#ሀዋሳዩኒቨርሲቲ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በፈተና አወጣጥና የተማሪ ምዘና ዘዴዎች ላይ ለመምህራኑ ስልጠና ሰጠ።
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በስልጠናው መርሃግብር መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት መምህራን በጉዳዩ ዙሪያ ምንም እንኳ ልምድና ዕውቀት ቢኖራቸውም ወቅቱን ያገናዘበ የመነቃቅያ ስልጠና አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ስልጠናውን ማዘጋጀታቸን አስረድተዋል።
ስልጠናው የተዘጋጀው ከመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት በተለይም በወጣት መምህራን ዘንድ የትምህርት አሰጣጥና የፈተና አዘገጃጀት ላይ ክፈተት መኖሩን በተማሪዎች ከተሰጠ ጥቆማ በመነሳት እንደሆነ ገልፀው ዓላማውም መምህራን በዒላማና መሠረታዊ የትምህርት ይዘትና ዝግጅት ላይ የተመሠረተ የሥነ-ማስተማር እና ምዘና ዘዴዎችን በመከተል ተማሪዎቻቸውን በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አጋዥ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ለማስቻል መሆኑን አብራርተዋል።
በኮሌጁ የጥራት ማሻሻያ ኃላፊና የሰልጠናው አስተባባሪ ዶ/ር በየነ ተክሉ በበኩላቸው ጥራት የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ጠቁመው የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በመከተል ከተማሪዎችና የኮሌጁ ማኅበረሰብ ጋር በመወያየት መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ኮሌጁ ተማሪዎቹን በማሳለፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም ውጤቱን አስጠብቆ ለመቀጠል የመምህራን የሙያ ክህሎት ስልጠና አጋዥ መሆኑ ስለታመነበት ስልጠናው መዘጋጀቱንም ኃላፊው አብራርተዋል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT