STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#የጤና_ተማሪዎች_ቅሬታ

እኛ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተመራቂ ተማሪዎች በዘንድሮ ዓመት ሰኔ 30/2015 አ/ም የኢንተርንሽፕ ፕራክቲስ (internship) ጨርሰን ነገር ግን የEXIT EXAM ለመፈተን ት/ሚኒስተር ባወጣዉ መስፈርት መሰረት በወቅቱ መሰፈርቱን ለማሟላት የሳምንታት ልዩነት በመኖሩ ለፈተናዉ መቀመጥ እንዳልተቻለ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አሳዉቆን ነበር::

ይሄም ሊሆን የቻለው የህክምና ተማሪዎቸ አንደ ሌላዉ ትምህርት ዘርፍ በየዩኒቨርሲዉ የሚጣናቀቅበት ሰአት ገደብ እኩል ስላልሆነ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን የ7 ዐመት ትምህርታችንን ካጠናቀቅን ወር ያለፈን ቢሆንም EXIT EXAM ለመፈተን ለ6ወር ያለምንም የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በየቤታችን ሄደን እንድንጠብቅ ዩኒቨርሲቲዉ አሳዉቆናል።

ስለሆነም ት/ሚኒስተር ባወጣዉ የፈተና ሰአት ልንቀመጥ አልቻልንም።

ካሁን በሁላ ቀጣዩ የEXIT EXAM ከ6ወር በኋላ መሆኑን ት/ሚኒስተር ያወጣዉ መመሪያ ስለሆነ ፤ እኛ 7አመት ሙሉ በትምህርት ቆየተን ብደጋሚ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ያለምንም ምክንየት እና ሥራ እንድንቀመጥ እየተገደድን ነው:: ስለሆነም ይሄን ጉዳይ ት/ሚኒስተር አይቶ፡ በዚ ሁለት ወራት በመጨረስ ላይ ያሉ የጤና ተማሪዎች በማማከል አዲስ የፈተና ሥርዓት እንዲያወጣልን እንጠይቃለን።

የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ የህክምና ተማሪዎች

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT