STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Exit የወደቁ ተማሪዎችን Graduation Ceremony ላይ እናሳትፋለን።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከምረቃ ስነስርዓቱ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚንስቴር < የመውጫ ፈተና #ያላለፉ ተማሪዎች ዲግሪ አይሰጣቸው > የሚለውን አቋም ተቀብለው የምረቃ በዓሉ ላይ ግን ምርጫውን ማለትም የወደቁ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ መካፈል አለመካፈላቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ለተቋማቱ #እንደተወ ገልፀዋል።

በመሆኑም እርሳቸው የሚመሩት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበር የመውጫ ፈተና #ያላለፉትንም ጭምር Graduation Ceremony ላይ እንደሚያካትት ገልፀዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል።

አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል።

የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል።

ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል።

የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ላይ እንደሆነም ህብረቱ ጠቁሟል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ExitExam

ሁለተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ( Exit Exam ) ጥር ወር ላይ ይሰጣል‼️

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በዛሬው ዕለት #ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ተቋማት የመደበኛ ተማሪዎቻቸውን እንዲሁም 2015 ላይ የመውጫ ፈተና ወስደው #ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ እስከ ጥቅምት 10/2016 ድረስ ይልኩ ዘንድ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ቀጣዩ ማለትም ሁለተኛው የመውጫ ፈተና ጥር ወር ላይ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

፨ የመውጫ ፈተና በየ ስድስት ወሩ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር መግለፁ ይታወሳል።


( ከላይ የተያያዘውን ደብዳቤ ይመልከቱ ‼️ )

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot