Natinael Mekonnen
7.84K subscribers
15.9K photos
1.07K videos
20 files
2.49K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
መነሻውን መቀሌ መዳረሻውን ባህርዳር ያደረገ የከባድ ጭነት መኪና 8,900 ክላሽ ጥይት ከሹፌርና ረዳቱ ጋር
በክልል የመረጃና ደህንነት ባለሙያዎች ከፍተኛ ክትትል በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ እጅ ከፍንጅ መያዙን የደቡብ ጎንደር ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።

የዞኑ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኋላፊ አቶ ጌትነት ዓላማው የክልሉን ህዝብና መንግስት የማያባራ ቀውስ፣ትርምስና ጦርነት ውስጥ ለማስገባትና ቀጠናውን የጦርነት አውድማ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የወስጥና የውጭ ጠላቶች ሴራ በተለይ ህውሃት አማራ ክልልን ለማተራመስና ባህር ዳርን ማዕከል አድርጎ እየተንቀሳቀሰም ነው" ብለዋል።
መረጃው የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው።
መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መጠቆም የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ሆነ፡፡

ተመራማሪዎች የልብ ምት መዛባት (cardiac arrhythmia) በመባል የሚታወቀውን መደበኛ ያልሆነ የልብ ምትን አስቀድሞ መጠቆም የሚያስችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ማድረጋቸውን ኤም.ኤስ.ኤን ድረገፅ ዘግቧል፡፡

የሉክሰምበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በተውጣጣ ቡድን የበለፀገው ሞዴል ከመደበኛ የልብ ምት ወደ መደበኛ ያልሆነ የሚደረገውን ሽግግር በ80 በመቶ የትክክለኛነት መጠን መተንበይ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ሞዴሉ በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኘው ቶንግጂ ሆስፒታል በ24 ሰዓት ውስጥ የተወሰዱ 350 የታማሚ ናሙናዎችን በግብዓትነት በመጠቀም በዲፕ ለርኒንግ የማሽን ማስተማር ሂደት የበለፀገ ነው፡፡

ቴክኖሎጂውን ሰዎች ከሚጠቀሟቸው የተለያዩ ተለባሽ ስማርት መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት ለታካሚዎች ስለልብ ምታቸው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች ሲኖሩም በአማካይ በየ30 ደቂቃ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የቅድመ መከላከል ርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላቸዋል፡፡

ሞዴሉ ሰዎች የልባቸውን ደህንነት በየሰዓቱ ክትትል እንዲያደርጉና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ተጠቅመው ጤናቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኦቪድ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ማብቂያ እስከ ሰኞ ሚያዚያ 21 ድረስ ተራዘመ
**
ታላቅ ቅናሽ ያለው የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የ6 ሺህ 124 ቤቶች ሽያጭ ለአንድ ቀን ብቻ ተራዝሟል፡፡ ፈጥነው ይመዝገቡ ፣ ሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የመጨረሻ የሽያጭ ቀን ነው !

በርታካታ ቤት ገዥዎችን እየተሳተፉበት ያለው የኦቪድ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ገዥዎች በቂ የመግዣ ቀናት እንዲኖራቸው ታሳቢ በማድርግና በገዥዎች ጥያቄ መሰረት የማብቂያ ቀኑን ለአንድ ቀን ብቻ ያራዘመ መሆኑን አቪድ ሪል ስቴት አስታውቋል፡፡

• የኦቪድ የ6 ሺህ 124 ቤቶች ሽያጭ በአድዋ ዜሮዜሮ ሙዚየም እየተከናወነ ነው

• ቀድመው ለገዙ 1000 ሰዎች ከ 415 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሆናሉ

• በርካታ የቤት ገዥዎችም በአድዋ ሙዚየም እየተካሄደ ባለዉ ታላቅ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ላይ ተገኝተው ምዝገባ እያከናወኑ ነው

• ግንባታን በአጭር ጊዜ እና በጥራት በመገንባት ከፍተኛ ስምና ዝና ያተረፈው ኦቪድ ግሩፕ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ኦቪድ ገላን ጉራ የተሰኘ መለሰተኛ ከተማን በሦስት ዓመታት ዉስጥ ገንብቶ
ለማጠናቀቅ በቅርቡ ግንባታ አስጀምሯል፡፡

• ኦቪድ በ18 ወራት ግዙፍ የመኖሪያ መንደር፣ በ69 ቀናት 11 ወለል ሕንጻ እንዲሁም በ8 ወራት ግዙፍ የገበያ ማዕከል ገንብቶ ማጠናቀቅ የቻለ ተቋም ነው፡፡
• የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ መለስተኛ ከተማ ውስጥ 6 ሺ124 ቤቶችን ሽያጭ ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚቆይ ሲሆን ታላቅ ቅናሽ የሽያጭ አውደርዩ ሚያዚያ 21 ይጠናቀቃል፡፡

• የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ከቦሌ አየርመንገድ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ተጀምሯል፡፡
የመመዝገቢያ ሊንክ: https://bit.ly/ovid2024
ለበለጠ መረጃ በ 9727 ይደውሉ!
ኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የነገ መኖርያዎ!!!
የኮሪደር ልማት ስራው ለነዋሪዎች መልካም እድል የፈጠረ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራችን ለነዋሪዎቻችን መልካም እድል የፈጠረ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲያካሂድ የነበረውን የ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎች ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል፡፡

በቀሪ ወራት ለላቀ ውጤታማ ስራ የሚያተጉ እንዲሁም የነዋሪዎች ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን ቀልጣፋና ከተማዋን የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ወራት የተከናወኑት የሰው ተኮር ስራዎች የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ ያበሱ መሆናቸውን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡

የመሬት ዲጂታላይዜሽን እና የገቢ አሰባሰብ ስራዎችም ውጤት ካገኘንባቸው ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ 53.7 ሚሊዮን ዩሮ መደበ፡፡

ለኢትዮጵያ 53.7 ሚሊዮን ዩሮ እንመደበ፣ በሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 50 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያስፈልግ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል።

ህብረቱ፦
-ለኬንያ 14፣
-ሶማሊያ 42.5፣
-ሱዳን 52፣
-ኡጋንዳ 32፣
-ለደቡብ ሱዳን 43.5 ሚሊዮን ዩሮ ለጅቡቲ ደግሞ 500 ሺሕ ዩሮ መስጠቱን ገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ጊዜያዊ ገደብ ጣለ።

የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት በኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማስቀመጡን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ፦

- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ፤

- አባል ሀገራት ከአሁን በኋላ ከ2 ጊዜ በላይ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት እንደማይችሉ ፤

- የዲፕሎማቲክ ወይም የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛ የቪዛ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ተነግሯል።

በተጨማሪ መደበኛ ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ተቀይሯል።

ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቆዩትን ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።

ይሄ ገደብ እንከመቼ እንደሚቆይ የተባለ ነገር የለም።
ኢሰማኮ

መንግስት በአገሪቱ ያሉ ግጭቶችን በዉይይት እንዲፈታ እና የሠራተኞች ጥያቄን እና የሥራ ግብር እንዲቀነስ ለቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ ኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ጠየቀ።

በ ትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት “የክልሉ ሠራተኞች ላይ የህይወት፣ የአካል፣ የኢኮኖሚና ማኀበራዊ ጉዳቶች ደርሰውባቸዋል” ያለው ኢሰማኮ “አሁንም የሚሠሙ ችግሮች ወደዚያ አስከፊ መጠፋፋት እንዳይመጣ ትኩረትን የሚሹ” መሆናቸውን አመላክቷል።

ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛው "ኑሮ ውድነቱን መቋቋም ስላልቻለ" የሥራ ግብር እንዲቀነስልንና በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በተደነገገዉ መሠረት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ተግባራዊ እንዲሆንም አሳስቧል።

መንግስት "በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶችና ጦርነቶች በውይይት መፍትሄ እንዲያገኙ ሆደ ሰፊ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ እንዲጫወት፤  ታጣቂ ሀይሎችም ፊታቸውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ለውይይት እንዲያዞሩና ዘላቂ ሰላም መፍትሔ እንዲያመጡ" ትናንት ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።
በአየር ወለድና ኮማንዶ ዕዝ ስር የሚገኝ አንድ ሻለቃ በወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የፅንፈኛውን ቡድን መደምሰሱ ተገለፀ።

የፅንፈኛው ቡድን የተደመሰሰው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ልዩ ስሙ በሬሳና ይድኖ በተባለ ቦታ መሆኑን የሻለቃው አዛዥ ሻለቃ ኢሬና መንገሻ ተናግረዋል ።

በተደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻም በርካታ የጦር መሳሪያ እና የፅንፈኛው አባላት መማረካቸውን አዛዡ ገልጸዋል።

በወረዳው በተፈጠረው ሰላም ለወረዳው አርሶ አደሮች በሰራዊቱ አጋዥነት የአፈር ማዳበሪያ እስከ ቀበሌ ድረስ እየቀረበ መሆኑን ሻለቃ ኢሬና ተናግረዋል። አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ይደርስባቸው የነበረው መጉላላት ተቀርፎ እና ካልተገባ ወጪ ተላቀው ወደ እርሻ ሥራቸው እንዲመለሱ ማሥቻሉም ተገልጿል ።
ኮርፖሬሸኑ የ 9 ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ገመገመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ 9 ወራት የሥራ አፈጻጸሙ የበጀት ዓመቱን እቅድ ሊያሳካ የሚችል አዳዲስ ስኬቶች መመዝገባቸውን ለአንድ ቀን በተካሄደው የአፈጻጸም ግምገማ ተገልጿል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በመሩት በዚህ ግምገማ ለቀሪ ተግባራት የአፈጻጸም አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡

የዛሬ ስድስት ዓመታት የtጀመረው ለውጥና ሪፎርም ግለቱን ጨምሮ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ከፍ ያለ ስኬት ሊመዘገብ እንደሚችል የሚያሳይ አፈጻጸም መመዝገቡን በዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም የታየው ውጤት አመላካች እንደሆነም ተገምግሟል፡፡

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ በመንግስትና በሕዝብ ያገኘው እውቅና ፣ የተቋሙ ገጽታ መቀየር መቻሉ እንዲሁም ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ በግምገማው በጥንካሬ ተነስቷል ፡፡

በሠራተኛውና በአመራሩ መካከል ያለው የተግባርና የአመለካከት አንድነት ፣ የተቋሙ ስኬት አገራዊ ገጽታ እየተላባሰ መምጣቱ፣ የሪል ስቴት ገበያው እንዲረጋ ማድረግ መቻሉ፣ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ግንበታ ላይ የታየው ለውጥ፣በየገቢ እድገት እና በፍ/ቤት የማሸናፍ ዓቅም አሁንም ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ በመደርኩ በጥንካሬ ከተነሱት መካከል ሆነዋል፡፡

የኮንስራክሽን ግባዓት እጥረትን የሚያቃልሉት የኮንክሪትና የብሎኬት ማምረቻ ፋብሪካዎች እንዲሁም የኮከበ ጽብሀ ፣ የሶማሌ ተራ፣የምስራቅ አጠቃላይ ሳይቶች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ማድረግ መቻሉም በግምገማው ተጠቁሟል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በዘጠኝ የእቅድ ወራት በተለይ በመረጃ አያያዝና ማዘመን፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በኮንትራት አስተዳደር ሥራዎች፣ የሪኖቬሽን ሥራዎች ፣ ገቢን ለማሳደግ የተሰሩ ሥራዎች፣ አዳዲስ ሳይቶችን ወደ ሥራ ከማስገባት ረገድ የተሰሩ ሥራዎች ለይ ያተኮረ ግምገማ አካሄዶል፡፡

በዘጠኝ ወራት ገቢን ለማሳደግና ተጨማሪ ሀብት ለመፍጠር የተሰራው ሥራ በበጀት ዓመቱ ከእቅድ በላይ ገቢ ሊገኝ እንደሚችል የሚጠቁም እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

በኮርፖሬሽኑ እድገት ልክ እና ለአደዲስ ፕሮጀክቶች ልማት የሚውል ፋይናንስ የማፈላግ ሥራ እና በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚረዱ ተጨማሪ የአፈጻጸም አቅጣጫ በማስቀመጥ ለአንድ ቀን የተካሄደው ውጤታማ ግምገማ ተጠናቋል፡፡
" ... ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን " - ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች / #UAE / ንብረት የሆነው ' ዲፒ ወርልድ ኩባንያ ' የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ማቀዳቸው ተሰምቷል።

ለዚህ የወደብ አጠቃቀምና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ስምምነት በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት።

ስምምነቱ ወደ መጨረሻውው ምዕራፍ መድረሱንና በሚቀጥሉት 60 ቀናት ተጠናቆ ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር አሳውቋል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሰኢድ ሀሰን አቡዱለሂ ፥ " ኢትዮጵያ ጎረቤታችን ናት፤ ከእነሱ ጋር ቢዝነስ መስራት እንፈልጋለን በአሁን ወቅት የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ወይም Transit Agreement እያዘጋጀን ነው። አንዴ ስምምነቱን ከተፈራረምን በመጀመሪያው ዓመት ከኢትዮጵያ ጭነት 30% እናስተናግዳለን " ብለዋል።

ይህን በተመለከተ " ስምምነቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው በአንድ ወይም ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ እየተወያየን ነው ምናልባት በመጪዎቹ 60 ቀናት ሊጠናቀቅ ይችላል ከ60 ቀናት በኃላ እንፈራረማለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

ከወራት በፊት እ.አ.አ ጥር 1 ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በተመሳሳይ ወደ ተግባር የሚገባበት የመጨረሻው ስምምነት በ2 ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

መግባቢያ ምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴዎችም መታጨታቸውን ተናግረዋል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት ወደ #መጨረሻው ደርሶ ወደ ተግባር ከገባ ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር በሊዝ ኪራይ የምታገኝ ሲሆን ሶማሌላንድ በበኩሏ ለረጅም አመታት ስትፈልገው የነበረውን እውቃና የማግኘት እድል እንደሚፈጥርላት ባለስልጣናቱ አመልክተዋል።

ለንግድ ስራ ሌላ ወደብ መገንባት ሳያስፈልግ የበርበራ ወደብን ኢትዮጵያ እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል።
የተሰጠንን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ሰላም እናረጋግጣለን ፦ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

አዛዡ የአሃዱዎችን የግዳጅ አፈፃፀም በተመለከተ ከሠራዊት አባላቱ ጋር የተወያዩ ሲሆን ማዕከላዊ እዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሸባሪውን የሸኔ ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጥፋት ቡድኑ የሚንቀሳቀስባቸው ዞኖች ወደ ሰላምና ልማት እንዲመለሱ በማድረግ ተልዕኳችንን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀት አለብን ብለዋል።

ዕዙ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን ከግዳጅ ጎን ለጎን በመስጠት የአመራሩንና የአባሉን ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊና ታክቲካዊ ክህሎቱን በማሳደግ ግዳጁን በብቃት የሚፈፅም ሰራዊት ገንብተናል ፤ ሰራዊቱ ማንኛውንም ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ መሰናክል በማለፍ ጠላትን መደምሰስ የሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል።

የመንግስትን የሰላም ጥሪ ባለመቀበል ጫካ የመረጡ ሀይሎች በራሳቸው ጊዜ የቀረበላቸውን አማራጭ እንዲቀበሉ ካልሆነም ተበትኖ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የሸኔን የሽብር ቡድን በመደምሰስ አስፈላጊውን ዋጋ ከፍለን ሰላምን ለህብረተሰቡ እናረጋግጣለን ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ ተናግረዋል።

ከሠራዊቱ ጋር ፊት ለፊት የተወያዩት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ የቀጣይ ተልዕኮ ውጤታማነት የሚረጋገጠው የሰራዊቱ ሞራላዊና ስነ- ልቦናዊ ዝግጁነት የተገነባ ሲሆን መሆኑን ጠቁመው እስካሁን በስልጠና ላይ የተፈጠሩ አቅሞች ይህንን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ከህብረተሰቡና ከፀጥታ ሀይሉ በመጣመር ሰላም በማረጋገጥ ለህዝቡ እፎይታ ለመስጠት የተለመደ ጀግንነቱን እና ድል አድራጊነቱን ለማስቀጠል መነሳሳት ይገባል ሲሉ ለሰራዊቱ አባላት መልዕክት አስተላልፈዋል።