STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ👇

ወሎ ዩኒቨርሲት ተማሪዎቹን ከ #የካቲት 30 ጀምሮ በሁለት ዙር እንደሚያስገባ አሳስቦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛም(ህብረቱ) ተማሪዎች የሚገቡበት ቀን እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ የመግቢያ ቀንን በማስታወቂያ ሊገለፅ ይገባል በማለት ለዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ለሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

የማኔጅመንት አካላት ተማሪዎችን በማስታወቂያ እንደሚገልፁ የነገሩን ቢሆንም #የካቲት21 ቀን በነበራቸው ስብሰባ እንደ ዩኒቨርሲቲ በቴሌቬዥን እንደሚያስነግሩና ከተባለው ቀን #አንድ_ሳምንት በመጨመር(👉መጋቢት 07 አካባቢ) እንደሚያስገቡ ገልፀውልናል‼️

፨ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?

ተማሪዎች ባልተዘጋጀ ዶርምና ካፌ መተው እንዳይንገላቱብን አስቀድመን መጨረስ ያለብንን ነገር መጨረስና ማረጋገጥ ስላለብን እንዲሁም መብራት በማይኖርበት ጊዜ ተማሪዎችን በዳቦ አቅርቦትና በጥናት ጊዜ እንዳይጉላሉ ጀነሬተሮች በህውሓት ሃይሎች ስለተበላሹ ይሄንንም ለማሰራት ጊዜ ስለሚፈልግ ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ህብረቱ ገልጿል።

፨ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ እንደገለፃችሁት በሁለት ዙር ወይስ አንድ ላይ ትጠራላቹህ ብለን የጠየቅን ሲሆን ፡ የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር እንደ ተማሪዎች አገልግሎት በቂ የመኝታ በሮች ስለተገጠሙልኝ በተጨማሪም የምግብ ቤት ግብዓቶች ስለተሟሉ በአንድ ላይ ቢገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይቻላል ያለ ሲሆን የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚጠሩ ገልፀው በቅድሚያ አንደኛ ዓመት እና ሁለተኛ ዓመት የነበሩትን ጠርቶ አንድ ሳምንት ባልሞላ ልዩነት ቀሪዎችን የሚጠራ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

📌የደሴ ካምፓስ ዳይሬክተሮችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም እንደ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ላይ ስለሚጠራ ልዩነት እንደማይኖረው አረጋግጠናል፡፡

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ #መጋቢት15 ባሉት ቀናት ሁሉንም ተማሪዎች የሚያስገባ ስለሆነ ተማሪዎች ማስታወቂያ እንድትከታተሉ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ArbaMinchUniversity

የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2014 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን #የካቲት_29/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን #የካቲት_30 እና #መጋቢት_01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

* የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆነ አራት ጉርድ ፎቶ፣
* አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ እንዲሁም
* ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል

የምደባ ቦታ
👉 ዓባያ ካምፓስ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ (ዓባያ ግቢ)፣

👉 ጫሞ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣

👉ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እና የአቅም ማሻሻያ ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
   
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot