STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#የሥነ_ዜጋ እና #ሥነ_ምግባር ትምህርት ከ12ተኛ ክፍል #ፈተና እንዲወጣ ተደረገ‼️


ትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ ከሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርትን ሲያስወጣ፣ በአንጻሩ የኢኮኖሚክስ ትምህርት በማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ውስጥ ተካተተ።

በዚህ ዓመት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት መተግበር የጀመረው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የ12ተኛ ክፍል የፈተና ዝርዝር ላይ ለውጥ ማድረጉን ያሳወቀው ሐሙስ ጥር 9/2016 በጻፈው ደብዳቤ ነው። በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት ዓይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

#የተፈጥሮ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

#የማኅበራዊ_ሣይንስ፦ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።


የ12ተኛ ክፍል ፈተና ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የሚሰጠውን ትምህርት የሚያካትት ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና የሚወጣው ከ12ተኛ ክፍል ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል።

ኩረጃን እና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል በጥብቅ ቁጥጥር ውስጥ ከ2014 ዓ.ል. ጀምሮ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ መሰጠት የተጀመረው የ12ተኛ ክፍል ፈተና፤ ባለፉት ዓመታት እጅጉን ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የሚያልፉበት ሆኗል።

የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ፈተና መቼ ሊሰጥ እንደታሰበ ጥያቄ የቀረበላቸው የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ፤ “አሁን ከክልሎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው። በቅርቡ እናሳውቃለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot