STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#National_Exit_Exam

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች የሚከተሉት ይገኙበታል፦

• የመውጫ ፈተና ምዘናው የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።

• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡

• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፣ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።

• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማት እና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡

• ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#National_Exit_Exam

በመጪው ሐምሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት እያደረጉ ነው።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጿል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ240 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot