STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
41K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MoE

የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

አዋጁ (አዋጅ ቁ. 1298/15) ለትምህርት ሚኒስቴር ሀገራዊ የማስተባበር ስልጣን የሚሰጥ ነው።

አዋጁ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ ምርምር ተቋማት እና በኢንዱሰትሪው ዘርፍ መካከል ምቹ ትስስር በመፍጠር የትምህርት ጥራትን  ለማረጋገጥ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ለኢንዱስትሪ ዘርፍ በቂ እና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት የትስስር ሥራዎችን ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

አዋጁ ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ሲወያዩበት ቆይተው በቂ ግብዓትና ማሻሻያ ተደርጎበት መጽደቁ ተመላክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው። በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

#MoE

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርት ተከታታዮች ፈተና የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።

(ከላይ ያንብቡ)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 - መስከረም 23 ድረስ በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በ2016 ትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከዛሬ መስከረም 11 ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ይገባቸዋል።

ይህ ተከትሎ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ ይሰጣል።

የማለፊያ ነጥብ የሚወሰነው በትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱ ወዲያውኑ ማየት ይችላሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot

#MoE

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ትምህርት ውጪ ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሔደው ለሚያደርጓቸው የተግባር ላይ ልምምዶች የሚደረግ ወጪ÷ ከምርቃት በኋላ በሚከፍሉት የወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) መመርያ መሠረት ወደ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀላቀሉ አዳዲስ ተማሪዎች÷ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ተመርቀው እስኪወጡ ድረስ፣ መንግሥት ለምግብና ለመኝታ ያወጣውን ወጪ በሚገቡት ውል መሠረት ከምርቃት በኋላ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡

ተማሪዎች ወደ ተግባር ልምምድ ሲወጡ ለሚቆዩባቸው ጊዜያት ለሚኖራቸው የተግባር ላይ ትምህርት፣ ከምረቃ በኋላ ከወጪ መጋራት ጋር ተደምሮ እንዲከፍሉ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ዕቅድ መያዙንና ጥናት መጀመሩን፣ በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ተሾመ ዳንኤል ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ሐሳቡ በጥናት ላይ መሆኑንና ዓላማውም ወደፊት ተማሪዎች የተግባር ላይ ልምምድን ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ለማድረግ በማሰብ የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለክፍያው የልማት አጋር ድርጅቶች ለትምህርት ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ትስስር የሚመድቡት ገንዘብ ስለሚኖር፣ ከዚህ ገንዘብ ለወጪ መጋራት ሊከፈል የሚችልበት አሠራርም ሊዘረጋ እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ መማራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ (Letter of Proficiency) እንዲፃፍላቸው ለሚፈልጉ ትምህርት ሚኒስቴር አገልግሎቱን ይሰጣል።

ተገልጋዮች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ስትሔዱ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ፦

1. 12ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ዋናው ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣

2. በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ከሆነ፥ 10ኛ ክፍል ማጠናቀቃችሁን የሚገልፅ ዋናው ሰርተፊኬትና የማይመለስ አንድ ኮፒ፣

3. አመልካቾች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ /ፓስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ እንደሚጠበቅባችሁ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

አገልግሎቱ የሚሰጠው ሰኞ እና ሐሙስ በሥራ ሰዓት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም #አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ብሏል።

በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ያላለፉ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የሚያካሂዱት የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የሚመርጡት በዚህ ማስፈንጠሪያ (Link)
(https://exam.ethernet.edu.et)  ነው።

ስለሆነ ከጥር 08 እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በ " ቴሌ ብር " ብቻ በመክፈል መመዝገብ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል registration@ethernet.edu.et በኩል ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የሚፈቱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚያካሂዱትና  እና የአገልግሎት ክፍያ የሚፈፅሙት በተቋማቸው በኩል መሆኑን ገልጾ አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አመልክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot