STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን ሊያዘናጋ እንደሚችል ተገለጸ።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈታናን ማለፍ ላልቻሉ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎች አማራጭ እንዳላቸው እንዲያስቡ እንደሚያደርጋቸው እና እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈታናን ወስደው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች በዩንቨርስቲዎቹ ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያው አቶ ቢኒያም ገ/እየሱስ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው የትምህርት ባለሙያ ዶ/ር አለማየሁ ከበደ የአቶ ቢንያምን ሃሳብ በማጠናከር ተማሪዎቹ አሁን ላይ #ባናልፍም ሬሚዲያል እንወስዳለን በሚል ተስፋ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አያደርጉም ብለዋል፡፡

በድጋሚ ለመፈተን በዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚቆዩት አንድ አመት ቢሆንም መንግስትን ላልተገባ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ትኩረት ተደርጎበት ከስር ከመሰረቱ ሊሰራ እንደሚገባ ባለሞያዎቹ አመላክተዋል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot