STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ትዝብት

ዩኒቨርሲቲዎቻችን የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን የመውጫ ፈተና ሞዴል ፈተናዎችን እየፈተኑ እንደሆነና ለመውጫ ፈተናው ልዩ ትኩረት በመስጠት ተማሪዎቻቸውን ዝግጁ እያደረጉ እንደሆነ ነው።

ይህ ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና ከመንግስት ኃላፊዎች በኩል የሚሰማው ዝግጅት መሬት አለ አለ? ከተማሪው በኩል ያለው እይታስ ምን ይመስላል?


@NATIONALEXAMSRESULT
ሀይሌ በቴሌቪዥን ቶክሾው እየመጣ ነው😍

ጀግናው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በናሽናል ሚዲያ ኮርፖሬሽን ( NBC Ethiopia ) "ሀይሌ እና ልጆች" የሚል ርዕስ ያለው አዲስ ቶክሾው በቅርቡ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

በሩጫው ፣ በኢንቨስትመንቱ ፣ በሀገር ሽምግልናው የተሰካለት ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ከማያልቀው ፀጋው ለነገዋ ኢትዮጵያ ለማጋራት ከህጻናት ጋር መጫወትን መርጧል። በፕሮግራሙ የሚታደሙ ህፃናትም እንደ ሀይሌ በይቻላል መንፈስ ለነጋቸው መሰረት ጥለው ይመለሳሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደብረታቦር ዩንቨርስቲ‼️
ደብረታቦር  ዩኒቨርሰቲ ሁለተኛውን የተሳካ የሮኬት ሙከራ አከናውኗል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ከሃያ ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ መጓዝ የሚችል ሮኬት አስወነጨፈ
******
(ኢ ፕ ድ)

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ "አፄ ቴዎድሮስ 2015" የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሮኬት ከሃያ ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ አስወንጭፎ ስኬታማ ሙከራ ማድረግ ችሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በህዋ ምርምር ላይ ትኩረት በማድረግ ጋፋት የህዋ ምህንድስና ልማት ማዕከልንም አቋቁሞ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

የማዕከሉ መሥራችና ሰብሳቢ አቶ በለጠ ጌታቸው፣ ሮኬት የማስወንጨፉ ሙከራ ከዚህ በፊት ከተሞከሩት የተሻለ ምርምር የተደረገበትና ለህዋ ሳይንስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ተሸክሞ መሄድ የሚያስችል ቴክኖሎጅ የተገጠመለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው በዩኒቨርሲቲው ተማሪና ተመራማሪዎች የተሠራው ሥራ ኢትዮጵያ እንደሰለጠኑት ሀገራት በህዋ ምርምር የበኩሏን ድርሻ እንደምትይዝ ጅምሩን ያሳየ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከሚካሄዱት የህዋ ሳይንስ ምርምሮች ውስጥ በሮኬት ሳይንስ ዘርፍ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአማራ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሉ አያሌው (ዶ.ር) እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ኢትዮጵያ ወደፊት በዘርፉ ለምታደርገው ምርምር አጋዥ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@NATIONALEXAMSRESULT
📌How to check DV result on May 6 .

1⃣. Go to link https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx.

2⃣. Press Continue.

3⃣. Type the confirmation number that was given when you applied. eg. 20241O0DZWY3DOV9

4⃣. Provide the Last/Family Name that was used on the Electronic Diversity Visa Entry.

5⃣. Provide the year of birth for the primary entrant.

6⃣. Authentication "Type the characters as they appear in the picture."

7⃣. Press Submit.👏

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
file.pdf
244.3 KB
👆👆DV ውጤቱ በቁጥሮች ሲዘረዘር ይህንን ይመስላል
                  
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ይህ ችግር ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አጥር ስር ነው።ተለዋጭ መንገድ ሳይሰራ ግንባታ በመጀመሩ በተለይ አካል ጉዳተኞች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ከስፍራው የደረሰኝ ጥቆማ ይገልፃል።ዩኒቨርስቲው ለችግሩ መፍትሄ ቢያስቀምጥ መልካም ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ ሁለት ህጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክ/ከተማ ከታ በተሰኘዉ አካባቢ እድሜያቸዉ የ 12 እና 4 አመት የሆኑ ወንድምና እህት በአሳዳጊያቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ብሥራት ሬዲዮ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳን ጠቅሶ ዘግቧል።

የ12 አመት ታዳጊ የሆነዉ ናኦል ጌቱ እና የ 4 አመቷ ህጻን የሆነችዉ ናኑ ጌቱ ከትናንት በስቲያ ሌሊት የቤት ሰራተኛ ሆና ወደ ቤታቸዉ በገባችና በኋላም ከሟቾቹ ህጻናት አባት ጋር የፍቅር ግንኙነት አላት በተባለችዉ "ነጋሴ ከበደ" ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

ግለሰቧ ህጻናቱን በማረድ ከገደለች በኋላ አስክሬናቸውን በእሳት ማቃጠሏ ተነግሯል። ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ፥ ግለሰቧ ራስዋን "ትግስት" ብላ የምትጠራ ሲሆን ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላ ከአካባቢዉ መሰወሯን ገልጸዋል።

"ነጋሴ ከበደ" አልያም ራሷን "ትግስት" የምትለዉ
ግለሰብ ፤ ከሟች ህጻናቶቹ አባት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸዉና ከሶስት ወራት በፊት ተጋጭተዉ ከቤት መዉጣቷን፤ በኋላም በእርሷ ቤተሰቦች አሸማጋይነት ሁለቱ ጥንዶች እርቅ አድርገዉ ወደ ቤት መመለሷን ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ተናግረዋል።

አባት በከተማዉ ባለ የቄራዎች ድርጅት ሰራተኛ ሲሆን በዕለቱም በሌሊት ወደ ሥራ አቅንቶ በሥራው ላይ ሳለ ግለሰቧ ቤቱ መቃጠሉን ለአባት በስልክ ማስታወቋን ዘገባው ይገልጻል።

ግለሰቧ ከአካባቢው ራሷን መሰወሯን እና ፖሊስም በፍለጋ ላይ መሆኑን በሸገር ከተማ የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽቱ ለኪሳ ጨምረዉ መናገራቸውን የብስራት ራዲዮ የጣቢያው ዘገባ ያመላክታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆንና አስተዳደራዊ ነፃነት

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆናቸው አስተዳደራዊ ነፃነት
እንዲኖራቸው ያደርጋል ሲሉ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ አደረጃጀታቸው የምርምር እና የመማር ማስተማር ሂደቱን በነፃነት እንዲያከናውኑ የሚረዳቸው እንደሚሆን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ራስ ገዝ ከሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ከአስተዳደራዊ ነፃነት በተጨማሪ የአካዳሚክ ነፃነት እንደሚሰጥ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ራስ ገዝ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካካል አንዱ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ካሪኩለምን ጨምሮ አስተዳደራዊ አደረጃጀት ላይ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ሃብት ማመንጨት ላይ ለመስራት የተቋማቱን ኢንተርፕራይዞች በተገቢው መልክ እያደራጁ መሆኑን ጠቁመዋል። #ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በተለያዩ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ለመማር የተመዘገባችሁ አመልካቾች ትምህርት የሚጀምረው ነገ ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ አሟልተው የላኩ 145 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

እስካሁን የተሟላ ዝርዝር ከላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ፣ አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

(የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን የተሟላ መረጃ የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) #ETA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#National_Exit_Exam

በመጪው ሐምሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት እያደረጉ ነው።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተቋሙ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጿል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ240 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ሊደረግ ነው።

በኢትዮጵያ በቂ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ባለመኖራቸው፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሊያስተምሩ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን መምህራንን ጭምር የሚያሠለጥኑ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተመድበው የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያስተምሩበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

"የእንግሊዝኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻቸው የሆኑ ሦስት ሺህ የሚሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በአገር ቤት ያሉ መምህራንንና ተማሪዎችን እንዲያስተምሩ በየትምህርት ቤቱ አንድ ለመመደብ አቅደናል" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ጥሪ መሠረት በውጭ አገር ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን ወደ አገር ቤት ልከው ትምህርት እንዲሰጡ ለማድረግ እንዲመዘገቡ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት በማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በነፃ የሚያገኝበት ማስተማሪያ ‹‹ፖርታል›› እንደተዘጋጀም ገልጸዋል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የትምህርት ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ድረ-ገጽን መሠረት ያደረገ ዲጂታል መተገበሪያ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፤ በአጠቃቀሙ ላይ በተግባር የተደገፈ ሥልጠና መሠጠቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ስልጠናው የተሰጠው ከመምህራን ኮሌጆች ለተውጣጡና ከመረጃ ጋር ተያያዥነት ላላቸው የትምህርት ባለሙያዎች መሆኑም ተነግሯል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓትና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ ሰብስብ ለማ ዲጂታል መተግበሪያው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ከተቋማቱ ጋር በበይነመረብ (በኦንላይን) የሚያገናኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም መረጃዎችን በየፈርጁ እንዲሁም በተቋም ደረጃ እና በአገር አቀፍ ደረጃ በፍጥነት ተንትኖ መረጃው ለሚፈለገው ዓላማ በግብዓትነት እንዲውል የሚያስችልና ለአጠቃቀም ቀላልና ቀልጣፋ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ከዚህ በፊት የነበረውን መረጃን በወቅቱና በጥራት ሰብስቦና ተንተኖ ለሚፈልገዉ ግብዓት እንዲውል ማቅረብ ያለመቻል ዉስንነቶችን በሚቀርፍ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የዲጂታል መተግበሪያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ ወደ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መረጃ ለሚልኩ ተቋማት በየጊዜው የተላከውን መረጃ ተንትኖ የሚያስቀመጥበት በቂ የማከማቻ ቦታ ያለው መሆኑም ተገልጿል።

በመረጃዎች ላይ ማስተካከያ ካለም ማስተካከያ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነና፤ የተደረገው ማስተካከያንም በቀጥታ በአገር አቀፍ ደረጃ ተንትኖ የሚያስቀምጥ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚዉ መግለጻቸውን አዲስ ማለዳ ከሚኒስቴሩ መሥሪያ ቤቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወሎ ዩኒቨርሲቲ አርሶ አደሮች ወቅታዊ የገበያ መረጃ የሚያገኙበትን የስልክ መተግበሪያ በማበልጸግ ተግባራዊ አደረ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ አርሶ አደሮች ወቅታዊ የገበያ መረጃ እንዲደርሳቸው የሚያደርግ የስልክ መተግበሪያ በማበልጸግ ተደራሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ መተግበሪያ፤ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በወቅቱ ገበያ ሸጠው መጠቀም እንዲችሉ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

አርሶ አደሩ በብዙ ልፋት ያመረተውን ምርት ቀጥታ ለገበያ ማቅረብ ሲገባው ደላሎች በሚፈጥሩት የገበያ ሰንሰለት ብልሽት ምክንያት ምርቱን በሚፈልገው ዋጋ መሸጥ አለመቻሉ ተጠቁሟል።

ችግሩን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው ከ2015 መግቢያ አንስቶ ለሙከራ በተመረጡ የደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ለሚገኙ አርሶ አደሮች የስልክ መተግበሪያ አበልጽጎ ወቅታዊ የገበያ መረጃ በእጅ ስልካቸው መልዕክት እንዲደርስ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

መተግበሪያው ለ1 ሺሕ 300 አርሶ አደሮች በሳምንት አራት ቀን ወቅታዊ የገበያ መረጃ እንዲደርሳቸው በማድረጉ ምርታቸውን በወቅቱ ገበያ ሸጠው መጠቀም መቻላቸው ተገልጿል።

ቀጣይ ተደራሽነቱን በማስፋት ለበርካታ የምስራቅ አማራ አርሶ አደሮች ወቅታዊ የገበያ መረጃ እንዲደርሳቸው ለማድረግ እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን፤ መተግበሪያ ለአርሶ አደሩ ከንግድ ተቋማት ዕለታዊ ዋጋ በመላክ በምርቱ ተደራድሮ እንዲሸጥ ማስቻሉም ተመላክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ከኢፕድ_ማህደር ‼️

48 ዓመታት ቀሚስ የለበሰው ወንድ ተከሰሰ

48 ዓመት ሙሉ እንደ ሴት ቀሚስ በመልበስ ሸዋዬ ደገፉ በመባል በሴት ስም ይጠራ የነበረ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ሸዋዬ ደገፉ የወንድ ጾታውን በመደበቅ ቀሚስ ለብሶ በሴት ስም በመጠራት ካሳለፈው 48 ዓመታት ውስጥ በናዝሬት 10 አመት፣ በአሰላ ከተማ አራት አመት፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ 11 አመት በታላላቅ ሰዎች ቤት በሴት ሥራ ሙያ እየተቀጠረ መኖሩን ገልጿል፡፡

ሸዋዬ የወንድነት ጾታው እንዳይታወቅበት በአገጩ ግራና ቀኝ በመጠኑ የሚበቅለውን ጢም በየዕለቱ ይላጫል፡፡ ጠጉረ በራ በመሆኑም ዘወትር እንደ ሴት ሻሽ ይጠመጥማል፡፡ የጆሮ ጉትቻም እንደማይለየው ታውቋል፡፡

ሸዋዬ በትውልድ አገሩ በየረርና ከርዩ አውራጃ በኢጀሬ ከህጻንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሴት ቀሚስ ይለብስ እንደነበር ጠቅሶ ወደ ፊትም እስከ ዕለቱ ሞቱ ድረስ ቀሚስ መልበሱን እንደማይተው አስረድቷል፡፡

ተከሳሹ የሴቶቹን ሙያ አጠናቆ የሚያውቅ መሆኑን ገልጾ ከህጻንነቱ ጀምሮ ዘፈን የሚወድ፤ በዚህም ሙያ ብዙ ጊዜ እንደተጠቀመበት አረጋግጧል፡፡

ሸዋዬ ደገፉ በናዝሬት፣ በአሰላና በአዲስ አበባ እየተዘዋወረ ለ25 ዓመታት ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ጊዜ የወንድነት ጾታው ያልታወቀበት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ሸዋዬ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኤጀሬ ሲጓዝ ለጥቂት ጊዜ በናዝሬት ከተማ በሴት ሥራ ሙያ ተቀጥሮ ገንዘብ ለማግኘት ባለው ዕቅድ መሰረት በከተማው ውስጥ ሲዘዋወር ፖሊሶች በጥርጣሬ ያዙት፡፡ ከዚያም ሲጠየቅ ወንድ መሆኑንና በዚሁ በሴት ሁኔታ 48 አመታት ሙሉ መኖሩን አስረድቷል፡፡

በዚህም ጾታ የመለወጥና ቀሚስ የመልበስ አድራጎቱ ተከሶ አዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ሆኖም በዚሁ ሁኔታ ለመኖር የፈለገበት ምክንያት በሚገባ እስኪጣራ ድረስ በዋስ መለቀቁ ታውቋል፡፡

የካቲት 6 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ