STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የመጀመሪያ ዲግሪ (4ኛ እና 5ኛ ዓመት) እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪ (1ኛ እና 2ኛ ዓመት) ተማሪዎች የ2016 ትምህርት ዘመን የአንደኛ ሴሚስቴር ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀምረው ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መልዕክት የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ለምትጠባበቁ ተማሪዎች

የ12 ውጤት ይፋ ተደርጓል የሚሉ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች እየሰማቹህ ግራ አትጋቡ‼️

ውጤት ይፋ ከመደረጉ በፊት ትምህርት ሚንስቴር የፈተናውን አጠቃላይ ግምገማ ያካተተ መግለጫ ይሰጣል። በመግለጫው ላይም ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚያውቁበት ቀን እና ሰዓት በግልፅ ይነገራል። ከዚያ ውጭ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይሰጥ ውጤት ይፋ ተደርጎ አያውቅምና ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚናፈሱ ወሬዎች አትዋከቡ።

በትምህርት ሚኒስቴር መረጃ መሰረት ውጤት በዚህ ሳምንት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ትክክለኛ ምንጭ ያለው መረጃ ስንሰማ እንደተለመደው ቀድመን እናሳውቃቹሃለን። መልካም ውጤት❤️

ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ‼️
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሠራተኛ ተከሰሰ።

በተደረገ ክትትል በፍተሻ የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ እርማት አዳራሽ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው የተቋሙ ሠራተኛ ስልጣንን ያለአግባብ መገልግል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

ተከሳሹ ይድነቃቸው ተኮላ ይኼይስ የሚባል ሲሆን÷ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ተረኛ ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት ነው ክስ ያቀረበበት።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ በክሱ ተጠቅሷል።

በተለይም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ በነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ 30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም በተከሳሹ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን ፥ በተረኛ ችሎት ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የዋስትና መብት ጥያቄ አቅርቧል።

በተከሳሹ የዋስትና ጥያቄ ላይ አቃቤ ህግ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ ገልጾም ተከራክሯል።

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን መርምሮ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት በይደር የቀጠረ ሲሆን ፥ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ደግሞ ለጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የጅማ ዩኒቨርስቲ ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች በሙሉ ‼️

🔹Internship ላይ ላሉ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥቅምት 4/2016 ስሆኑ

🔹 2ኛ አመት ከዛ በላይ ጥቅምት 8--9/2016 የመግቢያ ቀን መሆኑን አሳውቋል ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወቂያ

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚሠጠው ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 ጀምሮ እስከ 25/01/2016 ዓ.ም  ምዝገባ እየተካሄደ  ይገኛል።

ለመመዝገብ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴሌ ብር ሱፐርአፕ

https://portal.aau.edu.et

ወይም ለዚህ ፈተና ብቻ በሚያገለግለው

https://gat.aau.edu.et

ይመዝገቡ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
" እስካሁን ውጤት አልተገለፀም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስካሁን አልተገለፀም ሲል አሳውቋል።

ተፈታኞችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የምስራች @#Exitexam Tutorial
🥇 ለአካውንቲንግ
🥇 ለማኔጅመንት
🥇 ለቢዝነስ ማኔጅመንት
🥇ለማርኬቲንግ ማኔጅመንት
🥇ለሲቪል ምህንድስና
🥇ለኮምፒውተር ሳይንስ
#የመውጫ ፈተና መዘጋጃ #ልዩ ትምህርት
➾  በአንጋፋ ፕሮፌሰሮችና የዪኒቨርስቲ
      መምህራን
➾ በት/ት ሚ/ር ለፈተና በተመረጡ ኮርሶች
      ላይ ብቻ: የፈተና ጥያቄዎች ላይ በማተኮር
➾ በቂ የጥናት ሞጁሎች
➾ ሞዴል የመለማመጃ ፈተናዎች ከሙሉ
      መልስና ማብራሪያ  ጋር
➾ የኦንላየን መለማመጃ   ሲስተም
➾ ውጤታማ የፈተና አሰራር ሥልጠና
***
💥 እጅግ በተመጣጣኝ ክፍያ 

🛎 በየማዕከላቱ ያሉ ውስን ቦታዎች ቀድመው
      ይያዙ
🔔 ሙሉ  ስምዎን  : የስልክ ቁጥርዎንና
     ዲፓርትመንትዎን 0908-198-786 
      ላይ ቴክስት በማድረግ ይመዝገቡ ።
➾➾➾➾➾➾
ለበለጠ መረጃ
➧ 0908198786 ማነጋገር ይቻላል።

➧➧     #Joinus @ t.me/aec_ethiopia

አድቫንስድ የት/ት ማማከር ማዕከል
           ከፍላጎትዎ ባሻገር !!!
#Passport

ፓስፓርት ታትሞላችሁ እሁድ በ20/01/2016 ዓ.ም እንድትወስዱ የጽሁፍ መልዕክት የደረሳችሁ እና በተለያየ ምክንያት መገኘት ያልቻላችሁ አርብ በ25/01/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30-5:30 በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ቢሮ በመገኘት ፓስፓርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#UnityUniversity

የማካሻ ትምህርት ውጤትን ከ50% በታች ላመጣችሁ ተማሪዎ#ዩኒቲ ዩንቨርሲቲ በሚሰጣቸው የቴክኒክ እና ሙያ መርሀግብሮች ትምህርት ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው የመግቢያ ውጤት መሰረት፡

1. Accounting and Finance
2. Nursing
3. Marketing and sales Management
4. Purchasing and Supply Management
5. Human Resources Management

ማስታወሻ: ከ50% በታች ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ብቻ የተለጠፈ

#ማስታወሻ ተምራቹህ ከደረጃ | እስከ |\/ ድረስ መማር የምትችሉ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ASTU ‼️ ተራዝሟል🙏

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች ያደረገው ጥሪ በአንድ ሳምንት አራዝሟል።

postponement of registration date for regular undergraduate and postgraduate students

All regular undergraduate(4th and 5th year) and postgraduate (2nd year and above) students, be informed that the previous announcement made for registration (28/01/2016-29/01/2016) has been postponed by one week.

⭐️ Further announcements will be made soon.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ዛሬ መስከረም 24 ዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን ነው!

⚡️በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ለ27ኛ ጊዜ ነው ዓለም አቀፉ የመምህራን ቀን የሚከበረው። ከመዋለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምታስተምሩ መምህራን እንኳን አደረሳችሁ!

ክብር ለትውልድ ቀራጮች👨‍🏫🙏
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እንዳልጠራ አሳወቀ።

ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ለሁሉም መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ" በሚል ተማሪዎች እንደተጠሩ ተደርጎ የሀሰት የጥሪ ማስታወቂያ እየተዘዋወረ መሆኑን ገልጿል።

የተለቀቀው የሐሰትና በውሸት የተቀነባበረ ጥሪ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎቻችን ህጋዊ የጥሪ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች፣ በራዲዮና የቴሌቪዥን ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአማርኛ ቋንቋ በሩሲያ ሞስኮ በትምህርት ቤት ደረጃ የመማር ማስተማር ሂደቱ በይፋ እንደተጀመረ እየተዘገበ ነው::

ቋንቋን ማወቅ ለራስ ነው:: ያወቀ ይጠቀማል እንጂ አይጎዳም:: እኔ በግሌ የሃገሬን ሁለትና ሶስት ቋንቋዎች ብችል ምንኛ በታደልኩኝ:: የኢትዮጵያን ሁለትና ሶስት ቋንቋ የምትናገሩ ኢትዮጵያዊያን እድለኞች ናችሁ:: እኔ በምኖርበት የስደት ሃገር ሳልወድ በግዴ ለእጀራዬ ስል የሰው ሃገር ቋንቋ ለምጄ ስራ እየሰራውበት ነው ጠቀመኝ እንጂ አልጎዳኝም::

አሁንም ቢሆን መጪው ትውልድ ወደፊት የሃገሩን ቋንቋ ሁለትና ሶስት ከዛ በላይም እንደሚናገር ተስፋ አለኝ:: ከጥላቻ እንውጣ ኦሮምኛ የሚችለው አማርኛውን አማርኛ የሚችለው ኦሮምኛውን ትግርኛውን ሌሎቹንም በሚችለው አቅሙ ይማር ይልመድ::

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአርሲ ዮኒቨርሲቲ ለክቡር ሼክ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል

#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot