STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#JigJigaUniversity

የጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ነባር የሶስተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ከህዳር 15 እስከ ህዳር 17/2014 ድረስ ሲሆን የአንደኛ ዓመት የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከህዳር 23 እስከ ህዳር 25/2014 ድረስ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አስታውቋል።

በተጨማሪም በጊዜያዊነት በትምህርት ሚኒስቴር ከመቀሌ ፣ከአክሱም እና ከወልድያ ዩንቨርሲቲዎች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹህ ተማሪዎች ከህዳር 23 እስከ ህዳር 25/2014 ድረስ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

@nationalexamsresult
#JigjigaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.regi@jju.edu.et መጎብኘት ትችላላችሁ፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 18 እና 19/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የበጋ ወሰን ትምህርት ቲቶርያል ከሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 719 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ (799) እና በኤክስቴንሽን (920) መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 449ኙ ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት አብዲ አህመድ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ ዲግሪ እና የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ከአንድ ወር በኋላ እንደሚያስመርቅ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብሮች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመማር ላመለከቱ የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ፈተናው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ በጎዴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በደጋህቡር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንዲሁም በፊቅ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ተፈታኞች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾችን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ፦

https://www.facebook.com/614590095253065/posts/pfbid02vdXcet51zSByjSyGbknWGK1WPZUDPdJexQEopi1VyFUc1eaWGPmuWoZH2Bx8z2qhl/?extid=a&mibextid=e8qoej

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በፈታኝነት፣ ለአይነ-ስውራን ተፈታኞች በአንባቢነት እንዲሁም በመልስ መስጫ ወረቀት ቆጣሪነትና አደራጅነት መስራት የሚፈልጉ የተቋሙ ሰራተኞች እንዲያመለክቱ ጋብዟል።

👉 አመልካቾች የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እና የተቋሙ ቅጥር ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል።

👉 የማመልከቻ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው አዲሱ የአስተዳደር ህንፃ፣ 2ኛ ፎቆ፣ ቢሮ ቁጥር 211

👉 የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እስከ አርብ ጳጉሜ 04/2014 ዓ.ም

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity #ድህረምረቃ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና የቅዳሜና እሁድ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች (የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ጨምሮ) ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 18/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

ከምዝገባው ቀን አስቀድሞ Official Transcript ለጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ፖ.ሳ.ቁ. 1020 ጅግጅጋ ማስላክ ያስፈልጋል።

የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል መፈጸም እና የምዝገባ ስሊፕ ለየትምህርት ክፍሎች መላክ እንደሚገባም ተገልጿል።

የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ትምህርት ጥቅምት 19 እንዲሁም የመደበኛ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JigJigaUniversity

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 07-08/2015 በመሆኑ ሁሉም መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ በተገለፁት ቀናት በመገኘት እንድትመዘገቡ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JigjigaUniversity

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለሪሜዲያል / Remedial የትምህርት ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 27 እና 28/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ (8) ፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ➧ regi@jju.edu.et


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመጀመሪኛ ዲግሪ አንደኛ ዓመት (Freshman) ወይም በ2015 ዓ.ም መደበኛ የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 06 እና 07 /2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ የስፖርት ትጥቅ፣ አንሶላ እና ጉርድ ፎቶግራፍ ልትይዙ እንደሚገባ ዩኒቨርሲቲው አስታውሷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ regi@jju.edu.et / info@jju.edu.et
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot