STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ማሳሰቢያ

ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እንዲያስገቡ የከፍተኛ ትምህርት ሥነ-ሥርዓት መመሪያ አንቀፅ 12 እና በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎችን መረጃ እንዲልኩ ለሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማሳሰብ በቁጥር በደብዳቤ ቁጥር 11/7-1/594/15 እና በቀን 27/03/15 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ማሳሰባችን ይታወሳል፡፡ በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት ከላይ #በምስሉ ስማቸው የተገለጸው የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃውን የላኩ መሆኑን እየገለጽን ከባለስልጣኑ አገልግሎት የሚያገኙት እነዚህ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ መሆናቸውን እንገልጻለን፡፡


የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን የአገልግሎት ክፍያዎች በቴሌብር!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ተገልጋዮች የምዝገባ፣ የትምህርት፣ የፈተና፣ የዶክመንት አውተንቲኬሽን፣ የትምህርት ማስረጃ የአልሙኒ እና መሰል አገልግሎቶች በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et/ በመግባት ሂደቱን ተከትላችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ በምታገኙት የመክፈያ ቁጥር (Payment order number) በመጠቀም በቴሌብር ሱፐርአፕ ወይም *127# በመደወል የአገልግሎት ክፍያችሁን በቀላሉ በመፈጸም የምትችሉ ሲሆን የክፍያ ደረሰኝ ከቴሌብር ሱፐርአፕ ታገኛላችሁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለደህንነት ሲባል የከተማ አስተዳደሩ የቀበሌ መታወቂያ ከሌላችሁ ብሔራዊ ፈተና ላይ አትቀመጡም እየተባሉ መሆኑን ምንጮች ገለፁ። የቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት ደግሞ የቤት ካርታ ያለው ቤተሠብ ስለሚያስፈልግ በኪራይ ቤት የሚኖሩ ለልጆቻቸው መታወቂያ ማውጣት እና እንዲፈተኑ ማድረግ ሌላ ፈተና እንደሆነባቸው ይናገራሉ ። ወላጆች በበኩላቸው የትምህርት ቤት መታወቂያ በቂ ነው ይላሉ።
ይሄን ችግራችንን ከተማ አስተዳደሩ ከግምት ቢያስገባ እና ማስተካከያ ቢያደርግ ብለዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
For Grade 12 National Exam (ለማትሪክ) ESSLCE ዝግጅት 

       📌መለማመጃ (Model) ፈተናዎች
📌የማትሪክ ሶልሽኖች
📌Past Exam Solutions
       📌ማብራሪያና መልሶች💡
📌አጫጭር ኖቶች📝
       
ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዝግጅት መለማመጃ

    📌ፈተናዎች ከሙሉ ማብራሪያና መልሶች፣
    📌 መፅሃፍትና Lecture Notes
   📌 አጫጭር ኖቶች

JOIN በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ✅️

✅️ለውዳጅ ዘመድ ያጋሩ
Share to families and friends

👍 Telegram Channel👇👇👇

https://t.me/tutorialpointeth
https://t.me/tutorialpointeth
https://t.me/tutorialpointeth

👉SUBSCRIBE👇YouTube Channel for video tutorials

https://www.youtube.com/@Tutorialpointeth
ለኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

ከያዝነው ዓመት ጀምሮ መሰጠት የሚጀምረውን የመውጫ ፈተና በተሳካ እና በተቀላጠፈ መልኩ ለመስጠት እንዲያስችል ከዚህ በፊት ከተሰጠ በተጨማሪ በሰኔ ወር በዩኒቨርሲቲው በኮምፒውተር ሲስተም ታግዞ የሚሰጠጠውን የሞዴል ፈተና አስመልክቶ ስልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ነገ ማለትም አርብ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ጀምሮ በአስተዳደር ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ትልቁ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
MoE circular #exitexam dates.pdf
326 KB
Exit exam Dates 👇👇👇
🛎 Exit Exam from Hamle 3 - 8
🛎 Result - Hamle 9
🛎 Graduation - Hamle 11 - 16

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግል እና በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ዕጩ ምሩቃን እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የሕግ ትምህርት መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ይሰጣል፡፡

የመውጫ ፈተናው ውጤት ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም እንደሚገለጽ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል፡፡

ከፈተናው መጠናቀቅ በኋላ ተማሪዎች ከሐምሌ 08/2015 ዓ.ም ጀምሮ የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ኦንላይን ማየት ይችላሉ ተብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ማካሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የሚሳተፉ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ እንደሚሆኑ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
MoE circular #exitexam dates.pdf
#MoE

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።


በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሰበር ዜና‼️

የማካካሻ ፕሮግራም የምዘና አይነት በድጋሚ ወደ ነበረበት ተመልሷል። (30/70)

ከዚህ በፊት የማካካሻ ፕሮግራም የምዘና አያያዝ 50% በዩኒቨረሲቲ ደረጃ እና 50%
በማዕከል (ትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ) እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን ትምህርት ሚኒስቴር በቀን 23/09/2015 ዓ.ም በድጋሜ በላከው ደብዳቤ መሰረት የምዘና አያያዙ በዩኒቨረሲቲ ደረጃ 30% እና በማዕከል (በትምህርት ሚኒሰቴር) ደረጃ ከ70%
እንደሆነ አሳውቆናል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Debra Tabor University ‼️

የማካካሻ ፕሮግራም ተማሪዎችን በተመለከተ

ከዚህ በፊት የማካካሻ ፕሮግራም የምዘና አያያዝ 50% በዩኒቨረሲቲ ደረጃ እና 50%
በማዕከል (ትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ) እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን ትምህርት ሚኒስቴር በቀን 23/09/2015 ዓ.ም በድጋሜ በላከው ደብዳቤ መሰረት የምዘና አያያዙ በዩኒቨረሲቲ ደረጃ 30% እና በማዕከል (በትምህርት ሚኒሰቴር) ደረጃ ከ70% እንደሆነ አሳውቆናል፡፡

ስለዚህ በዩኒቨርስቲው ደረጃ የሚሰጠው 30%
🧧Mid Exam......5%
🧧 Final Exam.....10%
🧧Group Assignment....15%

የዩኒቨርስቲው Final Exam ከ ሰኔ 12-16 ይሰጣል ።

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው ፈተና ከ ሰኔ 26-30 ይሰጣል ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምረቃ መርሐግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመዉጫ ፈተናዉን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ ናቸዉ - የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፈተና አስተዳደር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ የፈተና ቀናትን ያሳወቀ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምረቃ መርሐ ግብር ቀናቸዉንም ወስኗል። በዚህም መሰረት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸዉን የምረቃ መርሐግብር ከ ሐምሌ 11 እስከ 16 ባሉት ቀናት ማከናወን እንዳለባቸዉ አሳስቧል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይም መሳተፍ የሚችሉት የመዉጫ ፈተናዉን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸዉን ጠቅሷል።

በሌለ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ  የ12ኛ ክፍል ሬሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎቻቸዉን ዉጤት እና ለመጀመሪያ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪነት መብቃታቸዉን እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲያሳዉቁኝ ማለቱን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የ 2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከ ሐምሌ 19 እስከ 30 መመዘኛዉን የሚወስዱ እንደመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅታቸዉን ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ለፈተናዉ ብቻ መሆን እንዳለበት ገልጿል።

በ 2015 አመት የመዉጫ ፈተና ለመዉሰድ የተመዘገቡ እጩ ምሩቃን እና ባለፉት አመታት የህግ ትምህርት የመዉጫ ፈተና ወስደዉ ማለፊያ ዉጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች ከ ሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንዲፈተኑ እና ሐምሌ 10 ቀንም ዉጤታቸዉ የሚታወቅበት መሆኑን ጨምሮ አሳዉቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ሀገራዊ_ጉዳይ
በብሔር አንፋጅ ስንላቸው በሃይማኖት መጡ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ የነበረው ጥቃት ባይቆምም አሁን ደግሞ ፊቱን በጎን ወደ እስልምናው አዙሯል።

የዛሬ ሳምንት መስጂዳችን አይፍረስ በማለት በአንዋር መስጂድ ድምጻቸው ያሰሙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ከመጠን ያለፈ ርምጃ በመውሰድ ክቡር የሰው ሕይወት እንዲያልፍ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ያ ጠባሳ ሳይሽር በባሰ መልኩ ዛሬም አንዋር መስጂድ እና በኒ መስጂድ ብዙዎች ለከባድ ጉዳት እየተዳረጉ ይገኛሉ።

ለተጎዱ ምህረትን ለሞቱ ረፍተ ነፍስን ላዘኑ መፅናናትን እንመኛለን።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT