STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ከጸጥታ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የማቋቋም ሂደት መዘግየቱ ተነገረ።

በርካታ የአፍሪካ ወጣቶችን በፓን አፍሪካ መርህ ለማስተሳሰርና የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን ለመፍታት ከተያዙት የአህጉሪቱ ትላላቅ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የፓንአፍሪካኒዝም ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ለመገንባት እቅድ ተይዞ የመሰረተ ድንጋይ መጣሉ የሚታወስ ነው፡፡

ለመሆኑ የዚህ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ከምን ደረሰ ሲል #መናኽሪያ_ሬድዮ የጠየቃቸው የኒው ሆራይዘን ፎር ፓን አፍሪካኒዝም ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ህይወት አዳነ ግንባታው በሚከናወንበት ትግራይ ክልል ባለፉት ዓመታት የነበረው ጦርነትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተዳምረው ስራው በሚፈለገው ልክ አለመከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ኒው ሆራዘን ፎር ፓን አፍሪካኒዝም ድርጅት እንደ ግብረሰናይ ድርጅት ከግንባታው ጋር በተያያዘ አስፈላጊው ሂደት ዳግም እንዲጀምር ከአፍሪካ ህብረትና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይቶች ማድረጉን ገልጸው ግንባታው ግን በዚህ ቀን ይጀምራል ለማለት የሚያስችል መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ ሰላም ያለበት በመሆኑ ስራዎች በቶሎ ተጀምሮ የአፍሪካዊያንን ህልም የማየት ውጥን እንዲሰምርም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ተብሏል፡፡

[ዘገባው የመናኸሪያ ሬዲዮ ጣቢያ ነው]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot