STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ሰበር ዜና #ሀገራዊ_ጉዳይ


መንግስት በአሸባሪው የሕወሐት ኃይል ላይ “ብርቱና የማያዳግም” እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጠ!

መንግስት “ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይል” ባለው አሸባሪው የሕወሐት ኃይል እና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ ብርቱና የማያዳግም እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጠ፡፡
የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች የማያዳግም ክንዳቸውን እንዲያሳርፉ አቅጣጫ አስቀምጧል።
መንግስት እስካሁን በተናጠል የተኩ አቁም ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡አል ዐይን

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
አሜሪካ ቀጥላ ደግሞ ቤተመንግስት ገብቼ ካልመራኋችሁ ትለን ይሆን?

#ሀገራዊ_ጉዳይ

አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት አልፋ ማስፈራራት ጀምራለች!

ከህግ እና ስርአት ውጪ በሀገራችን የውስጥ ጉዳዮች ላይ ያለአግባብ ሲሰሩ የነበሩ 7 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች በ72 ሰአታት ውስጥ የሀገራችንን መሬት ለቀው እንዲወጡ የኢፌዴሪ መንግስት በትናትናው ዕለት ማስታወቁ ይታወቃል።

በዚህም በአሜሪካ እና አጋሮቿ የሚዘዋወር ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው እየተባለ የሚተቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያን ድርጊት መቃወማቸውን ወዲያውኑ አሳውቀው ነበር፡፡

እነሆ ዛሬ ደግሞ ወገኝተኝነትን አሸባሪ ተብሎ ለተፈረጀው የሕወኃት ቡድን ስታሳይ የከረመችው አሜሪካ 7ቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ወደስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ካልተደረገ ፕሬዝዳንቷ ጆባይደን የፈረሙበትን እና ልጥለው ያሰብኩትን ማዕቀብ ከመጣል እና ሌሎች ከባድ ርምጃዎችን ከመውሰድ ወደኋላ አልልም የሚል ማስፈራሪያ በኤምባሲዋ ገጽ በኩል አስተላልፋለች።

CNNን ጨምሮ ሌሎችም የአሜሪካ ሚዲያዎች ግልጽ ወገንተኝነት የታየባቸውን እና ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጡ ዘገባዎችን ሲሰሩ የሰነበቱ ሲሆን አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው እንደቀጠሉ ነው።

@NATIONALEXAMSRESULT
#ቦረና
#ሀገራዊ_ጉዳይ


በቦረና ዞን በምትገኘው ተልተሌ ወረዳ ባጋጠመው ድርቅ ከብቶቻቸውን ያጡ ገበሬዎች በበሬ ፈንታ ራሳቸው ሞፈር እየጎተቱ እርሻ ለማረስ ተገደዋል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#ሀገራዊ_ጉዳይ
በብሔር አንፋጅ ስንላቸው በሃይማኖት መጡ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ የነበረው ጥቃት ባይቆምም አሁን ደግሞ ፊቱን በጎን ወደ እስልምናው አዙሯል።

የዛሬ ሳምንት መስጂዳችን አይፍረስ በማለት በአንዋር መስጂድ ድምጻቸው ያሰሙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ከመጠን ያለፈ ርምጃ በመውሰድ ክቡር የሰው ሕይወት እንዲያልፍ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ያ ጠባሳ ሳይሽር በባሰ መልኩ ዛሬም አንዋር መስጂድ እና በኒ መስጂድ ብዙዎች ለከባድ ጉዳት እየተዳረጉ ይገኛሉ።

ለተጎዱ ምህረትን ለሞቱ ረፍተ ነፍስን ላዘኑ መፅናናትን እንመኛለን።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT