STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ስድስት መቶ ቤት ካመጡ ተማሪዎች በላይ ይሄ ልጅ ደስተኛ ነው 😍😁

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
“ዩኒቨርሲቲው የመምህራንን ክብር የሚመልሱ ተመራቂዎችን ማፍራት ይጠበቅበታል”
- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር
****
(ኢ ፕ ድ)
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የመምህራንን ክብር የሚመልሱ ተመራቂዎችን ማፍራት ይጠበቅበታል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው በማኀበረሰቡ ዘንድ መምህራን ያጡትን ክብር የሚመልስ ተማሪ ማፍራት ይጠበቅበታል። የትምህርት ዩኒቨርሲቲው በማስተማር ተግባሩ ጠንካራ የሞራል መሰረት ያላቸው፣ ሙያቸውን የሚያከበሩ መምህራንን ለሀገሪቱ ማብቃት ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዋነኛ ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ህንፃ መገንባት ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲው ይህን አካሄድ በመቀየር ዕውቀት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይኖርበታል ብለዋል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ የተማሩ ሰዎች ቁጥር በርካታ ቢሆንም ከጥራት አንጻር ሲታይ ክፍተቶች…….

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=111232

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትግራይ ክልል ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና ተጠናቀቀ
*
(
ኢ ፕ ድ)

በትግራይ ክልል ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርትና ብሔራዊ ፈተና ምዘና ቢሮ ገለፀ፡፡

የትምህርትና ብሔራዊ ፈተና ምዘና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍስሃ እንዳሉት፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከሁለት ወር በፊት በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች የማካካሻ ትምህርት ሲወስዱ የቆዩ ሲሆን፤ፈተናው ዛሬ ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ምንም እንኳ የቆዩበት ሁኔታ እጅግ አስከፊ የነበረ ቢሆንም፤ለሁለት ወራት ዩኒቨርሲቲ ገብተው የማካካሻ ትምህርትና የስነ ልቦና ዝግጅት ሲያደርጉ በመቆየታቸው የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሊረዳቸው ይችላል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
“በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የታየውን ውጤት ለመቀየር ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና ይጠናከራል” የትምሕርት ምዘናና እና ፈተናዎች አገልግሎት

ባሕር ዳር: ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ለመቅረፍ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንደሚጠናከር የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ፡፡

በአገልግሎቱ የፈተና አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ወንደሰን ኢየሱስወርቅ ለውጤት መቀነስ አንዱ ምክንያት ተማሪዎች በታችኞቹ የትምህርት ደረጃዎች በተገቢው ፈተና እየወሰዱ አለመምጣታቸው ነው ብለዋል።

ይህም ተማሪዎች በየደረጃው ማወቅ ያለባቸውን እንዳያውቁ ማድረጉን ገልጸው፤ በስተመጨረሻ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ የሚያደርግ መኾኑን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ተማሪዎች በተገቢው ምዘና እንዲያልፉ ይደረጋል በማለት ገልጸው፤ ይህንንም ለመተግበር በ8ኛ ክፍል የሚሰጠውን ፈተና ከማጠናከር ባለፈ በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ምዘና ለማጠናከር እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

ፋና እንደዘገበው ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉን አቀፍ የማሻሻል ሥራዎች እንደሚያስፈልግ የፈተናዎች ሥራ አስፈፃሚ ወንድወሰን ኢየሱስ ወርቅ ተናግረዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የምስራች @#Exitexam Tutorial
🥇 ለአካውንቲንግ
🥇 ለማኔጅመንት
🥇 ለቢዝነስ ማኔጅመንት
🥇ለማርኬቲንግ ማኔጅመንት
🥇ለሲቪል ምህንድስና
🥇ለኮምፒውተር ሳይንስ
#የመውጫ ፈተና መዘጋጃ #ልዩ ትምህርት
➾  በአንጋፋ ፕሮፌሰሮችና የዪኒቨርስቲ
      መምህራን
➾ በት/ት ሚ/ር ለፈተና በተመረጡ ኮርሶች
      ላይ ብቻ: የፈተና ጥያቄዎች ላይ በማተኮር
➾ በቂ የጥናት ሞጁሎች
➾ ሞዴል የመለማመጃ ፈተናዎች ከሙሉ
      መልስና ማብራሪያ  ጋር
➾ የኦንላየን መለማመጃ   ሲስተም
➾ ውጤታማ የፈተና አሰራር ሥልጠና
***
💥 እጅግ በተመጣጣኝ ክፍያ 

🛎 በየማዕከላቱ ያሉ ውስን ቦታዎች ቀድመው
      ይያዙ
🔔 ሙሉ  ስምዎን  : የስልክ ቁጥርዎንና
     ዲፓርትመንትዎን 0908-198-786 
      ላይ ቴክስት በማድረግ ይመዝገቡ ።
➾➾➾➾➾➾
ለበለጠ መረጃ
➧ 0908198786 ማነጋገር ይቻላል።

➧➧     #Joinus @ t.me/aec_ethiopia

አድቫንስድ የት/ት ማማከር ማዕከል
           ከፍላጎትዎ ባሻገር !!!
በሴት ተማሪዎች ላይ በተለይም ትኩረት ባነሰው ከ1 -12ኛ ክፍል ባሉ ሴት ተማሪዎች ላይ ከተማሪዎች ብቻ ሳይሆን በሚያስደነግጥ ሁኔታ ከመምህራንም የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች እና ትንኮሳዎች እየተባባሱ መጥተዋል። እኛም በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳባችንን ስናሰማ ቆይተናል።

ዛሬም እንዲሁ አሳፋሪ ክስተት ሰምተናል። ስለዚህ ጉዳይምን ያህል እያሰብን ይሆን?
ትኩረታችንን ተማሪዎች ላይ ብቻ ስናደርግ የመልካም መምህራንን ስም የሚያጠለሹ እንዲህ ያሉ መምህራንንስ ጉዳይ ለማን ተውነው?

@NATIONALEXAMSRESULT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ካልሳምሺኝ ቦርሳሽን አልሰጥሽም" ይህን የሚለው መምህር ነው!"

አሁን ከባለታሪኳ ተማሪ ጋር አውርተን መመለሳችን ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው። ተማሪ ናርዶስ ሀገር ሰላም ብላ ዩኒፎርሟን ለብሳ ወደ ት/ቤቷ ብታመራም በር ላይ ስትደርስ ግን የተማሪ መታወቂያ በመርሳቷ በር ላይ ካለቺው ፈታሽ ጋር አለመግባባት ውስጥ ትገባለች።

ይህንንም ተከትሎ ፈታሿ ቦርሳዋን ትነጥቅና አልሰጥም ትላታለች። እርሷም ቢያንስ ቦርሳው ውስጥ የታክሲ ብር ስላለ እሱን ስጪኝና መታወቂያዬን ከቤት ይዤ ልምጣ ብትልም ሰሚ ግን አላገኘችም።

ታድያ አንድ መምህር ይመጣና ቦርሳውን ከፈታሿ ተቀብሎ ናርዶስንም ለብቻዋ ጠርቶ የሆነውን ነገር ይጠይቃትና እርሷም ትነግረዋለች። እርሱ ግን የተሰጠውን ኃላፊነት በመዘንጋትና መምህር እንደመሆኑ መጠን እንደ አባት መጠበቅ ሲኖርበት " ሳሚኝና ቦርሳሽን ልስጥሽ" የሚል አሳፋሪ ጥያቄ ይጠይቃታል። እንዲያውም ወይ ሳሚኝ ወይም ቦርሳሽን እርሺው ይላታል።

ተማሪዋም በድንጋጤ ቦርሳዋንም ትታ ወደቤቷ ትመለሳለች። አሁን ላይ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው ማሳወቋን ነግራናለች።

እርሷ በድፍረት ይህን ጉዳይ ወጥታ ተናገረች! ጓዳ የተደበቁ ከዚህም የባሱ አሰቃቂ የትምህርት ቤት ክስተቶችን ግን ማን ይያቸው?

ስለሁሉም ተማሪ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
" የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል "

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ​​ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።

የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#የምስራች @#Exitexam Tutorial
🥇 ለአካውንቲንግ
🥇 ለማኔጅመንት
🥇 ለቢዝነስ ማኔጅመንት
🥇ለማርኬቲንግ ማኔጅመንት
🥇ለሲቪል ምህንድስና
🥇ለኮምፒውተር ሳይንስ
#የመውጫ ፈተና መዘጋጃ #ልዩ ትምህርት
➾  በአንጋፋ ፕሮፌሰሮችና የዪኒቨርስቲ
      መምህራን
➾ በት/ት ሚ/ር ለፈተና በተመረጡ ኮርሶች
      ላይ ብቻ: የፈተና ጥያቄዎች ላይ በማተኮር
➾ በቂ የጥናት ሞጁሎች
➾ ሞዴል የመለማመጃ ፈተናዎች ከሙሉ
      መልስና ማብራሪያ  ጋር
➾ የኦንላየን መለማመጃ   ሲስተም
➾ ውጤታማ የፈተና አሰራር ሥልጠና
***
💥 እጅግ በተመጣጣኝ ክፍያ 

🛎 በየማዕከላቱ ያሉ ውስን ቦታዎች ቀድመው
      ይያዙ
🔔 ሙሉ  ስምዎን  : የስልክ ቁጥርዎንና
     ዲፓርትመንትዎን 0908-198-786 
      ላይ ቴክስት በማድረግ ይመዝገቡ ።
➾➾➾➾➾➾
ለበለጠ መረጃ
➧ 0908198786 ማነጋገር ይቻላል።

➧➧     #Joinus @ t.me/aec_ethiopia

አድቫንስድ የት/ት ማማከር ማዕከል
           ከፍላጎትዎ ባሻገር !!!
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማታ እና የእረፍት ቀናት መርሐግብር የመጀመርያ ዲግሪ የአንደኛ ዓመት (በ2015 ዓ.ም የገቡ) ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ከጥቅምት 08 እስከ 10/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
“የተማሪዎች መውደቅ የትምህርት ሥርዓቱንና የትምህርት ሥርዓቱን የሚመራውን ተቋም ውድቀትና ክሽፈት ማሳያ ነው” እናት ፓርቲ

👉ፓርቲው ኹሉም ተማሪዎች ፈተናውን በድጋሚ እንዲፈተኑ ጠይቋል

ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 817 ሺሕ 832 ተማሪዎች መውደቃቸው የትምህርት ሚኒስቴርን የአሰራር ሂደት፣ የፈተና አወጣጥ፣ የግምገማ እንዲሁም መለኪያ መንገዶች ተአማኒነትን ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱ ባሻገር፤ ኹኔታው የተፈታኝ ተማሪዎችን መውደቅ ሳይሆን የትምህርት ሥርዓቱንና የትምህርት ሥርዓቱን የሚመራውን ተቋም ውድቀትና ክሽፈት ማሳያ ነው ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ።

ፓርቲው የ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ “በትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ የተሰጠበት የፈተናው ውጤት፤ ጥሮ ግሮ በመስራት "ልጄን ለቁምነገር አበቃለሁ" ብሎ ለዘመናት ያስተማረውን የአገራችንን ሕዝብ ክፋኛ አሳዝኗል፡፡” ብሏል።

በተጨማሪም ውጤቱ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተስፋ መቁረጥ እና የማይሽር ሥነ-ልቡናዊ ተጽእኖን ማሳደሩን ገልጿል።

ፓርቲው አክሎም፤ “አገራችን በጦርነት እና አለመረጋጋት ወስጥ መሆኗ እየታወቀ "97% ያህል ተማሪዎች ወድቀዋል" ማለት፤ የትምህርት ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ከመንግሥት ጋር የተዋዋለው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ያመለክታል።” ሲል ገልጿል፡፡

“ተማሪዎች የአገራችን ተስፋዎች ናቸው።” ያለው ፓርቲው፤ እነዚህን የነገ አገር ተረካቢ ኃይሎች በኢትዮጵያ ተስፋ እንዳያደርጉ ከጅምሩ ማምከን ተገቢ አለመሆኑን አመላክቷል፡፡

እንዲሁም “ባለፋት አምስት ዓመታት "ለውጥ እናመጣለን" በሚል ሰበብ እንዲሁም በቂ ምክክር፣ ምርምር እና ግምገማ ያልተደረገበትን አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በፖለቲካዊ ውሳኔ በትውልዱ ላይ ለመጫን የተደረገው እርብርብ ትልቅ ኪሳራ አሳድሯል።” ብሏል፡፡

“ለትምህርት ሴክተሩ እየተሰጠ የሚገኘው ትኩረት አናሳ መሆን፣ ለተማሪዎች የመጻሕፍት አቅርቦት አለመኖር፣ ትክክለኛ የትምህርት ሰነዶችን የማጣራት ዘመቻው ደካማና የይምሰል መሆኑ፣ የተንሸዋረረ የጥያቄ አወጣጥ፣ የምዘና ሥርዓቱ ዝርክርክነት፣ የጥያቄዎቹ መልስ ይፋ አለመደረጉ፣ ዝቅተኛ የበጀት ድልድል ወዘተ… አሁንም በዋልፈሰስ መቀጠላቸው፤ ቀጣዩ ትውልድ በትምህርት መስክ ተስፋ እንዳያደርግ ምክንያት ይሆናሉ” ብሎ እንደሚያምንም ፓርቲው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ባለፋት ሰላሳ ኹለት ዓመታት መምህራን ክብር እንዲያጡ፣ በሙያቸው ከመኩራት ይልቅ እንዲሸማቀቁ፣ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን መልሰው በችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎች ላይ እንዳያተኩሩ የተፈጸመባቸው በደል ሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ፓርቲውን እንደሚያሳስበው አመላክቷል፡፡

ስለሆነም “የትምህርት ሚኒስቴር የአሰራር ሥርዓቱን ከወሬ በዘለለ በተግባር ከፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያላቅቅ” የጠየቀው ፓርቲው፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከሥር መሠረቱ ስትራቴጂካሊ መስራት ሲገባው በስሜት ከአናቱ ለማስተካከል የሄደበት እርቀት የተሳሳተ በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡

እንዲሁም፤ የተማሪዎች ኹለንተናዊ አቅም እንዲያድግ መንግሥት በዋናነት ደሞዝን ጨምሮ የመምህራን አኗኗርና ሕይወት እንዲቀየር አፋጣኝ ወሳኔ በመስጠት ለተግባራዊነቱ እንዲሰራ አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም፤ በ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወደቁ የተማሪዎች ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ (817 ሺሕ 832) በመሆኑ፤ እንዲሁም የምዘና ሂደቱን በግልጽ ጥያቄ ውስጥ የሚከት በመሆኑ የተስተዋሉ ችግሮች በአግባቡ ተቀርፈው ኹሉም ተማሪዎች በድጋሚ እንዲፈተኑ ፓርቲው ጠይቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ካስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 99.3 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ፡፡

በትምህርት ቤቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 144 ተማሪዎች መካከል 143ቱ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ማህበሩ አሳውቋል።

በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ነጥብ 637 መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ትምህርት ቤቱ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችን ለማፍራት እየሠራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ደጀኔ ኢቲቻ ለኦቢኤን ተናግረዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉት የሊች ጎጎ እና ሀይረንዜ ትምህርት ቤቶች

በሀገር አቀፍ ደረጃ አምስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ያስፈተኗቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ መቻላቸው ይታወቃል።

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የሚገኘው የሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲሁም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የሚገኘው ሀይረንዜ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በማሳለፍ ታሪክ ፅፈዋል።

የመምህራንና ተማሪዎች መልካም ግንኙነት እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለውጤቱ መገኘትወሳኝ እንደነበር የትምህርት ቤቶቹ አመራሮች ገልጸዋል።

ውጤቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የትምህርት ጥራት ጉድለት ማስተካከል እንደሚቻል ተስፋ የሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሊች ጎጎን ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት (590) ያመጣው ተማሪ መልካሙ ፍሊፖስ የመምህራንና ሰራተኞች አገዛ እንዳልተለየው ገልጿል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች አንዱ የሆነው የሀይረንዚው ተማሪ አብዱረህማን ሽኩር (624)፥ ትምህርቱን በንቃትና በትጋት ከመከታተሉ በላይ የመምህራን የወላጆቹ ድጋፍ ወሳኝ እንደነበር ጠቁሟል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት ከመስከረም 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን መስጠት ጀምራል፡፡

በመሆኑ አገልግሎቱን የምትፈልጉ በሙሉ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ስካን በማድረግና https://neta.gov.et በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በኦንላይን ቀጠሮ ካስያዙ ተገልጋዮች በስተቀር ሌሎች ተገልጋዮችን በአካል #የማያስተናግድ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳውቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot