STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

የሬሜዲያል ተማሪዎች ፈተና ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

የሬሜዲያል/ማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ፈተናው በ30 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።

ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

በአማራ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል። እስካሁን 2.5 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከሌሎች ዓመታት አንጻር ሲታይ የተጓተተ መኾኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ጽ/ቤት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባው በተፈለገው ልክ መሔድ አለመቻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፉት ዓመታት የምዝገባ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው ዝቅተኛ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መኾኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ምዝገባው መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም የተማሪዎች ምዝገባ በተፈገው ልክ ባለመኾኑ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም መራዘሙን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች እንዲመዘገቡና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው መስከረም 14/2016 ዓ.ም እንዲጀመር ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ #አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ከ11,500 በላይ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

ፈተናቸውን ለማጠናቀቅ በድጋሚ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተማሪዎች በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ በሦስት ዞኖች እና በጎንደር ከተማ የመጡ መሆናቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅዓለም ጋሻው ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እንዲሁም የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር የትምህርት አይነቶች ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። #አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#Update

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እየተቀበሉ የሚገኙት ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሸኟቸውን ነባር ተማሪዎቻቸውን ነው።

ወለጋ ፣ አሶሳ ፣ መቱ እና ወ/ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተማሪዎቻቸውን መቀበል ከጀመሩ ተቋማት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የገጽ-ለገጽ ትምህርት መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

ከዚህ ከተማሪዎች ጥሪ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ሰላም በራቃቸው የአማራ ክልል ቀጠናዎች ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በክልሉ ያለው ሁኔታ ተማሪዎች በተባለው ቀን እንዲገኙ ላያደርጋቸው እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ እንዲያስብበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የፀጥታ ችግር መንገድ የመዘጋጋት፣ የተወሰኑ ቦታዎች ሙሉ ኔትዎርክ አለመስራት፣   የዳታ ኢንተርኔት መዘጋት፣ የደህንነት እጦት፣ የወላጆች ፍራቻና ሌሎችም ችግሮች ተደራርበው ጥሪውን ሰምቶ በተባለው ጊዜ ለመድረስ እንደሚያዳግት ማስገንዘባቸው ይታወሳል።

በተለይ በትግራይ ክልል እንደነበረው ተማሪዎች ከትምህርት እንዳስተጓጎሉ ፍርሃት እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ከዚህ ባለፈ በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን አለመጥራታቸው በተመሳሳይ አመት ከሚማሩ አቻ ጓደኞቻቸው ወደኃላ እንዳይቀሩ እንደሚያሰጋቸው በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ገልጸዋል። እነዚህም ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበው ነበር።

እስካሁን ተማሪዎች ባነሷቸው ስጋቶች ዙሪያ ምላሽ / ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በዘንድሮ ዓመት ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛነፈ የትምህርት ካላደር ለማስተካከል እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ብሄራዊ ፈተና፣ የመውጫ ፈተና ታሳቢ በማድረግ ጭምር የትምህርት ዓመቱ በአግባቡ እንዲሄድ ለማድረግ የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።

ፎቶ፦ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ሲመለሱ የሚያሳይ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (GAT) ምዝገባ ያደረጉ የተወሰኑ አመልካቾች ክፍያ ፈፅመው የማመልከቻ ሒደታቸውን ቢያጠናቅቁም የAdmission ቲኬት በመጠባበቅ ላይ (pending) እንደሆኑ ማወቁን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ችግሩን ለመፍታት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

አመልካቾች የAdmission ቲኬታቸውን ማግኘት የሚችሉበትን መፍትሔም እንደሚያመቻች አሳውቋል።

የተወሰኑ አመልካቾች Username and Password በኢሜይል እንዳልደረሳቸው መገንዘቡንም ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው የአመልካቾችን Username and Password በቀጥታ ለፈተና አስተባባሪዎች እንደሚልክና ተፈታኞች እንዲወስዱ ይደረጋል ተብሏል።

አመልካቾች Username and Password እንዲላክላቸው በመመዝገቢያው ፖርታል አማካኝነት ኢሜይል በማድረግ በመጠቀየቅ መውሰድ እንደሚችሉም ተመላክቷል።

የተሳሳተ ፎቶግራፍ በተወሰኑ አመልካቾች የAdmission ቲኬት ላይ መውጣቱን የገለጸው ዩኒቨርሲቲው፤ እነዚህ አመልካቾች የAdmission ቲኬታቸው እንዲታደስላቸው በመጠየቅ ማስተካከል እንደሚችሉ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 31, 224 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመሰጠቱ ተገለጸ


“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመስጠቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ቤቲንግ ቤቶችና ሌሎችም ቁጥር በማስገመት ለሚያጫወቱት “ኬኖ” አስተዳደሩ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ ይህን ጨዋታ በሚያጫውቱ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ጨዋታውን ሲያጫውቱ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

#ኢፕድ እንዳጣራው “ኬኖ” ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች እያዘወተሩት የሚገኝና በብዛት ብራቸውን የሚከስሩበት የቁማር ዓይነት ነው፡፡

(ኢ ፕ ድ)
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር ብሏል ሚኒስቴሩ።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል።

" የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።

በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም ለሪሚዲያል ተማሪዎች አውጥቶት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

የተስተካከለ የምዝገባ ጊዜ፦

➭ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም
የ4ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች (C2) እና በ2015 ዓ.ም መመረቅ የነበረባችሁ የጤና ሳይንስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ብቻ

➭ የካቲት 7 እና 8/2016 ዓ.ም
የ2ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር መደበኛ ተማሪዎች

➭ የካቲት 14 እና 15/2016 ዓ.ም
የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ነባር ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያገኛችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ የፍሬሽማን እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች

የምዝገባ ቦታ፦

➢ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደዉ በየነበራችሁበት ካምፓስ ነው።

➢ በ2016 ዓ.ም የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደዉ በዋናው ግቢ ብቻ ነው።

➢ በ2016 ዓ.ም አዲስ የሪሚዲያል የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-G የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችና እና ስማችሁ ከ A-H የሚጀምር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በቡሬ ካምፓስ የሚከናወን ሲሆን ስማችሁ ከተጠቀሱት ፊደላት ውጭ የሚጀምር ደግሞ በዋናው ካምፓስ የምትመዘገቡ ይሆናል።

Note:

በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች የምትገቡበት ባች በሚመዘገቡበት ቀን ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።


@NATIONALEXAMSRESULT


@studentsnewsadv35bot
#Update #WolloUniversity

በወሎ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓም በ Remedial program አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓም በ Remedial program አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 16 እና 17/05/16 ዓም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።በመሆኑም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ኮምቦልቻ ግቢ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ደሴ ግቢ የተመደባችሁ መሆኑን እንገልፃለን።

         ©ተማሪዎች ህብረት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም።

@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሲማሩበት ወደነበረው ተቋም መላኩንና  ተፈታኞችም ወዛው በመሔድ ማየት እንደሚችሉ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በተጨማሪም https://result.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት ውጤት ማየት ይቻላል።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

Via ቲክቫ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#ውጤት

ከፈተና የደንብ ጥሰት ጋር በተያያዘ

353 ተማሪዎች ላይ የሙሉ ፈተና ውጤት ተሰርዟል።

36 ተማሪዎች ላይ ደግሞ አንድ የትምህርት ዓይነት ተሰርዟል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
#update
#ውጤት

ካለፉት ሁለት ዓመታት የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል። በተለይ የተፈጥሮ ሳይንስ ውጤት።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (ትምህርት ሚኒስቴር)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
አጠቃላይ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ናቸው። ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ @NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#ውጤት

በ2016 ዓ.ም በአጠቃላይ ያለፉ ተማሪዎች 5.4% ተማሪዎች አልፈዋል።

ጠቅላላ ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር 36,409 ተማሪዎች አልፈዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
#update
#ውጤት

በሀገር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በትግራይ ነው።

በትግራይ ፈተናው ከ700 ነው የተሰጠው።

ከቀላሚኖ 675 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በወንድ ተማሪ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ  ጊዜ ነው ተብሏል።

ሌላ በሀገር ደረጃ ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ነው ከተፈጥሮ ሳይንስ፤ ሴት ናት። ከማህበራዊ ሳይንስ 538 ተመዝግቧል።

በተፈጥሮም በማህበራዊ ሳይንስም ትልቅ ውጤት የመጣው በሴቶች ነው።


በኦንላይን ከተፈተኑት ተማሪዎች ውስጥ 26.6% ያህሉ አልፈዋል

በወረቀት ከተፈተኑት ተማሪዎች ውስጥ 4.4% ያህሉ አልፈዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
ዘንድሮ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ላይ ትኩረት እንሰጣለን። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ @NATIONALEXAMSRESULT
#update

የትም ሀገር ላይ 50% ተማሪ ዩኒቨርሲቲ አይገባም። 25% ከገባ በራሱ ትልቅ ውጤት ነው። የዘንድሮው ውጤት ልጆቻችን ማጥናት ሲጀምሩ እና በአቋራጭ የትም እንደማደረስ ሲያውቁ፣ ትምህርት ቤቶችቻችን መትጋት ሲጀምሩ ለውጥ እንደሚመጣ አሳይቶናል።

ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ካሪኩለም ትምህርት መሰጠት ሲጀመር ደግሞ የበለጠ ውጤት እናያለን።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update #ውጤት #ሬሚዲያል

የሬሚዲያል (ማካካሻ) ትምህርት ዘንድሮም ከአምናው አንፃር በቁጥር ቢቀንስም (ሬሚዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ቢቀንስም) ይሰጣል። ቀስ በቀስ ቁጥሩን እየቀነስን ሙሉ ለሙሉ እናቋርጠዋለን።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT