" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።
ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ " የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #የተሳሳተ ነው " ብሏል።
ቢሮው የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።
የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት #ሀገር_አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።
መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ #የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር አስረግጦ ተናግሯል ፤ መላው የከተማው ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT