STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ
• በግንባታ ቴክኖሎጂ እና አስተዳደር
• በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ
• በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
ለመማር በኦንላይን ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ሐምሌ 11/2014 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በድረ-ገጽ መመልከት ይቻላሉ ተብሏል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#TVTI

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2015 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባን ከዛሬ
ጥር 23/2015 ዓ.ም እስከ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ያከናውናል።

በተቋሙ ዋና ግቢ ለመማር ያመለከታችሁና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ በተገለጹት ቀናት ይከናወናል።

፨መረጃው የ2014 ተፈታኝ ተማሪዎችን አይመለከትም‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የመውጫ_ፈተና_ውጤት
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተመራቂ ተማሪዎቹን የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

የተቋሙ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የመውጫ ፈተና ለሁለት ቀናት በኦንላይን መውሰዳቸው ይታወቃል፡፡

ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫንና "User Name" በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ጊዚያዊ ዲግሪ መውሰድ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች ፈተናውን በድጋሜ ከስድስት ወር በኋላ መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ውጤት ለመመልከት፡- https://result.ethernet.edu.et/

@NATIONALEXAMSRESULT
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 1,343 የተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎች 985 ተመራቂዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።

በነሐሴ መጨረሻ የተሰጠውን ፈተና ከወሰዱ ተመራቂዎች 74.34 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።

የመውጫ ፈተናው የኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከልን ጨምሮ በስምነት የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቷል።

በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ ስድስት) ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በሁለት የስልጠና መስኮች የመውጫ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና ጥር 27 እና 28/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ለ2ኛ ጊዜ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ የተቋሙ ተማሪዎች ፈተናው ጥር 17 እና 18/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነገረ ሲሆን "ከተቋሙ ውጪ በሆነ ምክንያት" ፈተናው በተባለው ጊዜ እንደማይሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

በዚህም ፈተናው የሚሰጥበት ግዜ ወደ ጥር 27 እና 28/2016 ዓ.ምመተላለፉ ተመላክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot