STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
Study in Belgium 🇧🇪

Government of Belgium Scholarships 2023

Fully Funded Scholarships are offered for international students in Belgium Universities

Programs: Bachelor, Master & Training Courses

Visit: https://tinyurl.com/mrxtxxfn

All the expenses will be covered by Belgium Government

Deadline: 27 January 2023

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
The University of Twente Scholarship in the Netherlands 2023

No. of Scholarships: approximately 50 scholarships are available

Link: https://scholarshipscorner.website/university-of-twente-scholarship/

Scholarship Value:

€ 3,000 - € 22,000 for one year (approximately 50 scholarships available).

Deadlines: 1 February 2023 and 1 May 2023.

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ‼️
የአማርኛ ቋንቋ መሰጠት መጀመሩ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያ፣ ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው አማርኛ ቋንቋ ከማወቅ በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ህዝቡን እና የኢትዮጵያን ባህል ማየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ የአፍሪካ ቋንቋዎችን የመማር ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ከአማርኛ በተጨማሪ በአፍሪካ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለው የስዋሂሊ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ቅሬታና ስጋት

በተለያዩ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ ባለመቻላቸው ስጋት ላይ እንደሆኑ ለዶቸ ቬለ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ሳይጠሯቸው ወራት እየተቆጠረ መሆኑ ስጋት ላይ እንደጣላቸውና ከሚመለከተው አካልም እስካሁን ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ እንደሆነች የገለፀች ወጣት፣ "ከግቢው ከወጣን ሐምሌ ወር አንስቶ እስካሁን አልተመለስንም" ትላለች። "የትምህርት አሰጣጡ ስለተዛባ የመጀመሪያው ሴሚስተርን ተምረን ነው የወጣነው" ያለችው  ወጣቷ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ወደ ወላጆቿ ቤት እንደምትገኝና በኢንተርኔት አለመኖር ምክንያት እዚያም ብዙ ስለ ትምህርት መረጃ እንደማታገኝ ነው የገለፀችው፡፡

በምስራቅ አርሲ ነዋሪ የሆነውና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የዘንድሮ ተመራቂ ነው፡፡ "ሰኔ መጨረሻ ጨርሰን እንደወጣን አልተመለስንም"፤ "ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንደሚያደርግ በተስፋ ብንጠብቅም እስካሁን አልተጠራንም" ብሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ቢያንስ ለተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል መፍትሔ እንዲያመቻችላቸውም ጠይቋል፡፡

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመትና የዘንድሮ ተማራቂ የሆነችው ወጣትም "ትምህርት ያቆምነውና ከግቢ የወጣነው ሰኔ 24 ቀን ነበር። ሚድ ፈተና ተፈትነን ነበር።   ያኔ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ፈተና ነበር። እና ለእነሱ ልቀቁ ተብለን ነው የለቀቅነው" ትላለች። "ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ከወጣን በኋላ ነው ነገሮች የተባባሱት" የምትለው በአርሲ ዞን ነዋሪ የሆነችው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ተማሪ፤ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ጥሪ አለማድረጉ እንዳሳሰባት ለዶቸ ቬለ ገልጻለች፡፡

በተመሳሳይ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነ ወጣት፣ ከተቋሙ ከወጣ አራት ወር እንዳለፈው ይገልጻል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች እየተቋረጠ የሚገኘው ትምህርት በተደጋጋሚ እቤት እንዲቀመጥ እንዳደረገውና ይህም ትልቅ የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰበት እንደሆነ ለለዶቸ ቬለ ተናግሯል፡፡

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ደምቢ ዶሎ ከተማ በመማርያ ክፍል ውስጥ የክፍል ጓደኛቸውን በቡድን የደፈሩት ሁለት ተማሪዎች በእስራት ተቀጡ።

በደምቢ ዶሎ ከተማ የፋሲሎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሆኑት ሰቦና ዲሪብሳ እና ኤቢሳ አድማሱ የክፍል ጓደኛቸውን በቡድን በመድፈራቸው አምስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የፍርድ ሂደቱን የመሩት ዳኛ ምትኩ ወዳጆ “ተበዳይዋ ተማሪ ስትሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙትም የክፍል ጓደኞቿ ናቸው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህ ወንጀል የተፈጸመው ተበዳይዋ የውጤት ስህተት ለማስተካከል ሰኔ 9/2015 ዓ. ም. ትምህርት ቤት በሄደችበት ወቅት ነው።

“ውጤት ለማስተካከል ትምህርት ቤት በሄደችበት ወቅት ብዙ ተማሪ አለመኖሩን እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው እያጫወቱ ወደ ክፍል ውስጥ ካስገቧት በኋላ በር ዘግተው የመድፈር ወንጀል ፈጽመውባታል” ብለዋል ዳኛ ምትኩ ወዳጆ።

ሁለተኛ ተከሳሽ የክፍሉን በር ሲዘጋ የመጀመሪያ ተከሳሽ የመድፈር ወንጀል ፈጽሟል። ከአንደኛ ተከሳሽ በመቀጠልም ሁለተኛው ተከሳሽ በድጋሚ የወንጀል ድርጊቱን በ10ኛ ክፍል ተማሪዋ ላይ መፈጽሙን የሰዮ ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል።

“ወንጀሉ ሲፈጸም ልጅቷ የድረሱልኝ ጩኸት ስታሰማ ነበር። ነገር ግን በወቅቱ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ስለነበረ ድምጿን ማንም አልሰማም” በማለት ዳኛው ጨምረው ተናግረዋል።

ተበዳይዋ የወንጀል ድርጊቱ ከተፈጸመባት በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቷ ሄዳ መቆየቷን ዳኛው ይናገራሉ። “ከዛ በኋላ ግን ሕመም ሲሰማት የደረሰባትን ለርዕሰ መምህሩ ተናገረች” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚያም የደምቢዶሎ ከተማ ፖሊስ ምርመራ አካሂዶ ዐቃቤ ሕግ በሰዮ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረቱን ዳኛ ምትኩ ይናገራሉ።

ሁለቱ ተማሪዎች የተከሰሱበት አንቀጽ በ1996 በወጣው አገሪቱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/1 መሠረት ከአምስት እስከ 15 ዓመት እንደሚያስቀጣ ገልጸዋል። ተከሳሾች የወንጀል ማቅለያ ከግምት ገብቶላቸው ፍርድ ቤቱ ታኅሣሥ 25/2016 ዓ. ም. በዋለው ችሎት ሁለቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ከስድስት ወር በእስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ተናግረዋል።

“እነዚህ ወጣቶች ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈጽመው ስለማያውቁ እንደ ቅጣት ማቅለያ ተወሰዶላቸዋል። በዐቃቤ ሕግ በኩልም ቅጣት ማጠናከሪያ ተብሎ የቀረበ አስተያየት ስለሌለ ሌሎችን ያስተምራል የተባለ ቅጣት” መተላለፉን ዳኛው ተናግረዋል።

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot