STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Voice message
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 122 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ፡፡
ኮሌጁ በ8ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 122 ሐኪሞች አስመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በሥራ ዓለም የተለያዩ ፈተናዎች እንደሚያጋጥማቸው በማወቅ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ሚኒስትር ዲኤታ አስገንዝበዋል፡፡
ኮሌጁ ከዚህ በፊት 739 የሕክምና ሐኪሞችን አስመርቋል። #አሚኮ
ለተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

የመቅደላ አምባ ዩንቨርሲቲ ዋናው ግቢ በህውዓት ወራሪ ሀይሎች ጉዳት ደርሶበታል።#አሚኮ
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በመቅደላ አምባ ዩንቨርሲቲ ተገኝቶ እንደተመለከተው አሸባሪውና ወራሪው ሃይል የዩኒቨርስቲውን የመማር ማስተማሪያ ቁሳቁሶች፣ የጥናትና ምርምር መሳሪያዎች እንዲሁም የተማሪዎችን የመኝታ ክፍሎች ዝርፊያና ውድመት እንዳደረሰባቸው ዘግቧል።
ወራሪው ቡድን መቅደላ አምባ ዩኒቨርሰቲ በሚገኝበት #ቱሉአወሊያ ከተማ የሚገኙ ባንኮችንና ሌሎች የመንግሥት ተቋማትን አውድሟል ሲል #አሚኮ ዘግቧል።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ከስርቆት ነጻ የሆነ ፈተና ለመስጠት የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከየሚማሩበት ትምህርት ቤት ወጣ ብሎ በመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሰጠት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።
የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ ወልድያ ከተማና ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ በማለት ዩኒቨርሲቲው መልካም ዕድል ተመኝቷል።
#አሚኮ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን

#Update
በአማራ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡
በክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል። እስካሁን 2.5 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
የተማሪዎች ምዝገባ ከሌሎች ዓመታት አንጻር ሲታይ የተጓተተ መኾኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ጽ/ቤት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባው በተፈለገው ልክ መሔድ አለመቻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፉት ዓመታት የምዝገባ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው ዝቅተኛ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መኾኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ምዝገባው መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡
በዚህም የተማሪዎች ምዝገባ በተፈገው ልክ ባለመኾኑ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም መራዘሙን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች እንዲመዘገቡና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው መስከረም 14/2016 ዓ.ም እንዲጀመር ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ #አሚኮ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ከ11,500 በላይ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡
ፈተናቸውን ለማጠናቀቅ በድጋሚ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተማሪዎች በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
ተማሪዎቹ በሦስት ዞኖች እና በጎንደር ከተማ የመጡ መሆናቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅዓለም ጋሻው ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እንዲሁም የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር የትምህርት አይነቶች ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። #አሚኮ

በአማራ ክልል በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 497 ትምህርት ቤቶች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
በክልሉ በ2015 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 214,997 ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን 210,323 ተማሪዎች ወይም 97.8 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
በክልሉ 574 ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከነዚህም 497 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በ77 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ የማለፊያውን ነጥብ እንዳለመጣ ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት (600 እና በላይ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፤ 500 እና በላይ ለማኅበራዊ ሳይንስ) ማስመዝገባቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ #አሚኮ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በክልሉ በ2015 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 214,997 ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን 210,323 ተማሪዎች ወይም 97.8 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
በክልሉ 574 ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከነዚህም 497 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በ77 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ የማለፊያውን ነጥብ እንዳለመጣ ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት (600 እና በላይ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፤ 500 እና በላይ ለማኅበራዊ ሳይንስ) ማስመዝገባቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ #አሚኮ
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
“በጸጥታ ችግር ምክንያት 310 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ኾነዋል” የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ አሳሰበ።
በሰላም መደፍረስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የኾኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ በትኩረት መሥራታ እንደሚገባ የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ አሳሰበ።
ከመስከረም ጀምሮ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩ ይታወቃል። የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ታደሰ ሸዋፈራው በሰጡን መረጃ “በጸጥታ ችግር ምክንያት በዞኑ 310 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ኾነዋል” ብለዋል።
በአንደኛ ደረጃ ትምህር ቤት መማር የነበረባቸው 219 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው። በተመሳሳይ በሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች መማር የነበረባቸው 57 ሺህ ተማሪዎች የመማር እድል አላገኙም።
33 ሺህ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎችም ወደ ትምህት ቤት አልሄዱም። በአጠቃላይ በዘንድሮው የመማር ማስተማር ጅማሮ 500 ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ተግባር ውጪ ናቸው። አንድ ትምህርት ቤት ደግሞ የተማሪዎች ምዝገባ እንኳን አላደረገም።
የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ በርካታ ውስንነቶች መኖራቸው ይታወቃል። ከነዚህ ውስንነቶች መካከል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አናሳ መኾን፣ በሽፋንም ይሁን በጥራት የትምህርት መሠረተ ልማት በሚፈለገው ደረጃ አለመሟላት፣ የግብዓት እጥረት እንዲሁም በልዩ ልዩ መልኩ ሊገለጽ የሚችል የፍላጎት ማነስ ተጠቃሽ ናቸው።
በተጠቀሱት እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት በየትምህርት ክፍሎቹ የሚመዘገበው ውጤት አመርቂ አይደለም። ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ የማለፍ ምጣኔው አናሳ እየኾነ ስለመምጣቱም ከሰሞኑ ይፋ በተደረገው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መረዳት ይቻላል።
አሁን ላይ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ደግሞ ችግሩን ‘በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ’ አድርጎታል። ባለሙያዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው የትምህርት ዘርፉን መደገፍ አለመቻላቸውንም አቶ ታደሰ ነግረውናል።
“የሁሉም ነገር መሰረቱ ሰላም ነው” ያሉት ኀላፊው ሰላም የጠፋበት አካባቢ ከልማት እና ከእድገት የተነጠለ መኾኑ አይቀሬ ስለመኾኑ አስገንዝበዋል። ስለዚህ ከምንም ነገር ቅድሚያ ለሰላም መስራት ይገባል ነው ያሉት።
የሰላምን ዋጋ በውል በመገንዘብ ስለሰላም እንሥራ፤ ተሻጋሪ አስተሳሰብ ያላቸውን ሀገር ተረካቢ ልጆች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱም ሁላችንም ጥረት እናድርግ ሲሉ ኀላፊው ጥሪ አቅርበዋል።