STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም ነባር #የክረምት እና #የእረፍት ቀናት መርሃ ግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15 እስከ 18/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተመሳሳይ ፈተና ያለፉ አዲስ ገቢ #የሁለተኛ ዲግሪ #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ 18/2014 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል የተባለ ሲሆን ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ በ'PGDT' የትምህርት ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ምዝገባ ከሐምሌ 14 እስከ 19/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በደህንነት ካሜራ በመታገዝ እየሰጠ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል፡፡

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MattuUniversity

በ2015 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ #ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 30/2015 ዓ.ም እና መጋቢት 01/2015 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

➧ ስማችሁ ከ”A-B” የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በበደሌ ካምፓስ፤
➧ ስማችሁ ከ“A-B” የሚጀምር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በበደሌ ካምፓስ፣
➧ ቀሪዎቻችሁ በዋናዉ ጊቢ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot