STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.2K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።

በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።

#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል፦

ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#MizanTepiUniversity

ለሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ነባር መደበኛ እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው 👉 ጥር 13-14 መሆኑን እየገለፅን በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡


ማሳሰቢያ፡ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለተመደባችሁ ተማሪዎች
1ኛ. ከነበራችሁበት ዩኒቨርሲቲ የተሰጣችሁን መታወቂያ ካርድ
2ኛ. ግሬድ ሪፖርት
3ኛ. አንሶላ፣ ብርድልብስ እና የትራስ ጨርቅ በመያዝ የግብርና፣ የማህበራዊ ሳይንስ፤ የህግ እና የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የትምህርት መስኮች ተማሪዎች ሚዛን ከተማ በሚገኘው ሚዛን ካምፓስ፤ ከላይ ባልተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ካምፓስ በአካል እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ነባር መደበኛ ተማሪዎች እና ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ
ከጥር 13 እስከ 14/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎች የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እና ግሬድ ሪፖርት ለምዝገባ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። እንዲሁም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባቸዋል።

የግብርና፣ የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እና የሕግ ተማሪዎች ሚዛን ከተማ በሚገኘው ሚዛን ካምፓስ በመገኘት ተመዝገቡ የተባለ ሲሆን ከተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ውጪ ያሉ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ካምፓስ እንዲመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተቋሙ የተመደቡ 942 ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት አጠናቋል።

ከተማሪዎቹ በተጨማሪ 82 በጊዜያዊነት ከትምህርት ሚኒስቴር ምደባ የተሰጣቸው መምህራንም እንደሚቀበል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ነባር መደበኛ ተማሪዎች እና ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎችን ከጥር 13 እስከ 14/2014 ዓ.ም ይቀበላል።

የተማሪዎቹ ምዝገባ ሚዛን ከተማ በሚገኘው ሚዛን ካምፓስ እና ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ካምፓስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው መግለጹ ይታወሳል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#MizanTepiUniversity

በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ የአገር አቀፍ ፈተና ወስደው ዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በስሩ በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ መድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ _በዚህም መሰረት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው መቀበል የሚጀምርበትን ትክክለኛ ጊዜ ለተማሪዎቻችን በቀላሉ ተደራሽ በሚሆኑ ሚዲያዎች ማለትም በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን (EBC) እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽና ፌስቡክ ገጾች ጭምር የሚያሳውቅ ስለሆነ ተማሪዎች በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MizanTepiUniversity

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ቀን ተገለፀ።

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ (ተመራቂ የነርሲንግና የፋርማሲ ት/ት ክፍሎች ተማሪዎች ውጭ) ለሁሉም የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ህዳር 5 እና 6 /2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑ የነርሲንግና የፋርማሲ ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜያ ታህሳስ 3 እና 4 መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ተብሏል።

* ከተገለጸው ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች 398 ነጻ የትምህር ዕድል ለአካባቢው ማኅበረሰብ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ነጻ የትምህር ዕድሉ የአካባቢውን ማኅበረሰብ የትምህርት ፍትሀዊ ተደራሽነት እና ተጠቃሚነት በተግባር ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና ዞኖች ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች (ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ) ለ2015 የትምህርት ዘመን ለ218 ሰልጣኞች በሁለተኛ ዲግሪ ነጻ ትምህርት ዕድል በመደበኛ ፕሮግራም ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለሚሰሩ ተቋማት እና የክልሉና የዞኖች የሰው ኃይል ክፍተት ከግምት ውስጥ በማስገባት በድምሩ 180 ነጻ የትምህርት ዕድል በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MizanTepiUniversity

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኮምፒውተርና ሞባይል ስልክ ስርቆት እያጋጠማቸው መሆኑን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ቅሬታቸውን አድርሰዋል።

ዩኒቨርሲቲው ሙሉ አጥር የሌለው መሆኑ የተማሪዎች ማደሪያ አካባቢ ዘረፋ እንዲበራከት ማድረጉንና በዘረፋው መቸገራቸውንና ስጋት እንዳደረባቸው ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርሲቲውን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መሠረት ታደሰ አነጋግረን ተከታዩን ብለውናል።

"ተሰረቀ ስለተባለው የሞባይል ስልክ የተማሪዎች ኅብረት ጥያቄ ለዩኒቨርሲቲው አቅርቧል።"

"የዩኒቨርሲቲው አመራር በተገኙበት ከዞኖ ፖሊስ መምሪያ አካላት ጋር ምልከታ ተደርጓል። ፖሊስ ቀጣይነት ያለው ምርመራ ጀምሯል።"

"የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ግቢ 52 ሄክታር ነው። በቅርቡ በማስፋፊያ የተጨመረ የተወሰነ ቦታ ብቻ አጥር የለውም። ይሁን እንጂ በቂጥበቃ በመኖሩ ስጋት የለውም። ማኅበረሰቡ ነው የኛ ዋነኛ ጠባቂ ብለን የምናምነው።"

"የተፈጠረው የስርቆት ችግር ከውስጥ ማኅበረሰብ ወይስ ከውጭ ማኅበረሰብ የሚለው እየተጣራ ነው።"

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MizanTepiUniversity

በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችው ተማሪዎች፤ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 03 እና 04/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ጊቢ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ጊቢ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

ከ9ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
ዘጠኝ 3 x 4 የሆ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
የስፖርት ትጥቅ፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MizanTepiUniversity

በ2016 ዓ.ም በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥር 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

➧ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - ዋናው ግቢ (ሚዛን አማን ከተማ)
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - ቴፒ ግቢ (ቴፒ ከተማ)

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና 3 ኮፒ፣
ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 3 ኮፒ፣
የቅርብ ጊዜ ዘጠኝ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፓርት ትጥቅ፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot