STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል።

በጦርነት ምክንያት በክልሉ ያሉት ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኃላም ተማሪዎችን በፍጥነት ወደ ቀደመው የትምህርት ህይወታቸው እንዲመለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ዘግይቷል።

ከሰሞኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት እስኪጀመር #በሬድዮ እና #ቴሌቪዥን ትምህርት እንዲጀመር ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ስለማሳወቁ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅድሚያ ትንንሽ ህፃናት ላይ ትኩረት እንዳደረገ የገለፀው ቢሮው ይህም በአቅም ውስንነት እና በጀት ስለሌለው መሆኑን አመልክቷል። በሚዲያ ትምህርቱን ከመዋለህፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጿል።

የሬድዮ ትምህርት በድምፂ ወያነ፣ የቴሌቪዥን ትምህርት በትግራይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል ተብሏል።

ትምህርቱ ፤ የትግራይ ህፃናት በጦርነት ከደረሰባቸው ጫና እንዲወጡ ለማድረግና ለመደበኛው ትምህርት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ እንጂ ከክፍል ወደ ክፍል የሚያሻግራቸው እንዳልሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሬድዮ እና ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ትምህርት በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ ፤ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በሬድዮ የሚሰጠው ትምህርት ትግርኛ ፣ እንግሊዘኛ እና አካባቢ ሳይንስ ሲሆን በቴሌቪዥን ሒሳብን እንደሚያካትት አሳውቋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#በሪሜዲያል_ፕሮግራም ወደ ወለጋ ዩንቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ #የሪሜዲያል (#Remedial) #ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን መጋቢት 7 እና 8/ 2015 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።


ምደባ 👇
1. በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባቡ ሁሉም ተማሪዎች ነቀምቴ ካምፓስ ያመለክታሉ።
2. በማህበራዊ ሳይንስ ሰማችሁ በፊደል ተራ (እንግሊዝኛ) #ከM_Z የሚጀምር ተማሪዎች ነቀምቴ ካምፓስ ታመለክታላችሁ።
3. በማህበራዊ ሳይንስ ሰማችሁ በፊደል ተራ (እንግሊዝኛ) #ከA_L የሚጀምር ተማሪዎች ጊምቢ ካምፓስ ታመለክታላችሁ።


ምንጭ፡ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Tigray

ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል።

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#Update

መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ከሊል ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አደጋው ትላንት 1 ሰዓት ከ20 ላይ በዶዶላ ማዕከል ለማስተማር መምህራንን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ " ሰብስቤ ዋሻ " የሚባል አካባቢ ገደል ውስጥ ገብቶ መድረሱን ያብራራቱ ፕሬዜዳንቱ " አደጋው እጅግ በጣም አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

አደጋው እንዴት ሊደርስ ቻለ በሚለው ጉዳይ ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተጠየቁት ዶ/ር ኢብራሂም " መኪናው ገደል ውስጥ የገባበት ቦታ በተደጋጋሚ መሰል አደጋዎች የሚደርሱበት ቦታ ነው ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከአደጋው የተረፉና ህክምና ላይ ያሉ መምህራኖቻችን ናቸው እንዴት የተፈጠረ የሚለውን መረጃውን መስጠት የሚችሉት " ብለዋል።

" በአካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ግን መኪናው አደገኛ ኩርባ አለች እሱን ጨርሶ እንደወረደ ቀጥታ እንደገባ ነው የነገሩን " ሲሉ አክለዋል።

በአደጋው እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን የገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከጉዳት የተረፉ በዶዶላ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ሆስፒታሎች ህክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በህክምና ላይ ካሉት ቀላል ጉዳት እንዲሁም ከባድ ጉዳት የደረደባቸው ያሉ ሲሆን ተቋሙ እነሱን እየተከታተለ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ህይወታቸው ያለፈውን ወደ ጎባ ሆስፒታል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው " በብዛት የባሌ አካባቢ ተወላጆች ስለሆኑ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው ቤተሰቦቻቸው ወስደወል፤ ራቅ ራው ካሉ አካባቢዎች የመጡ መምህራኖቻችንን ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሽኝት እንዳረጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ለማስተማር ወደ ዶዶላ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ የዩኒቨርስቲው #መምህራን#ሠራተኞች እና #ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

28 የሚሆኑ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ አብረውት ለነበሩት የምዕራብ አርሲና የባሌ ዞኖች፣ የሻሸመኔ፣ አዳባ፣ ዶዶላና ሮቤ ከተሞች ነዋሪዎችና አመራሮች ዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች በተለይ አደጋው የተፈጠረበት አከባቢ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot