STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#InjibaraUniversity

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠልና የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመጡ ተማሪዎች መካከል ስምምነት ላይ ተደረሰ!
.
.
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ለመቅረፍ ከሰኞ ማለትም ከቀን 08/02/12 ጀምሮ ምክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በምክክሩ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር አካላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይት ሂደቱም በዋናነት በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከሰቱት አላስፈላጊ ግጭቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሊንፀባረቁ እንደማይገባና ተማሪ ጥያቄ ካለው በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከሁሉም አካባቢ የመጡ ተማሪዎች ተቻችለውና ተከባብረው ለዩኒቨርሲቲውና ለሀገር ሰላም በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ብርሃኑ በላይ እና የሀገር ሽማግሌዎች ለተማሪዎች ምክር ሰጥተው፤ ለተገኘው ሰላምና በጋራ የመቆም መንፈስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከነገ ማለትም ከ12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

#Via_Injibara_University_FB_page

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች እና በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 03 እና 04/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ የተማሪነት መታወቂያ እና የሁሉም ሴሚስተር ግሬድ ሪፖርት ሊይዙ እንደሚገባ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በሌላ በኩል የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ የኤክስቴንሽን ተማሪዎች ምዝገባ ከታኅሳስ 22 እስከ 24/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል።

የኤክስቴንሽን ተማሪዎች የቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ታኅሳስ 30/2014 ዓ.ም ሲሆን በዕለቱ ትምህርት እንደሚጀመር ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#InjibaraUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ከግንቦት 09-11/2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት ከታች የተገለፁትን የመመዝገቢያ መስፈርት በማሟላት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

#እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ኮርስ ያጠናቀቁና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ ሰኔ 15 እና 16/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የምዝገባ ጥሪው በነርሲንግ፣ በሜዲካል ላብራቶሪ፣ በሚድዋይፈሪ፣ በአንስቴዥያ፣ አካባቢ ጤና፣ የህጸናት ጤና እና ሳይካትሪ ትምህርት ክፍሎች የተመደቡ ተማሪዎች ብቻ እንደሚመለከት ተገልጿል።

ሰኔ 18/2014 ዓ.ም ትምህርት ይጀምራል ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ ለመማር የማመልከቻ ጊዜን እስከ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም አራዝሟል።

የመግቢያ ፈተና ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም ያከናውናል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዕለቱ ያስመርቃል።

የመማር ማስተማር ሥራውን በ2010 ዓ.ም የጀመረው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፤ ዘንድሮ 3ኛ ዙር ሰልጣኞቹን ያስመርቃል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#InjibaraUniversity

በ2015 ዓ.ም ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ጽዱ፣ ውብ፣ በትምህርት ጥራት ተመራጭ፣ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ አድርጋችሁ እንድትመርጡ በአክብሮት እንጋብዛለን!

ስለ እንጅባራ በጥቂቱ፡-
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ መርኃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ   450 ኪ.ሜ ከአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ደግሞ 112 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አካባቢው ነፋሻማና ለጤና ምቹ በመሆኑ ብዙዎቹ ለኑሮ የሚመርጡትም ነው እንጅባራ፡፡

ከግንባታ ሥራዎች ጎን ለጎን አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን የጀመረው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ምቹ፣  ጽዱና ለዐይን ማራኪ ገጽታን ተላብሷል፡፡ በዚህም ከተማሪዎች እና ከተለያዩ አካላት ምስጋና እና እውቅና አግኝቷል፡፡  

በ2014 ዓ.ም በተደረገው የተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ምርጫም በሀገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከምርጥ አሥር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኗል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመደበኛና በተከታታይ ሞዳሊቲዎች 15,000 ተማሪዎችን በሰባት ኮሌጆችና አንድ ትምህርት ቤት ሥር በተደራጁ 58 ትምህርት ክፍሎች በማስተማር የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ጥራትን አንድ ወሳኝ የትኩረት መስክ አድርጎ ለይቷል፡፡

የትምህርት ጥራትን በአግባቡ ለመከወን ከ95 በላይ ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ አካዳሚክ ማዕረግ  እንዲሁም ከ500 በላይ የሌክቸረር ማዕረግ ያላቸውን መምህራን  በመያዝ እና መሰረታዊ የቤተ ሙከራ ግብዓቶችን በማሟላት ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት እየሠራም ይገኛል፡፡

ውድ ተማሪዎች ለውሳኔ እንዲረዳችሁ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡትን ፕሮግራሞች ከዚህ በታች ማየት ትችላላችሁ፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ አድርጉ፡፡

በፎቶ ከተገለጹት በተጨማሪ ፕሮግራሞችን ከታች በተገለጹትን ሊንኮች  መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

https://www.inu.edu.et/postgraduate-programs
https://www.inu.edu.et/undergraduate-programs

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot