STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Ambouniversity

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ ብሎ በሰየመውና በግቢው ዋና በር ፊት ለፊት የተሰራው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ያሰራው ይህ የእውቁ አርቲስት ሀውልት ሲመረቅ ቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

©አምቦ ዩኒቨርሲቲ

#SHARE
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23,192 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

መረጃውን በማጋራት ላልሰሙ እናሰማ


ለበለጠ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ4 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛ፣ በክረምት እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከል ሁለቱ በ 'PhD' ሲሆኑ 23ቱ ደግሞ የሜዲሲን ተማሪዎች መሆናቸውን ሰምተናል።

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን የተከታተሉ 448 ተማሪዎች በዕለቱ ይመረቃሉ።

አንጋፋው አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት በቅርቡ ማክበር እንደሚጀምር የዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መንግስቱ ባላቻ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ተማሪዎች የ2016 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት ጥቅምት 07/2016 ይጀምራል ተብሏል።

የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AmboUniversity

በ2016 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፤ እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም) በዩኒቨርሲቲው ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ዉጤት አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነዉ ታህሳስ 4-5/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋን።

በተጠቀሰው ቀናት ብቻ በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋና ካምፓስ ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ አምቦ ከተማ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ተብሏል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትሄዱ ከ8 -12ተኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃ በሙሉ ዋናውንና ኮፒ፤ 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ፤ አንሶላ፤ ብርድልብስ፤ እንዲሁም ትራስልብስ ይዛችሁ መሄድ እንዳትዘነጉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 3,022 የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የተመደቡለት ሲሆን የተማሪዎቹ መግቢያ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም እንዲሆን የተቋሙ ሴኔት ትላንት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መንግስቱ ቱሉ (ዶ/ር) ለ #ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot