STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች #Exit_Exam ዘንድሮ መጀመሩን ተቃውመዋል።

አንድ ሴሚስተር በ45 ቀን እየተማርን የመውጫ ፈተና ውሰዱ መባሉ አግባብ አይደለምም ብለዋል።



ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የጅግጅጋ ዬንቨርሲቲ ተማሪዎች የጋራ ጸሎት አታደርሱም ተብለው በልዩ ኃይሎች ሲመለሱ መንግስት ኦርቶዶክስ ላይ በደሉን ቀጥሏል

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
@NATIONALEXAMSRESULT በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ!

ሰሞኑን የተከሰተው ችግር ግን ትልቅ ሀገራዊ ችግር ነው ሀገር ችግር ውስጥ ሆና ደሞ ዝምታን መምረጥ ተገቢ አይደለም እኛ ያለ ኦርቶዶክስ,ሙስሊም,ካቶሊክ,ፕሮቴስታንት ተከታዮች ባዶ ነን ፈጣሪ መልካም ነገር ለሀገራችን ያምጣልን

🕊ሰላም ለኢትዮጵያውያን በሙሉ🕊

Team: @NATIONALEXAMSRESULT
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ልኽቀቱ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከወራት በኋላ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባወጣው መልዕክት፤ የተቋሙን ልኽቀት ለመመለስ የሁሉንም የትብብር ድጋፍ ጠይቋል፡፡

ባለፉት ሁለት አስቸጋሪ ዓመታት በሀሳብ እና ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብረው ለነበሩ ዓለም አቀፍ አጋሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከEBS ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ የመንግስትን ሦሥት ውሳኔዎች አብራርተዋል።

1. 50 በመቶ ባያመጡም መቶ ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ ሴሚስተር የማብቂያ ትምህርት ተከታትለው በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

2. በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት እንዲገቡ ይደረጋል።

3. በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በድጋሜ በግል መውሰድ ይችላሉ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስተዳደር "ተማሪዎቻችን እና ትምህርት ቤቶቻችን ምን እንደሚመስሉ" በደንብ ያሳየ እንደነበር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

"ውጤቱ ያስደነግጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ያለን የሥራ ኃላፊዎች ውጤቱን ለመቀበል ቀናት ወስዶብናል" ሲሉም ተደምጠዋል።

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በመንግስት በሚወሰን ነጥብ "ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ" ሆነው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡበት ዕድል እንዳለ መገለጹ ይታወቃል።


ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ሕዝቅኤል ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

በዚህም የሚኒስቴሩ የባለሙያዎች እና የአመራሮች ቡድን በተናጠል በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የደረሰውን የጉዳት ዳሰሳ ጥናት ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡

የአመራሮች ቡድኑ ከመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ሥራ በፍጥነት ማስጀመር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከሩን ጠቁመዋል፡፡

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከEBS ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ የመንግስትን ሦሥት ውሳኔዎች አብራርተዋል። 1. 50 በመቶ ባያመጡም መቶ ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ ሴሚስተር የማብቂያ ትምህርት ተከታትለው በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያ…
የ 100,000 ተማሪዎች  ማለፊያ ከግማሽ በታች ቢሆንም በጣም እንደማይወርድ ፍንጭ ተሰቷል የፈተናዎች  አገልግሎት  ጸሀፊ ከተማሪዎች  ቁጥር አንጻር እና የመስክ ልይታ አንጻር ማለፊያውን እንናገራለን  ነገር ግን በጣም ውጤት የወረደባቸው  ልጆች  ዘንድሮ  ዳግም  ሚፈተኑበትን እድል ስላላቸው  ይህን መጠበቅ  ቀርቶባቸው ለፈተና ቢዘጋጁ ብለዋል።

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የመውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሰሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርስቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሳሙኤል በአሁኑ ወቅትም የፈተና ንድፈ ማሳያና / Blueprint / የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡፡(MoE)

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ ዩኒቨርሲቲያችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ የተሰጠው ዩኒቨርሲቲያችን የትምህርት ጥራት ማዕከላት ለማድረግ (“We are dedicated to innovative knowledge”) በሚል መርህ ቃል በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በ2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲተያችን ገብተው በአፕላድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና የመግቢያ ፈተና ውጤት በማምጣት ያለፉትን መቀበል ይፈልጋል ፡፡

✏️ልዩነታችን
• ለተማሪዎቻችን ለቀጣይ የትምህርት ስኮላርሽፕ መስጠት
• ተማሪዎች የራሳቸው ካሪኩለም (Curriculum ) እንዲቀርፁ ማስቻሉ
• Dual-major/minor degree ማግኘታቸው
• Fast track ተጠቃሚ መሆናቸው
• ያሉን ፕሮግራሞች በሙሉ አለማአቀፍ እውቅና ያላቸው ካሪኩለም Accreditation መሆኑን እየገለፅን ፡-

💢በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች

1) School of Applied Natural Sciences (SoANS)
• Applied Biology
• Applied Chemistry
• Applied Mathematics
• Applied Physics
• Applied Geology
• Industrial Chemistry
• Pharmacy

2) School of Civil Engineering & Architecture (SoCEA)
• Architecture
• Civil Engineering
• Water Resources Engineering

3) School of Electrical Engineering & Computing (SoEEC)
• Computer Science & Engineering
• Electronics & Communication Engineering
• Electrical Power & Control Engineering
• Software Engineering

4) School of Mechanical, Chemical & Materials Science & Engineering (SoMCME)
• Chemical Engineering
• Materials Science & Engineering
• Mechanical Engineering
ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲ መረጃ በዩኒቨርሲቲው ድህረ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
http://www.astu.edu.et/ Facebook-


ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ካምፓሶች ላይ የእርምት እርምጃ ወስዷል፡፡

ባለሥልጣኑ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ የፍተሻ ጉብኝት የስነ ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ ሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ግሬት ኮሌጅ መገናኛ፣ ቦሌ ሚካኤል እና ቡልቡላ ካምፓሶች እንዲሁም ሮያል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሰሜን ካምፓስ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ወስዷል፡፡

ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ መዝግቦ ማስተማር፣ ፈቃድ ሳያገኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር፣ ከባለስልጣኑ ባልተሰጠው ፈቃድ ትምህርት መስጠት፤ ተቋማቱ ከፈጸሟቸው ጥሰቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

ተቋማቱ ጥሰት በፈጸሙባቸው የትምህርት መስኮች ያሉ ተማሪዎችን እንዲያሰናብቱ እንዲሁም በመስኮቹ ለተከታታይ ከሁለት እስከ ሦሥት ዓመታት ፈቃድ እንዳይጠይቁ እግድ ተጥሎባቸዋል፡፡

በተፈፀመው የህግ ጥሰት ግኝት የተቋሙ ባለሀብቶች እና የበላይ አመራሮች በፍትሐ ብሄር እና በወንጀል ህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ካለ በሚመለከታቸው የፍትህ አላካት ተጠያቂ የሚያደረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#አማራ

የክልሉ ትምህርት ቢሮ እየተተገበረ ላለው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን መጻሕፍት ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡

አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ ለማድረስ ከ31 ሚሊየን 668 ሺህ 812 በላይ መጻሕፍት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን መጻሕፍቱን በአንድ ጊዜ ለማሳተም ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ ቢያንስ አንድ መፅሐፍ ለሦስት ተማሪዎች እንዲሆን እና በዙር እንዲታተም እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡

ከ5 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት በውጭ ሀገር የታተሙ ቢኖሩም በውጭ ምንዛሬ እጥረት መረከብ እንዳልተቻለም ተነግሯል፡፡

በውጭ ሀገር ከታተሙት 8 ሚሊየን 888 ሺህ 169 መጻሕፍት ውስጥ እስካሁን 1 ሚሊየን 425 ሺህ 502 መጻሕፍት መሰራጨታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የታተሙ 944 ሺህ 882 መጻሕፍት መሠራጨታቸውን ነው የተነገረው።

#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል 7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ አዳዲስ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለተማሪዎች እየተሰራጩ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
በኦሮሚያ ክልል ለተዘጋጀው የቅድመ መደበኛ እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዲስ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት በፍጥነት አሳትሞ ለተማሪዎች ለማሰራጨት በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል።
 
በዚህ መሰረት የመምህራን መምሪያ መጽሐፍትን በቅድሚያ በማሳተም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ መደረጉም ተነግሯል።
 
አሁን ላይም ከ7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሐፍት መታተማቸው የተገለጸ ሲሆን ከታተሙት መጽሐፍት ውስጥም 5 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች መሰራጨታቸውን ተገልጿል።

ምንጭ፦ FBC

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot