STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የቴክኒክ እና ሞያ መግቢያ ነጥብ ‼️


የ2012 የትምህርት ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ



የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪውን የሰው ሃይል ስብጥርን በጠበቀ መልኩ በሀገሪቱ ያለውን የገበያ ፍላጎት መሰረት በማድረግ በየዓመቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የቅበላ መስፈርት የሚያወጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህ ዓመት አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት ተጠናቆ ተግባራዊ እንዲሆን በርካታ የመሸጋገሪያ ተግባራት የሚከናወኑበት መሆኑን የገለፀው ኤጀንሲው ይህንን እና የገበያውን ፍላጎት አንዲሁም የሰው ኃይል አሰላለፍን ከግምጥ ውስጥ በማስገባት የ2012 የትምህርት ዘመን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የቅበላ መስፈርትን አውጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

በደረጃ 1 እና 2

10ኛ ክፍል ላጠናቀቁ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.57 እና ከዚያ በታች
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.43 እና ከዚያ በታች
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.43 እና ከዚያ በታች
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.29 እና ከዚያ በታች
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 1.14 እና ከዚያ በታች

በደረጃ 3 እና 4

የ10ኛ ክፍል ላጠናቀቁ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.71 እና ከዚያ በላይ
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.57 እና ከዚያ በላይ
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 1.57 እና ከዚያ በላይ
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 1.43 እና ከዚያ በላይ
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 1.29 እና ከዚያ በላይ

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 129 እና ከዚያ በታች
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 129 እና ከዚያ በታች
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 99 እና ከዚያ በታች

በደረጃ 5

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ

• ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ
• ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 130 እና ከዚያ በላይ
• ሴት ታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 130 እና ከዚያ በላይ
• ሴቶች ከታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች 125 እና ከዚያ በላይ
• ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 100 እና ከዚያ በላይ

በመቁረጫ ነጥቡ ላይ በደረጃ 5 ስር የተመለከተው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ለወሰዱ ተብሎ ቢቀመጥም 10ኛ ክፍል ተፈትነው 11ኛ ክፍል የሚያስገባ ነጥብ ያላቸው በተጠቀሰው ደረጃ ላይ መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል፡፡


#EBC


#share and join
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው ከ45 በላይ ግለሰቦች በለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው ከ45 በላይ ግለሰቦችን በለይቶ ማቆያ በማስገባት ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

ቫይረሱ ከተገኘበት ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉት 45 የሚሆኑ ግለሰቦች ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልጸዋል።

በዚህም እየተደረገ ባለው ክትትል እስካሁን ምንም አይነት ምልክት የታየበት ሰው እንዳልተገኘም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።

ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ከተስፋፋባቸው ሀገራት በሚመጡ ሰዎች ላይ ከመጀመሪያውኑ የሰውነት ሙቀትን መለካት እና ሌሎች የበሽታው ምልክቶች ልየታና የክትትል እንደሚደረግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

#Ebc

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
ሆቴሉን ለሆስፒታልነት አልሰጠም| ስለCR7 የተወራው የሐሰት ዜና ነው❗️

ክርስቲያኖ ሮናልዶ CR7 ሆቴሉን በCORONA ለተጠቁ ሰዎች መታከሚያ እንዲሆን ሰጠ ተብሎ የተወራው ወሬ የሐሰት መረጃ መሆኑ ተገለጸ።

አንድ የእስፔን ጋዜጣ በስህተት በድኅረ ገጹ ከለጠፈው በኋላ ወዲያው ያጠፋው ቢሆንም ወሬው ግን በመላው ዓለም በፍጥነት በመሰራጨቱ በቀላሉ ሊታመን ችሏል ይሁንና ግን የCR7 ሆቴል አሁንም በሆቴልነቱ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ CR7 የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ራሱን እና ቤተሰቡን ከበሽታው ለመከላከል ሲል የግሉን ደሴት ገዝቷል።

#SportDaily
#EBC

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ ተጠየቀ
********

በዩክሬን የገኙ ኢትዮጵያያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳሰበ።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው ክትትል እያደረገ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

በዚህም በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋግሮ ማስፈቀዱን አስታውቋል።

በመሆኑም በታቸለ ፍጥነት በዩኩሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት በተቻለ ፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ አሳስቧል።

#EBC

    ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ 475 ተማሪዎቹን አሥመረቀ
***

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒም ሕክምና ኮጅ በተለያየ ህክምና ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 475 ተማሪዎቹን አሥመርቋል።

በዛሬው እለት ከተመረቁት መካከል 140ው ሴቶች ናቸው።

ሆስፒታሉ የተመሠረተበት 75ኛ አመት ክብረ በአልም በዚሁ መታሰቡ ተገልጿል።

የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶ/ር ወንድምገኝ ገዛኸኝ የዘንድሮውን ምርቃት ከምስረታው ቀን ጋር መገናኘቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ምሩቃኑ ከእለቱ የክብር አንግዳ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እጅ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

#EBC

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
2015 ዓ.ም ስናስታውሰው

በኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር በማገባደድ ላይ የምንገኘው የ2015 ዓ.ም በበጎ፣ በሐዘንም ሆነ በደስታ እጅግ በርካታ ዜናዎች የተስተናገዱበት ዓመት ነበር። ከነዚህ ዜናዎች ጎላ ጎላ ብለው የወጡትን እናስታውሳችሁ፦

• መስከረም 17/2015 ዓ.ም
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ስርዓተ ቀብሩም መስከረም 19/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• መስከረም 24/2015 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው ከፈቱ።

• ጥቅምት 1/2015 ዓ.ም
አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ፓሪስ ውስጥ ተፈጸመ፡፡

• ጥቅምት 23/ 2015 ዓ.ም
ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እልባት የሰጠ ታሪካዊ ስምምነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ተፈረመ፡፡

• ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም
የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡ ስርአተ ቀብሩም ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ተፈፀመ፡፡

• ሕዳር 26/ 2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የቤት ሰራተኛ የሞት ቅጣት ተፈረደባት፡፡

• ሕዳር 27/2015 ዓ.ም
ቄስ በሊና ሠርካ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም ታኅሣሥ 3/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በጴጥሮስ ወጳውሎስ የፕሮቴስታንት እና ካቶሊክ መካነ መቃብር ተፈፀመ፡፡

• ታኅሣሥ 2/2015 ዓ.ም
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ስርአተ ቀብሩም ታኅሣሥ 3/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡

• ታኅሣሥ 19/2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ መቀሌ ዳግም መደበኛ በረራ ጀመረ፡፡

• ታኅሣሥ 24/2015 ዓ.ም
የክብር አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከ22 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች፡፡

• ጥር 19/2015 ዓ.ም
በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ890 ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 29 ሺህ 909 ብቻ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

• የካቲት 28/2015 ዓ.ም
አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም የካቲት 29/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• የካቲት 28/2015 ዓ.ም
ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ያህል ቅርሶች በእንግሊዝ መገኘታቸው ተገለጸ፡፡ ቅርሶቹ በፈረንጆቹ 1868 እንግሊዝ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በወታደሮች የተዘረፉ መሆናቸውም ተነገረ፡፡

• መጋቢት 12/2015 ዓ.ም
የአካባቢ ጉዳይ ተመራማሪው ዶክተር ተወልደ ብርሃን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም መጋቢት 13/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• መጋቢት 12/2015 ዓ.ም
በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ሕጻን ሶሊያና ዳንኤል በሱሉልታ ክፍለ ከተማ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

• መጋቢት 12/2015 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም መጋቢት 17/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• መጋቢት 13/2015 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓትን) ከሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ሰረዘ፡፡

• መጋቢት 14/2015 ዓ.ም
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

• መጋቢት 14/ 2015 ዓ.ም
የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡

• መጋቢት 21/ 2015 ዓ.ም
“የምፅአት ቀን በመቅረቡ ሞት እና መፈናቀል ይኖራል” በሚል ስጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን በስደት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

• መጋቢት 18 /2015 ዓ.ም
“የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ። ስርአተ ቀብራቸውም መጋቢት 22/2015 ዓ.ም በእየሩሳሌም (እስራኤል) ተፈጸመ፡፡

• ሚያዝያ 7/2015 ዓ.ም
“የክልል ልዩ ኃይል” የሚባል አደረጃጀት ማብቃቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

• ሚያዝያ 15/2015 ዓ.ም
ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ስርአተ ቀብሩም ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም
የአማራ ክልል ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ግርማ የሺጥላ ተገደሉ፡፡ ስርአተ ቀብራቸውም ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም በትውልድ ቦታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን መሃል ሜዳ ከተማ ተካሄደ፡፡

• ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም
ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ስርአተ ቀብሩም ግንቦት 6/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

• ግንቦት 4/2015 ዓ.ም
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ስርአተ ቀብሯም ግንቦት 7/2015 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈጸመ፡፡

• ሰኔ 19/2015 ዓ.ም
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የስራ መልቀቂያ አስገቡ፡፡

• ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብሯን አሳካች፡፡

• ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ (መቄዶኒያ) እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡

• ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡

• ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም
አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

• ነሐሴ 8/2015 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ፡፡

• ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ተቀላቅላለች።

• ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

• ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም
የፊልምና የቴሌቭዥን ድራማዎች ዳይሬክተር አሸብር ካብታሙ ከዚህ ዓም በሞት ተለየ፡፡ ስርአተ ቀብሩም ነሐሴ 22/2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ፡፡

#EBC

@NATIONALEXAMSRESULT
የአብርሆት ቤተመፅሀፍት ከዛሬ ጀምሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ
**
በቀን እስከ 15ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግደው ቤተመፅሀፍቱ፤ የ24 ሰዓት አገልግሎት በመጀመር የአንባቢያንን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰራ ነው የተገለፀው፡፡
የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እስከ ምሽቱ 6 ሰአት አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል::
ይሁንና በበርካታ ሰዎች ጥያቄ እና ፍላጎት መሰረት፤ ቤተ መፅሀፍቱ ከዛሬ ጀምሮ 24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ነው የቤተ መፅሀፍቱ ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ የገለፁት::
ከጊዜ ወደጊዜ የአንባቢያን ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ብሎም የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት፤ ቁጥር ሁለት አብርሆትን ለመገንባት ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል:
የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን አንባቢዎችን አስተናግዷል:: #EBC

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot