Natinael Mekonnen
7.82K subscribers
16.3K photos
1.09K videos
20 files
2.52K links
ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21
Download Telegram
የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት የ9ወራት አፈፃፀም ሪፓርት ላይ ያነሷቸው ነጥቦች

•የቱሪዝም መረጃ አያያዝን ለማዘመን የሚያስችል tourism satellite account(TSA) ስርአትን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው::

•የኮንሶ አለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ የ8 ቅርሶች ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው::

•ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የጌዲኦ መልካምድር እና የባሌ ተራሮችን በሚዳሰስ ቅርስነት በሀረሪ ክልል የሚከበረውን ሸዋል ኢድ ደግሞ በማይዳሰስ ወካይ ቅርስነት ከ 40 አመት በህላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ሶስት ቅርሶቿን ማስመዝገብ የቻለችበት አመት መሆኑን::

•የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ አካባቢ ምቹ በማድረግ እና የሰው ሀብት ልማት ላይ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል::

•የድሬ ሼክ ሁሴን መካነ ቅርስ ዙሪያ የሚስተዋሉ መሰረታዊ የቱሪስት አገልግሎቶች ጉድለቶችን ለመሙላት ፕሮጀክት ተቀርፆ ለትግበራ ዝግጁ ተደርጓል።

•በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ የኬብል ካር እና ቱሪስት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፕሮጀክት ጥናት፣ የዲዛይን ስራ ማጠናቀቅ ተችላል፡፡

•የጂማ አባጂፋር ቤተመንግስት እድሳት ተጠናቆ በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል::

•ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር በላሊበላ ከተማ በዋናነት ቱሪስቶች በከተማዉና አካባቢዉ የሚገኙ ቅርሶችን ከመጎብኘት ባሻገር ያለዉን ዕምቅ የባህል ሀብት በአንድ ስፍራ መጎብኘት የሚችሉበት ደረጃዉን የጠበቀ የባህል/ቱሪዝም ማዕከል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነዉ፡፡

•በአፋር ክልል በኤርታኢሌ የእሳተ ጎመራ ድንቅ የተፈጥሮ ትዕይንት መመልከቻ ቦታ ላይ ለጎብኝዎች መወጣጫ የሚሆን ደረጃዎች ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመከናዎን ላይ ናቸዉ፡፡

•በተለያዩ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፎች 75 የሀገር ውስጥ እና 16 የውጭ ባለሃብቶች ሴክተሩን ተቀላቅለዋል፡፡

•ከዘርፉ በ9ወራት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ3.5 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ 3.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል፡፡

•በዘርፉ ባለፉት 9ወራት 81,673 የስራ እድሎች ተፈጥረዋል፡፡ ከዚህ መካከል 30,968 ቋሚ የስራ እድሎች ሲሆኑ 50,705 ደግሞ ግዚያዊ ናቸው::
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀሞሮ ወረዳ ላይ ለበርካታ ዓመታት የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የሽኔ አባላት ለምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር እጅ መስጠታቸው ተገለፀ።

በጃን ኢፓ ሲመራ የነበረውና ሰላሳ አምስት የሰው ሀይል ያለው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ከሰላሳ አራት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጋር እራሱ አመራሩን ጃን ኢፓን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት እጅ ሠጥተዋል።

የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ወልዳይ አስፋው በአካባቢው ለብዙ ዓመታት ከህዝቡ ጋርና ከሽብር ቡድኑ ጋር ባደረግነው ውይይት ከጦርነት ይልቅ ሰላምን አማራጭ አድርገው በፈቃደኝነት ከፍተኛ አመራሩን ጃል ኢፓን ጨምሮ ሰላሳ አምስት ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጅ እንዲሠጡ አድርገናል ብለዋል።

በጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም ያሉት ሻለቃ ወልዳይ አስፋው ቀጣይም በድርድርና በሰላማዊ ውይይት የሚያምኑትን ታጣቂዎች እየመከርን ወደ ሰላም እንዲመጡ የማድረግ ስራዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን አጠናክረን እንቀጥልበታለን ብለዋል።

የሀሞሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቀጤሳ ሽፈራው መከላከያ ሰራዊቱ በየጊዜው በሽብር ቡድኑ ላይ በሚወስደው እርምጃ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረው ዛሬም አብዛኛው የሽብር ቡድኑ የሰላምን አማራጭ እንዲጠቀም ያደረገው ሠራዊቱ በመሆኑ ትልቅ ክብር ይገበዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራር ጃን ኢፖ አሁን እያደረግን ባለው የትግል አቅጣጫ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የማይጠቅምና እርስ በእርስ ደም የሚያፋስስ በመሆኑ የእስካሁኑ ይበቃል በማለትና በተሰጠን የሰላም አማራጭ መጠቀምን በመምረጥ በእኔ የሚመራውን ሙሉ ቡድን ይዤ ለመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ሰጥቻለው ሲል አስረድቷል።
„በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት እንደ ሰጎን አንገትን በአሸዋ ስውጥ መደበቅ ሳይሆን፤ የችግሩን መንስኤ መጋፈጥና በሰከነ መንገድ መፍታት ይገባል“

አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በታሪካዊው ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደው 4ኛው ልዩ ሴሚናር ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡
ዩቲዩበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ...🇪🇹👌

ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡