STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ማስታወቂያ በ2015 ዓም የትምህርት ዘመን ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች
*******
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃግብር በስሩ ባሉት ሰባት (7) ካምፓሶቹ በጠቅላላው ዘጠና አምስት (95) የትምህርት መስኮች ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል:: የትምህርት መስኮቹ ዝርዝር ከሚሰጡበት ኮሌጅ እና ካምፓስ ጭምር ከዚህ በታች ታገኙታላችሁ:: ሙሉውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ለማግኘት በዌብሳይታችን ገፅ ላይ ይመልከቱ::
https://www.hu.edu.et
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Tigray

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል።

በጦርነት ምክንያት በክልሉ ያሉት ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኃላም ተማሪዎችን በፍጥነት ወደ ቀደመው የትምህርት ህይወታቸው እንዲመለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ዘግይቷል።

ከሰሞኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት እስኪጀመር #በሬድዮ እና #ቴሌቪዥን ትምህርት እንዲጀመር ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ስለማሳወቁ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅድሚያ ትንንሽ ህፃናት ላይ ትኩረት እንዳደረገ የገለፀው ቢሮው ይህም በአቅም ውስንነት እና በጀት ስለሌለው መሆኑን አመልክቷል። በሚዲያ ትምህርቱን ከመዋለህፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጿል።

የሬድዮ ትምህርት በድምፂ ወያነ፣ የቴሌቪዥን ትምህርት በትግራይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል ተብሏል።

ትምህርቱ ፤ የትግራይ ህፃናት በጦርነት ከደረሰባቸው ጫና እንዲወጡ ለማድረግና ለመደበኛው ትምህርት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ እንጂ ከክፍል ወደ ክፍል የሚያሻግራቸው እንዳልሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሬድዮ እና ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ትምህርት በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ ፤ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በሬድዮ የሚሰጠው ትምህርት ትግርኛ ፣ እንግሊዘኛ እና አካባቢ ሳይንስ ሲሆን በቴሌቪዥን ሒሳብን እንደሚያካትት አሳውቋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትምህርት ሚኒስቴር  ደረጃቸውን የጠበቁ  ትምህርት  ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን  ሚነስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
---------------------------------------------
ጥር 25/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር ) ሚኒስትሩ በጦርነት የወደሙና በልዪ ሁኔታ  የሚገነቡ 71  ትምህርት ቤቶችን ስራ  በይፋ አስጀምረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ   በ71 ትምህርት ቤቶች ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር  ላይ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ትምህርት ቤቶች በተሻለ ዲዛይን የሚጠበቅባቸውን መሠረተ ልማት አሟልተው ይገነባሉ።

ምቹና  የተሻሉ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለትምህርት ጥራት  ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ   ትምህርት ቤቶቹ በዚህ ዓመት ተገንብተው እስከ መጪው መስከረም  ወር ድረስ ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተናግረዋል።

ከ71 ትምህርት ቤቶች መካከል 50ዎቹ በዓለም ባንክ ድጋፍና ትብብር 16ቱ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት እንዲሁም 5ቱ በዲያስፖራ ትረስት ፈንድ እንደሚገነቡ አመልክተዋል።

በመሆኑም የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የትምህርት ቤቶቹ  ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ገንዘብና የጥራት ደረጃ ተገንብተው ለአገልግሎት እንዲበቁ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት  መሻሻል  መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዩሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ መንገድ ለመገንባት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወሻ

የዩኒቨርስቲ ምደባ በቅርቡ ይደረጋል።

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ያመጡ 29,909 ተማሪዎች በ 2015 አንደኛ አመትን ተምረው እንዲጨርሱ ሲባል በቅርቡ ምደባ ተደርጎ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረጋል።

የ 100 ሺ ምልመላ ከሰኞ ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል። ከዚሁ ጋር አያይዘውም የማካካሻ ትምህርቱ እንዴት እንደሚሰጥ ማብራሪያ ይደረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ጥቁር ልብስ የለበሱ ተማሪዎችን ወደ ግቢ እንዳይገቡ ከለከለ!

ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ በትናንትናው ዕለት ቤተ ክርስቲያን ውለው የመጡ  ጥቁር ልብስ የለበሱ ተማሪዎችን ወደ ግቢው እንዳይገቡ መከልከሉ ተገለጸ።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለጻ ዩኒቨርሲቲው ታስቦበት ሳይሆን በድንገት ጥቁር ልብስ የለበሱ ተማሪዎችን እንዳይገቡ ከከለከለ በኋላ ከዚህ በኋላ ከለበሳችሁ አትገቡም በማለት ማስጠንቀቂያ በመስጠት እንዳስገባቸው ተገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መላው ሕዝበ ክርስቲያንን የጾመ ነነዌን ሦስት ቀናት ጥቁር ልብስ በመልበስ እንዲያሳልፉ አዋጅ ማወጁ አይዘነጋም።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2014 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈታና ወስዳችሁ የዩኒርቨሲቲ መግቢያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ምርጫችሁ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንድታደርጉ ያሉን ፕሮግራሞች እና ስለዩኒቨርሲቲያችን አጭር መግለጫ ከላይ ያንቡ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#InjibaraUniversity

በ2015 ዓ.ም ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ጽዱ፣ ውብ፣ በትምህርት ጥራት ተመራጭ፣ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ አድርጋችሁ እንድትመርጡ በአክብሮት እንጋብዛለን!

ስለ እንጅባራ በጥቂቱ፡-
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ መርኃ ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ   450 ኪ.ሜ ከአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ደግሞ 112 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አካባቢው ነፋሻማና ለጤና ምቹ በመሆኑ ብዙዎቹ ለኑሮ የሚመርጡትም ነው እንጅባራ፡፡

ከግንባታ ሥራዎች ጎን ለጎን አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን የጀመረው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ምቹ፣  ጽዱና ለዐይን ማራኪ ገጽታን ተላብሷል፡፡ በዚህም ከተማሪዎች እና ከተለያዩ አካላት ምስጋና እና እውቅና አግኝቷል፡፡  

በ2014 ዓ.ም በተደረገው የተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ምርጫም በሀገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከምርጥ አሥር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆኗል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመደበኛና በተከታታይ ሞዳሊቲዎች 15,000 ተማሪዎችን በሰባት ኮሌጆችና አንድ ትምህርት ቤት ሥር በተደራጁ 58 ትምህርት ክፍሎች በማስተማር የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ጥራትን አንድ ወሳኝ የትኩረት መስክ አድርጎ ለይቷል፡፡

የትምህርት ጥራትን በአግባቡ ለመከወን ከ95 በላይ ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ አካዳሚክ ማዕረግ  እንዲሁም ከ500 በላይ የሌክቸረር ማዕረግ ያላቸውን መምህራን  በመያዝ እና መሰረታዊ የቤተ ሙከራ ግብዓቶችን በማሟላት ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት እየሠራም ይገኛል፡፡

ውድ ተማሪዎች ለውሳኔ እንዲረዳችሁ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡትን ፕሮግራሞች ከዚህ በታች ማየት ትችላላችሁ፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ አድርጉ፡፡

በፎቶ ከተገለጹት በተጨማሪ ፕሮግራሞችን ከታች በተገለጹትን ሊንኮች  መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

https://www.inu.edu.et/postgraduate-programs
https://www.inu.edu.et/undergraduate-programs

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የ6 ወራት የስራ አፈፃፃም የህብረቱ ስራ-አስፈፃሚዎች እና የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በተገኙበት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተገምግሟል።

በመርሀ-ግብሩ ከተገኙ አመራሮች መካከል መልዕክት ያስተላለፉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ተወካይና የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጣፊ፤ የሀገረ አቀፍ ህብረቱ ስራ-አስፈፃሚዎችን ወደ ታሪካዊቷና ለምለም ወደ ሆነችው ባሌ ዞን እንዲሁም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በሰላም እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ለዚህ መድረክ ዩኒቨርሲቲያችንን መርጣችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

ኃላፊው አያይዘውም የተማሪዎች ህብረት ለሰላማዊ መማር ማስተማር እያደረጉት ያለዉ አስተዋፅኦ አይተኬ መሆኑን ገልፀው ከዚህ በተሻለ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ምክር ለግሰዋል ።

ተማሪ ሚካኤል ያቦነሽ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባለፈው ግማሽ ዓመት የመማር ማስተማሩ ሂደት በተነፃፃሪ የተሻለና ሰላማዊ ሆኖ መገባደድ እንዲችል የተማሪ ህብረቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ ውጤት መገኘት እንዲችል የተማሪ ህብረት በየደረጃው ከሚገኙ የተቋማቱ አመራሮች፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ሲያደርጉ የነበረውን ርብርብ በቀጣይ 6 ወራትም አጠናክረው በመቀጠል የተሻለ አፈፃፀም ማምጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ከግምገማው መድረክ በተጨማሪ የሀገር አቀፍ ህብረቱ ከወደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከተማሪዎች እንዲሁም ከተማሪ ተወካዮች ጋር የተለያዩ ውይይቶች ብሎም ስልጠናዎች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
©EHEISU

@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
# ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ)  ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን  በቀጣዩ ሊንክ 

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

                        
ትምህርት ሚኒስቴር!

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው የድንገተኛ ጉብኝት ፍተሻ የስነ-ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ #ሐራምቤ ዩንቨርስቲ (ሲኤምሲ ካምፓስ)፤ #ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ (አራት ኪሎ ካምፓስ) እና #ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ (አዲስ አበባ ካምፓስ) ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን ይፋ አደረጓል፡፡

ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት

፨ሐራምቤ ዩንቨርሲቲ በሲኤምሲ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በዲግሪ መርሀ ግብር በቢዝነስ ማኔጅመንት የትምህርት መስክ ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ፤ ፈቃድ ባላገኘባቸው ማስተርስ ኢን ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ማስተርስ ኢን አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ የትምህርት መስኮች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር አድርጎ ማስታወቁ እና የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማሩ በመረጋገጡ...

፨ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአራት ኪሎ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር በማስተርስ ኦፍ ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ በመረጋገጡ...

፨ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ካምፓሱ ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ በማስተርስ ኦፍ በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን እና ግሎባል ስተዲስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን እያስተማረ መሆኑ በባለሥልጣኑ በመረጋገጡ...

⭕️በሶስቱ ተቋማት ላይ የተላለፈውን የማስተካከያ እርምጃ ከምስሉ ያንብቡ።



ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot