STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በደቡብ ወሎ ዞን 85 ሴንቲ ሜትር የምትረዝመዉ አጭሯ ተማሪ ትምህርቴን በአግባቡ እንዳልማር በርካታ ችግሮች ገጥመዉኛል ስትል ተናገረች

በደቡብ ወሎ ዞን በአምሐራ ሳይንት ወረዳ 85 ሴንቲ ሜትር የምትረዝመው አጭሯ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ትምህርቴን በአግባቡ እንዳልማር በርካታ ችግሮች አሉብኝ ማለቷ ተነግሯል ።

የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ አማከለች ጌታቸው የምትባል ሲሆን 28 ዓመት እንደሆናት እና በደቡብ ወሎ ዞን በአምሐራ ሳይንት ወረዳ በ 032 ቀበሌ ጭቅማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መወለዷ ተገልጿል ። ትምህርቷን በአምሐራ ሳይንት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እየተከታተለች ትገኛ፤ች ። ነገር ግን የምትኖርበት የቤተሰቦቿ መኖሪያ ቤት እና ትምህርቷን የምትከታተልበት ቦታ የሚራራቅ ከመሆኑ በተጨማሪ የትራንስፖርት አለመኖሩ ለመማር ችግር እንደሆነባት መናገሯን የአምሐራ ሳይንት ወረዳ ትምህርት ጽ/ት ቤት ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ክንዱ ጥላሁን ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ቤተሰቦች ስላሉኝ በትምህርት ቤት አቅራቢያ ቤት ተከራይቼ ለመኖር አልቻልኩም ትላለች ። ከአሁን ቀደም በበቅሎ ለመመላለስ ሞክራ ለመውጣት እና ለመቀመጥ አለመቻሏን ታነሳለች ። ስለሆነም አቅሙ ከሚፈቅድ ማንኛውም አካል እርዳታ እንደምትፈልግ መናገሯን አ/ቶ ክንዱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በካፋ ዞን ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸው 522 የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በካፋ ዞን በሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በመንግስት መስሪያ ቤቶች እስካሁን በተደረገ ማጣራት 522 ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሰራተኞች እና አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

የካፋ ዞን አስተዳዳር  ጽ/ቤት ኃላፊና በዞኑ የሀሰተኛ ትምህርት አጣሪ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ገብሬ እንደገለፁት ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ባለሙያዎች የትምህርት ማስረጃ የማጣራት እና የፍተሻ በቀጣይም ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን መሆኑን ተናግረዋል።

ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የትምህርት ጥራትን ከመጉዳትም ባሻገር የሀገር ዕድገትና ኢኮኖሚን ወደ ኃላ የሚጎትትና የተማረ የሰው ሀይል በተፈለገው ቦታ ላይ ተመድቦ እንዳይሰራና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰቡ ከመስጠት አንፃር እንቅፋት እንደሆነም ገልፀዋል ።

የማጣራት ሂደቱ እስከ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ የሚሄድ በመሆኑ ጊዜ እና ሃብት የሚፈጅ ቢሆንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመንግስት መስሪያ ቤት የሚገኙ አካላት የመንግስትን ሃብት ከማባከን ባሻገር ባልተማሩበት ሙያ በሃሰት ማስረጃ ህዝቡ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ እንደነበርና ከስራ እና ከደመወዝ ከመታገድ ባሻገር በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን ትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ለብስራት ሬዲዮ በላከው መግለጫ አመላክቷል።

በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለሸገር የተማሪዎች ሰርቪስ ተጠቃሚ ተማሪ ወላጆች በሙሉ

የተማሪ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ወላጆች በሙሉ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግልት ድርጅት የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ህዳር 24/2015 ዓ.ም በተማሪ ሰርቪስ ታሪፍ ዙሪያ ከወላጆች ጋር የምክክር መድረክ ማዘጋጀቱን ብስራት ራዲዮ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል። በመሆኑ በእለቱ ወላጆች እንድትገኙ ሲል ጥሪዉን አቅርቧል። የውይይት ቦታዎቹንም ገልጿል --

1ኛ. በቃሊቲ ዴፖ ስር የምትገለገሉ የተማሪ ወላጆች ውል በገባችሁበት በቃሊቲ ዴፖ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ

2ኛ. በሸጎሌ ዴፖ ስር የምትገለገሉ የተማሪ ወላጆች ውል በገባችሁበት በሸጎሌ ዴፖ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ

3ኛ. በመካኒሳ ዴፖ ስር የምትገለገሉ የተማሪ ወላጆች ውል በገባችሁበት የመካኒሳ ዴፖ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ

4ኛ. በሰሚት ዴፖ ስር የምትገለገሉ የተማሪ ወላጆች 22 እየሩስ ህንፃ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ስለሚካሄድ  ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች እንድትገኙ ሲል ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የጋና ፕሬዝዳንት በመሳደባቸዉ ከትምህርት ቤት የተባረሩት ተማሪዎች ይቅርታ ጠየቁ

በትላንትናዉ እለት የጋናውን ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶን ሲሳደቡ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ ከትምህርት ቤት የተባረሩ ስምንት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ይቅርታ በማለት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ጠይቀዋል።ተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት ፕሬዝዳንቱን፣ ርዕሰ መምህሩን፣ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ እና ጋናውያንን ይቅርታ እንጠይቃለን ቪዲዮ በዚህ ደረጃ ይሰራጫል ብለን አልጠበቅንም ነበር ብለዋል።

የልጅነት ጨዋታ ነበር፣ እናዝናለን እናም ፕሬዝዳንቱ ወደ ትምህርት ገበታችን እንድንመለስ ያድርጉን ሲሉ ተንበርክከዉ ተማሪዎቹ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡የጋና የትምህርት አገልግሎት በበኩሉ "የተማሪዎቹን ድርጊት ተቀባይነት የሌለዉና በጋና የትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚፈለገውን የስነምግባር መመዘኛን የሚጻረር ነው” ሲል ገልጿል።

የጋና መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲና ፓርላማ አባል በበኩላቸዉ በተማሪዎቹ ላይ ከትምህርት እንዲታገዱ የተደረሰበት ውሳኔ ከባድ እና ኋላ ቀር ነው በማለት ፤ፕሬዚዳንቱ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል፡፡ዘግይቶ በወጣ መረጃ መሰረት ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶን በመሳደብ የተባረሩ ስምንት የጋና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ መፈቀዱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንት አኩፎ-አዶ የቺያና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን መባረርን በመቃወም ጣልቃ መግባታቸዉን ገልጸዋል፡፡የጋና ትምህርት አገልግሎት "ተማሪዎቹን ከመባረር ይልቅ አማራጭ የስነምግባር እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ተሰጥቷል" ሲል የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
@NATIONALEXAMSRESULT


@studentsnewsadv35bot
በመቀሌ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉ ተሰማ

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉን ብስራት ራዲዮ ከነዋሪዎች አረጋግጧል። በስልክ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፤ አንዳንድ የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመሩን እና ህጻናት ወደ ትምህርት ቤቶች መሄድ መጀመራቸዉን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ትምህርት ጀምረዋል ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የመንግስት የትምህርት ተቋማት እስካሁን አመለመጀመራቸዉን ነዋሪዎቹ አክለዋል።

በክልሉ የትምህርት መጀመሩን ለማረጋገጥ ብስራት ራዲዮ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯን ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤልን ጠይቆ ባገኘዉ ምላሽ ፤ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዳግም በክልሉ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ነዋሪዎችም በቅርቡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ይጀመራሉ መባሉን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በክልሉ የኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ ትምህትርት ተዘግቶ የቆየ ሲሆን በግዜያት በኋላ በተቀሰቀሰው ግጭትም ተማሪዎች ለሶስት አመታት ገደማ ከትምህርት ገበታቸዉ ርቀዉ ቆይተዋል።

ብስራት ራዲዮ ከዚህ ቀደም በሰራዉ ዘገባ ፤ በጦርነቱ ወቅት የቄስ ትምህርት መደበኛዉን የትምህርት ስርዓት ተክቶ ህጻናት ፊደል እንዲቆጥሩ እና መሰረታዊ እዉቀት እንዲያገኙ የራሱን አስተዋጽኦ ሲወጣ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
⚠️⚠️⚠️ አስቸኳይ ⚠️⚠️⚠️
⚠️⚠️⚠️ #SHARE ⚠️⚠️⚠️

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ሁለት ዓመት ያልሞላትን ህጻን ልጅ ሞግዚቷ ይዛት መሰወሯ ተሰማ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ሰፈር ልዩ ስሙ ኤልቤተል ቁጥር 2 ትምህርት ቤት ጀርባ ከሚገኘው የህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት ሶሊያና ዳንኤል የተባለችዋን ሁለት ዓመት ያልሞላትን ህጻን ቤዛዊት በቀለ የተባለችው ሞግዚቷ ይዛት መሰወሯን የህጻኗ አክስት የሆኑት መድሃኒት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በደላላ አማካይነት ባሞግዚትነት  የተቀጠረችው ግለሰቧ ገና 20 ቀኗ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የልጅቷ አያት በተኙበት ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ አዲስ ሰፈር ከሚገኘው መኖሪያ በት ይዛት መሰወሯ ተነግሯል፡፡

በትራንስፖርትና መንገድ ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን ህብረተሰቡ ከተመለከተ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ፈላጊ ቤተሰብ ጥሪ አቅርበዋል።


#ዳጉ_ጆርናል
@NATIONALEXAMSRESULT
በሀድያ ዞን በጨዋታ ላይ የነበረው የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ህፃን ስስ ብልቱን ተመቶ ህይወቱ አለፈ

በሀድያ ዞን ሻሽጎ ወረዳ የእርግጫ ጨዋታ ላይ ከነበሩ ሁለት ህፃናት መካከል የዘጠኝ ዓመቱ ታዳጊ ህፃን ስስ ብልቱ በእርግጫ ተመቶ ህይወቱ ማለፉን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ይህው ድርጊት የተሰማው በሻሾጎ ወረዳ ፎፎ ቀበሌ ሲሆን ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በጨዋታ ላይ የነበሩት የ9 ዓመቱ እና የ12 ዓመቷ ዓመቷ ሴት ታዳጊ ህፃናት እርስ በርስ የእርግጫ ጨዋታ ሲጫወቱ ስስ ብልቱ  የተረገጠዉ ህፃን   በደረሰበት ከባድ ጉዳት ለህክምና እንኳን ሳይበቃ  ህይወቱ አልፏል።

የታዳጊዉ ህይወት ማለፉን ተከትሎ በግድያ ወንጀል የተጠረጠረችዉ የ12 አመቷ ህፃን ብቻዋን ወደ ፖሊስ ጊዜያዊ ማረሚያ ቤት ዉስጥ ገብታ የምትሰጠዉ የተከሳሽነት ቃል ህጋዊ መሠረት ስለማይኖረዉ ወላጅ አባቷን በቁጥጥር ስር በማዋል የክስ መዝገባቸው በመጣራት ላይ መሆኑን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"አፍጥጡ🤔" | ሆንግ ኮንግ አጫሾችን አፍጥጦ በመመልከት ሲጋራ የሚጨስባቸውን ቦታዎች ለመቀነስ እየሞከረች ትገኛለች

የቻይና አካል ሆና በራስ ገዝ መስተዳድር የምትተዳደረው ሆንግ ኮንግ ከሲጋራ የፀዱ አካባቢዎችን ለመፍጠር  የተለያዩ ጥብቅ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ቁጥጥሩም ፍሬ ያፈራ ይመስላል። በ1980ዎቹ ከህዝቧ 23 በመቶ የሚሆነውን ሲጋራ አጫሽ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏታል።

በሆንግ ኮንግ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ሲጋራ ማጨስ ፈፅሞ የተከለከለ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ህጉ ሳይፈፀም የሚቀርበት ጊዜ አለ።

ለዚህ ነው የሆንግ ኮንግ ጤና ሚኒስትር  ፕሮፌሰር ሎ ቹንግ ማው አጫሾች ላይ ማፍጠጥን እንደ መፍትሔ የወሰዱት።

ፕሮፌሰሩ <<በሬስቶራንትም ሆነ ሰው በተሰበሰበበት ስፍራ ሲጋራ ለመለኮስ ከኪሳቸው የሚያወጡትን አፍጥጡባቸው። አስተያየታችሁ ኮስተር ያለ ይሁን። ያኔ አይሞክሩትም>> ይላሉ።

ሚኒስትሩ <<እስኪ የአውቶብስ ሰልፍን ተመልከቱ። ተሰለፉ የሚል ህግ የለም። ግን ሰዎች በራሳቸው ልማድ ይሰለፋሉ። ይሄንን ልምምድ በሲጋራ አለማጨስ ላይ ልናመጣው ይገባል። ይህም ከሲጋራ የፀዱ ከተሞችን ለመፍጠር ያስችላል>> ሲሉ መናገራቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

@NATIONALEXAMSRESULT
በነገዉ እለት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በአዲስአበባ ይሰጣል ተባለ

ነገ ጷግሜን 1/2015 ዓ.ም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

አገልግሎቱን የሚሰጡት የከተማ አውቶብስና የከተማ ቀላል ባቡር መሆናቸዉን ቢሮዉ ገልጿል።

#ዳጉ_ጆርናል

@NATIONALEXAMSRESULT
የአርሲ ዮኒቨርሲቲ ለክቡር ሼክ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል

#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot