🙏🙏🙏🙏እስኪ አንተ እንኳ ችግራችንን ሰምተህ ዝም አትበል ድምፃችንን አሰማልን እና የበኩልህን ተወጣልን🙏🙏🙏🙏😭

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
👆ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲም የባሰ ደብረ ታቦር አለ🤦‍♂
እንዴት ያለ ቅዠት ነው⁉️

ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ሕይወት ላይ ማሾፍ ይዟል።

"የሜዲስን መግቢያ ያልመጣላችሁ እንዳለ ኢንጂነሪንግ ተመድባችኋል" ይላል፡፡
ዩኒቨርሲቲው አብዷል❗️አልቀበልም ያለ ደግሞ ጊቢውን ለቆ እንዲወጣ ተነግሯቸዋል😳 ምን ማለት ነው?! ያልፈለጉስ? ሌላ ፊልድ ተወዳድረው የመግባት መብታቸውስ?!!!

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ ዶክተሮች

1. ዶ/ር አቤል ጤናው: 3.93
2. ዶ/ር ናታን ወንድወሰን: 3.92
3. ዶ/ር ዮዲት አብርሃም: 3.91
4. ዶ/ር ትእግስት አበባው: 3.91
.
ከተመረቁት 292 ተማሪዎች ውስጥ 74% ሐኪሞች በማዕረግ የተመረቁ ናችው::

በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!

[ Hakim ]

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#ሰበር_ዜና❗️

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማግኘቱን አንድ የዘረመል ምሕንድስና ኩባንያ አስታወቀ❗️

#SHARE #SHARE #SHARE

ኩባንያው እንዳስታወቀው ክትባቱን አበልጽጎ በመጨረስ በእንስሳት ላይ ለመሞከርና በአሜሪካ ተቆጣጣሪ አካላት ይሁንታን ለማግኘት ዝግጁ ነው፡፡

የኩባንያው መግለጫ የእንግሊዝ ተመራማሪዎች ያገኙትን ውጤት መመርመር መጀመራቸውን ከገለጹ በኋላ የወጣ ነው፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ በርካታ ተመራማሪዎች ክትባትና መድኃኒት ፍለጋ እየጣደፉ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ክትባት ማግኘት መቻል ደግሞ እንደ ትልቅ ስኬት የሚወሰድ ነው፡፡ ምንም እንኳ የቴክሳሱ ኩባንያ ክትባቱን እስከ መቼ ለገበያ እንደሚያቀርብ ባያሳውቅም ከዚህ ቀደም ያሉ ልምዶች እንደሚያሳዩት ከሙከራ አንስቶ በማምረት የማሠራጨቱ ሂደት ከ18 – 24 ወራት ይወስዳል፡፡

ብዙ ጊዜ ክትባቶች የሚሠሩት የበሽታው ምንጭ የሆነውን ንቁ ያልሆነ ተህዋስ በመውሰድ ነው፡፡ በአግባቡ እንዳልተጠና የሚገለጸውን የኮሮና ቫይረስ አምጭ ተህዋስ ለክትባቱ መሥሪያነት ይጠቀሙ አይጠቀሙ ተመራማሪዎቹ አልገለጹም፤ ሜይል ኦንላይን ግን በእንዲህ ዓይነቱ አደገኛ ቫይረስ ንቁ ያልሆነውን ተህዋስ ለክትባት ሊጠቀሙ እንደማይችሉ ግምቱን አስቀምጧል፡፡

የዘረመል መሐንዲሶቹ ‘አዴኖቫይረስ’ ከሚባል ዝርያ ክትባቱን እንደፈጠሩት ነው እየተነገረ ያለው፡፡ አዴኖቫይረስ በመተንፈሻ አካላት ላይ ቁስለት በመፍጠርና ጉንፋን በማስከተል የሚታወቅ የቫይረስ ዝርያ ነው፤ በብዛት ክትባቶች የሚመረቱበትም ነው፡፡

© ሜይል ኦንላይን

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
ሁሉም አልፏል| Woldia university😳


ኢንጂነሪንግ የተመዘገባቹህ ተማሪዎች በሙሉ አልፋችኋል ተብላቹሃል😉👍


ተጨማሪ ለ90 ተማሪዎችም ክፍት ቦታ በመኖሩ ምህንድስና ለመቀላቀል የምትፈልጉ ተማሪዎች መመዝገብ ትችላላቹሁ ተብላችኋል 😎

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
ቤተሰብ| ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጎንደር ከተማ አስተዳደርና ከከተማው ማህበራሰብ ጋር በመሆን የ”ጎንደርቤተሰብ” ፕሮጀክትን ተግባራዊ አድርጎ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጾ ይህንን ታላቅ እና ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ተግባር እንዲቀጥል ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቱን በጽ/ቤት ደረጃ አቋቁሞ ሥራውን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የ2012 ዓ.ም የመጨረሻ ዙር የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ትውውቅ ፕሮግራምም መጋቢት 06/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰአት ጀምሮ በሳይንስ አምባ አዳራሽ ያካሂዳል። በዚህ ፕሮግራም ላይ ለመሳትፍ የምትፈልጉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም የጎንደር እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዕለቱ በቦታው ተገኝታችሁ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል፡፡

[ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቤተሰብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ]

ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT