ምክር አልወድም!!በአጋጣሚ ከመጣ ግን አላልፈውም።ለምሳሌ ጃክ ዶውሰን እዚህች
የእራት ግብዣ ላይ የሚናገራት የሕይወት
ፍልስፍና እንዴት እንደምትመቸኝ!
እንዲህ ትነበባለች....
“የሚያስፈልገኝን ሁሉ እዚሁ ከእኔ ጋር አለኝ። እተነፍሳለሁ፣ ጥቂት ባዶ የወረቀት ገጾችም አሉኝ
(የምስልባቸው)
ጠዋት ስነሳ ምን እንደሚፈጠር፣ ማንን እንደማገኝ፣ የት እንደማደርስ ሳላውቅ መንቃትን እወዳለሁ።
ከጥቂት ቀናት በፊት ብቻ ከድልድይ ስር ተኝቼ ነበር፤ አሁን ደግሞ በዓለም ላይ በጣም ውብና ታላቅ በሆነው መርከብ ላይ፣ እናንተን ከመሰሉ መኳንንትና እመቤቶች ጋር ሻምፓኝ እየጠጣሁ ነው።
ሕይወት ስጦታ ናት ብዬ አምናለሁ፤ እናም ያንን ስጦታ በከንቱ ለማባከን አልፈልግም።
ቀጣዩ የሕይወት ካርድ ምን እንደሚሆን አታውቅም። ስለዚህ ሕይወት የምትሰጥህን እየተቀበልክ፣ በየቀኑም ያንን ቀን ትርጉም እንዲኖረው ማድረግን መማር አለብህ።”
— ጃክ ዳውሰን
🥂 cheers

ከአመታት በፊት ነበር ከድሃ እናቴ ብር ሰርቄ ከማፈቅራት ልጅ ጋር የጠፋሁት። በጊዜው እሷ የ 17 እኔ ዴግሞ የ 18 አመት ልጅ ነበርኩ። በጣም ስለምወዳት ልክ እንደጠፋን ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ነበር ይዣት የመጣሁት እና ለሁለት ወር የሚሆን ከፍዬ በርካሽ ጠበብ ያለች ቤት ተከራየን። እኔም ወፍጮ ቤት ሸክም ስራ አጊኝቼ ለትንሽ ጊዜ ሰርቼ ተባረርኩ…እኔም የማፈቅራትም ልጅ እረጅም ጊዜ ምግብ ሳንበላ ፆማችንን እናድር ስለነበር እንደ ወንድ ተደብቄ አለቅስ ነበር ...ይሄም ይባስ ብሎ የቤት ኪራይ ደርሶ እጃችን ላይ ያለው ሲያልቅ አከራያችን ቤት ፈልጉ ብላ አባረረችን ...ቀጥታ ጎዳና ነበር የወጣነው በዚህ ውስጥ ግን ፍቅሬ አይዞህ ይሄም ያልፋል ጠንክር የተሻሉ ቀናቶች እናያለን የኔ ውድ እያለች ሳትለየኝ ታበረታኝ ነበር ...ከትንሽ ጊዜ ቡሃላ አንድ ጥሩ ሰው በጣም አሳዝነነው የስድስት ወር የቤት ኪራይ ከፍሎልን ትንሽ ገንዘብ እረድቶን ሄደ ...እኔም በተሰጠን ብር ንግድ ጀምሬ በትንሽ ጊዜ ውስጥ አሪፍ ገቢ ማግኘት ጀመርኩ ቤታችንም ሞላ ....ሚስቴም አረገዘች ለመውለድ ጥቂት ወራት ብቻ ሲቀራት ነበር ....በትንሽዬ ፀብ ተጣልተን ማውራት ያቆምነው እኔም ከዛ ቡሃላ ቡዙ ሳልቆይ ቤቱን ጥዬላት ወጥቼ ከሌላ ሴቶች ጋር ፈታ ማለት ጀመርኩ አንድ ቀን ግን ....ስራ ላይ እያለሁ ስልክ ተደወለልኝ ሚስትህ ምጧ መቶ ሆስፒታል ነች ቶሎ ድረስ ነበር የተባልኩት ....ስልኩን ዘግቼ በድንጋጤ እየሮጥኩ ስሄድ እዛ እንደደረስኩ ግን ያልጠበኩት ነገር ነበር የገጠመኝ ...ሚስትህን ወደ ሆስፒታል በቶሎ የሚያመጣት አጥታ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ማትረፍ አልቻልንም ህይወቷ አልፏል አለኝ ዶክተሩ ...ከዓይኖቼ እንባ እየፈሰሱ በፀፀት ስሜት መሬት ተቀምጫ ግርግዳ እየደበደብኩ መጮህ ስጀመር ...በድንገት አንድ የህፃን ልጅ ድምፅ ከውስጥ ሰማሁ የኔ ልጅ ነው ብዬ ዘልዬ ክፍል ውስጥ ስገባ ....ነርሶች የሚስቴን በአንሶላ ሲሸፍኑት አየሁ በቃ ምን ልበል ልጅ ስለተወለደልኝ ልደሰት? ወይስ ሚስቴ ስለሞተች ላልቅስ? ብቻ አላውቅም ውስጤ ምን አለ ህልም በሆነ ብዬ ተመኘሁ ....እውነት ነው ይሔ መቼም የማይሻር ከባድ ዘላለማዊ ፀፀት ነው።
✍️✍️ ይለፍ ድርሰት
✍️✍️ ይለፍ ድርሰት
people so tired mutilated either by love or no love.
people just are not good to each other one on one
the rich are not good to the rich the poor are not good to the poor.
we are afraid.
our educational system tells us that we can all be big-ass winners.
it hasn't told us about the gutters or the suicides.
The Crunch
Charles Bukowski
Page 162

ናይጄሪያዊው ደራሲና የፖለቲካ አክቲቪስት ቺነዋ አቼቤ ከፃፋቸው አጫጭር ታሪኮች መካካል አንዱ እንደዚህ ይነበባል ፦
አንድ የሆነ ሰው በቤቱ ውስጥ ባለ አይጥ ውድ የሆነ አልማዝ ይዋጥበታል።የአልማዝ ባለቤቱ አልማዙን የዋጠበትን አይጥ ለመግደል ከአንድ አዳኝ ጋር በመነጋገር ይስማማል።
አዳኙ ወደ ሰውየው ቤት ሲገባ ከ1000 በላይ አይጦች አንድ ላይ አብረው ተሰብሰበው ነገር ግን አንድ አይጥ ብቻውን ተቀምጦ ይመለከተዋል።
አዳኙ ከሌሎቹ አይጦች ብቻውን ተለይቶ የተቀመጠውን አይጥ ይገድለውና፤ አዳኙም ለባለቤቱ "ይሄ አልማዙን የዋጠው አይጥ ነው" በማለት ይነግረዋል።
የአልማዝ ባለቤቱም በመገረም " አይጡ አልማዝ መዋጡን አንዴት ልታውቅ ቻልክ?" በማለት አዳኙን ጠየቀው።
አዳኙም "ደደብ ሀብታም ሲሆን ከሌሎች ጋር አይደባለቅም።" በማለት መለሰለት ።
✍

ይህንን ፎቶ ባየሁት ቁጥር አይኖቼ በእምባ የመሞላታቸው ምስጢር እንቆቅልሽ ይሆንብኛል ።እስከዛሬ
የትኛውም አለም ላይ የተደረገ የነፃነት ትግል እንደ ቬተንሀም ቀልቤን የገዛውና ስሜቴን ያሸፈተው የለም (የ ሀገሬው አድዋም ቢሆን)
ሀገርን መውደድና ለሀገር መኖር ለካ ይለያያል በወቅቱ ሀያል የነበረችውን ፈረንሣይ እና ታላቋን አሜሪካ አንበርክካ ነፃቷን ከማወጇ በላይ የህዝቧቿ ጀግንነት ና ልባቸው ውስጥ ጥልቅ የሆነው የሀገር ፍቅር ስሜት ከምንም በላይ ያስደንቃል ።
*የ ሆቺ ሚኒ ጀግንነት እንዳለ ሆኖ *
ፎቶው ታላቋን አሜሪካ አሽቀንጥረው ከሀገራቸው ካስወጡ በኋላ የተገኘ ነው። (በነገራችን ላይ አሜሪካ በፊልሞቿ ብቻ ነው እስካሁን ቬትንሀምን ያሸነፈቻት ሽንፈቷን ላለማመን )

“እሺ ቆይ … ኢ-አማኝ ነህ ወይስ አግኖስቲክ? ግራ ገባኝኮ?”
"ፈጣሪ የለም አልልም። ፈጣሪ አለም አልልም። ፈጣሪ ምናልባት ይኖር ይኾናል የሚል የጥርጣሬ አስተሳሰብ ውስጥም አይደለሁም።በአጭሩ አማኝም፣ ኢ-አማኝም ወይም የፈጣሪ መኖር ግድ የማይሰጠው አግኖስቲክም አይደለሁም።”
“ታዲያ ምንድነህ?”
“እኔ የምመራው በውጫዊ ሕግ ሳይኾን በውስጣዊ ንቃተ-ሕሊና፤ በመንፈሳዊ ነጻነት ነው። ይህ ለአንድ ሃይማኖተኛ ሰው ‘ባዶነት’ ኾኖ ሊታየው ይችላል። በእውነተኛው ዓለም ግን የሰው ልጅ ያለ ምንም‘ተስፋ’ ወይም ‘መለኮታዊ ጥበቃ’ መንፈሳዊ ነጻነቱን ጠብቆ መኖር ይችላል ብዬ አምናለሁ … መንፈሳዊ ነጻነት የሚጀምረው ከራስህ ውጭ ካሉ አስገዳጅ ትዕዛዛት፣ ከገነት ስጦታ ናፍቆት እና ከሲዖል ቅጣት ፍርሃት ራስህን ነጻ ስታወጣ ነው። ይህም ነጻነት ‘የመኖር ሙሉ ኃላፊነትን በራስ ጫንቃ ላይ መሸከም’ ማለት ነው።”
“ፒካሶ፣ ግራ ገባኸኝኮ! አማኝ አይደለሁም ትላለህ፣ ደግሞ አምላክ የለም ብዬ አልከራከርም ትላለህ። መሐል ለመሐል መቆም አይከብድም? ይሄ መንፈሳዊ ነጻነት የምትለው ነገር መጨረሻው የት ነው?”
“ጥልሽ … መጨረሻ የለውም፤ ምክንያቱም መንፈሳዊ ነጻነት ግብ ሳይኾን ጉዞ ነው። አምላክ የለም ብዬ ድርቅ ብል፣ እኔም እንደ አንተ እምነት ውስጥ ወደቅኩ ማለት ነው። እኔ ግን ካለማወቅም ኾነ ካለማመን እስር ነጻ ነኝ። መኖርን ብቻ ነው የማውቀው። የኔ ትኩረት ‘ፈጣሪ አለ ወይስ የለም?’ በሚለው ረቂቅ ክርክር ላይ ሳይኾን፣ "ሰው እንዴትበነጻነት ይኑር?" በሚለው ተግባራዊ ሕ ይወት ላይ ነው።”
“እንግዲያውስ ያንተ 'አምላክ' ያንተ ሕሊና ነው ማለት ነዋ?”
“ሕሊናዬ መንገዴ ነው እንጂ አምላኬ አይደለም። እኔ የምመራው በኾነውና ባለው እውነት ብቻ ነው። የሃይማኖት ድራማዎች ሳይጋርዱኝ፣ ሕይወትን ራቁቷን በፍቅር ማየት መቻል - ይሄ ነው መንፈሳዊ ነጻነት!”

👏2
የየትኛውም እምነት አክራሪ አይስበኝም። እግዚአብሔር በእነሱ ጭንቅላት ልክ ትንሽ ይመስላቸዋል። ራሳቸውን የፈጣሪ የስለት ልጅ የሚያደርጉት ነገር ከእኔነቴ አይገጥምም። ጭንቅላታቸው ለብልታቸው ብቻ ነው የሚገዛው። ቅንዝራቸው ማስመሰላቸው ውስጥ ተሸጉጧል። እግር በሚረግጠው ቀሚስ ስር ያደረ ግልሙትና አላቸው።
ከእኔ በላይ ማን አለ ባይነታቸው ላይ ትእቢት በትልቁ ተስሏል። ነጠላቸው የመርገም ጨርቅ ነው። የይሁዳ ድልድይ ላይ እንዳሉት ካህን ናቸው። የቅዳሴ ዜማ የማርያም ፀሎት ወደ ደጁ የመለሳትን አመንዝራ ከሰው በተሰወረ ነውራቸው ያነውሯታል።
አጭር አትልበሱ ሲሉ ለእግዜሩ ቃል ለመገዛት አይደለም። ይልቁንም በረጅም ልብስ የተሸፈነ አውሬነታቸው እንዳይጋለጥባቸውም ነው። ከጥበብ ውል የላቸውም። ከተፃፈው ሁሉ ሽርሙጥና የሚል ቃል ጎልቶ ይታያቸዋል። ከተፈጥሮ ጋር ግብግብ ይገጥማሉ።
የተፃፈ ጥበብ ከነውራቸው ያላትማቸዋል። ከተዋበ ድርሰት ውስጥ ግልሙትና ይገንባቸዋል። ከውብ ተፈጥሮ መሀል ለብልታቸው ይገዛሉ። ዝምታቸው ካወራም ካደረገም በላይ ይጮሀል ። በሰዎች ያደመቁት ሀጥያት በህሊናቸው ጓዳ ተፈጥሮ ያረጀ ነገር ነው።
ለአምላክ የተለየ ቅርብ ነን ብለው ራሳቸውን ይሾማሉ። ለፍቅር እርቃኑን ከዋለ አምላካቸው እንኳን አይማሩም። በተደበቀ እርቃናቸው በኩል ያነወሩት እልፍ ግልሙትነት አለ። ከማህላቸው ግን አንድም ንፁህ ሆኖ ድንጋይ የወረወረ አይገኝም። ሁላችንም እኩል ነን። አንደኛችን አፋችን ሌላኛችን ጭናችን ነው የተከፈተው።
የጌታ ነኝ ማለት ብቻውን ፅድቅ ቢሆን ኖሮ ለስቅለት የሚቀርቡት አመንዝሮች እንጂ የቤተመቅደሱ ካህናት ባልሆኑ ነበር። ከተፈለቀቀ ሴትነት ስር ከተገኘ ሀጥያት በላይ ጌታዋ እግር ስር የተሰበረች የአልባስጥሮስ ሽቶ ውድ ናት።

አብዛኛው ሰው በህይወቱ ውስጥ የሚሰቃየው ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር በሚያደርገው አላስፈላጊ ትግል ነው።
ነገሮችን፣ ሁኔታዎችንና ሰዎችን በራሳችሁ ፍላጎትና እቅድ ስር ለማስገባት ስትታገሉ፣ ከህይወት ተፈጥሮአዊ ፍሰት ጋር ትጋጫላችሁ። ህይወት ግን እንደ ወንዝ ናት፤ ወንዝን በኃይል ወደ ወደፈለጋችሁት አቅጣጫ ልታስገድዱት አትችሉም።
ህይወትን ለመቆጣጠር መሞከር ማለት በውኃ ላይ መስመር ለመሳል እንደመሞከር ያለ እብደት ነው።
የመቆጣጠር ፍላጎታችሁንና እኔነታችሁን ለቀቅ አድርጋችሁ ከህይወት ፍሰት ጋር መዋኘት ስትጀምሩ፣ ውጥረታችሁ በሙሉ ይረግፋል። ህይወት እራሷን እንድትመራ ፈቅዳችሁ በዝምታና በንቃት ስትከተሏት፣ እያንዳንዱ ቅጽበት ያለ ምንም ጥረት የሚከሰት ታላቅ መለኮታዊ ተአምር ይሆንላችኋል።
OSHO
ሀላስ

[አንዲት ሴት ለማትወደው ሰው በወርቅና በሀብት ስትሸጥ አየሁ፤ ቤተሰቦቿም "ይህ ለደስታሽ ነው" አሏት። እሷ ግን በመጋረጃው ውስጥ ሆና በዝምታ ታለቅስ ነበር።በዚህ መካከል ትልቁ ሐዘን የሰውን ልጅ ልብ በገንዘብ መመዘናቸው ነው። ፍቅር ነጻ መሆን ሲገባው፣ በወርቅ ሰንሰለት ታስሮ ወደ መኝታ ክፍል ይወሰዳል። ያንን ሰው ስታቅፈው፣ የምታቅፈው ስጋውን እንጂ ነፍሱን አይደለም።
ይህ "ሕጋዊ ግልሙትና" ይባላል፤ ስሙ ግን "ጋብቻ" ተብሎ ይከበራል። ነፍስህ ከሌላ ጋር ሆና፣ ስጋህ ግን ከሌላ ጋር እንዲሆን መገደድ ከገሃነም በላይ የሚያም ስቃይ ነው።ሕብረተሰቡ "ክብር ይለዋል፣ እኔ ግን "ሞት" እለዋለሁ። ስንት ንጹህ ልቦች በዚህ በወግና በልማድ ሰይፍ ተሰልበዋል? ስንት ህልሞችስ በሀብታሞች እግር ስር ተረግጠዋል? ይህ ግፍ በየቀኑ በቤቶቻችሁ ውስጥ ይፈጸማል፤ እናንተ ግን በዝምታ ትመለከታላችሁ። የሰው ልጅ ትልቁ ውድቀት፣ ፍቅርን ከመንፈስ አውጥቶ ወደ ንግድ የቀየረበት ዕለት ነው። ]
Kahlil gibran