STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#DillaUniversity

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ሰልጣኞችን ተቀብሏል።

የስቴም ማዕከሉ በጌዲኦ ዞን ከሚገኙ 8 ወረዳዎች እና 5 ከተማ አስተዳደሮች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያላቸው 300 ተማሪዎችን ለማሰልጠን መቀበሉን የዩኒቨርሲቲው ስቴም ማዕከል ዳይሬክተር ተካልኝ ታደሰ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርት መስኮች ለሁለት ወራት ስልጠና ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ሰልጣኞቹ በቆይታቸው የመኝታ፣ ምግብ እና ሕክምና አገልግሎት በዩኒቨርሲቲው እንደሚቀርብላቸው ተገልጿል።


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#DillaUniversity

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

ሚኒስቴሩ በፈታኝነት እና ለአይነ-ስውራን ተፈታኞች አንባቢነት ከመምህራን ብቻ፣ በመልስ መስጫ ወረቀት ቆጣሪነትና አደራጅነት ከመምህራን፣ ቴክኒካል ረዳቶች፣ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ካላቸው የአስተዳደር ሰራተኞች መካከል መልምሎ እንድሊኩ ዩኒቨርሲቲዎችን አዟል።

በዚህም የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ቴክኒካል ረዳቶች እና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች፦

• የዲላ ዩኒቨርሲቲ መታወቂያና ኮፒ
• የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርትና ኮፒ
• ከትምህርት ክፍል/ዘርፍ መስፈርቶቹን ስላማሟላታችሁ የሚያስረዳ የድጋፍ ደብዳቤ

👉 የምዝገባ ቦታ፦ ኦዳያአ ግቢ አዲሱ የአስተዳደር ህንፃ፣ 1ኛ ፎቆ፣ ቢሮ ቁጥር FF-036

👉 የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ነሐሴ 30/2014 ዓ.ም (ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ)

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

➤የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ
    ➭ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም

➤የ3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ
    ➭ ኅዳር 05 እና 06/2015 ዓ.ም

➤ የጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች (ከ2ኛ ዓመት ጀምሮ) ሪፖርት ማድረጊያ
    ➭ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎች ነገ ኅዳር 10/2015 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 229 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምሩቃን በተጨማሪ በሌሎች ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ፣ በክረምት፣ በቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 4 ሺህ 615 ተማሪዎችም ተመርቀዋል።

ከሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተመራቂ የሆነችው ኢክራም ጀማል CGPA 4.00 በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቅሬታ‼️ #DillaUniversity

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሰመራ ካምፓስ ተማሪዎች ግቢያቸው ውስጥ የሚከሰተው የዝርፊያ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ ስጋት እየፈጠረባቸው እንደሆነ ገልፀውልናል።

ትላንት ምሽት 5፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ ተማሪ ላይ የዝርፊያ እና የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመ በርካታ የሰመራ ካምፓስ (ዲላ ዩኒቨርስቲ) ተማሪዎች የገለፁልን ሲሆን ዩንቨርሲቲው እየደረሰ ያለውን የዝርፊያና ተያያዥ ወንጀሎች መፍትሄ ሊሰጠን አልቻለም ሲሉ የግቢውን አስተዳደር ክፉኛ ወቅሰዋል።

ዝርፊያው የሚፈፀመው ከግቢ ውጭ በምሽት ሰርገው በሚገቡ አካላት መሆኑን የገለፁት ተማሪዎቹ ስልክ፣ላፕቶፕ፣ልብስ፣ ገንዘብ እና የመሳሰሉትን ነገሮች ለመዝረፍ ሲሉ በተማሪዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ዩንቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

○ Atc

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል የትምህርት ፕሮግራም በተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ እንደሚያደርግ ግልጿል፡፡

ተቋሙ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በቅርቡ እንዳጠናቀቀ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ የሚዲያ ገጾቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ www.du.edu.et ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ በተቋሙ የተመደባችሁ ተማሪዎች በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

በ2015 ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 14 እና 15/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-

➧ የማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በሐሴዴላ ግቢ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በኦዳያአ ግቢ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ትምህርት የሚጀመረው ➧ መጋቢት 18/2015 ዓ.ም

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

በ2016 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦

በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ (ኦዳያኣ ካምፓስ) በሚገኘው ሬጂስትራር ጽ/ቤት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ 3x4 የቅርብ ጊዜ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot