የብዕር ስሜ(®)
147 subscribers
28 photos
1 video
2 files
9 links
የብዕር ስሜ»ሂወት ይቀጥላል»ኑ ተቀላቀሉን።አብረን ሀገር ሀገር የሚሸቱ ድርሰቶችን እናጣጥም።*join* እምትለውን ብቻ በመጫን የብዕር ስሜ የተሰኘው ቻናል አባል ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችን ነው።
↘️⬇️⬇️⬇️↙️
➡️ JOIN ⬅️
↗️⬆️⬆️⬆️↖️
Download Telegram
Dani admin:
ይሁን ግድ የለኝም፦

ቅዠት አልባ ሌሊት
ውል ያጣ ሠንሠለት
የቀዘቀዘ እሣት
ሊገለፅ የማይችል ሠላም ያጣ ህይወት
ከልብ ውሥጥ ገብቶ
ሸምቀቆ ቀበቶ
አሣሥሮ 'ሚያሥቀምጥ
ሣይገዛ ሲሼንቶ
ይሁን ግድ የለኝም(2)

ግን ብቻ ንገሯት ሠላም አይገኝም
መውደዴ ማፍቀሬ በግልፅ ባይታይም
እኔ እወዳታለው እሷ ባትወደኝም
ይሁን ግድ የለኝም(2)

ሢያሻት አትረዳኝ ካወቀች በኃላ
አፌ ቃል ቢያወጣ ሣትሠማው ከሌላ
አንደበቴ ይድፈር
ፍቅሩን ለመናገር
ያኔ ባይገባትም
አቅም አያንሠኝም
ይሁን ግድ የለኝም(2)

ንገሯት ንገሯት ንገሯት ብያለው
ከርሷ ጋር ለመኖር ብዙ ጓጉቻለው
ያለችኝን ተሥፋ ማብዛት ፈልጋለው
ደሥተኛ ለመሆን ብዙ አቅጃለው
ይወድሻል በሏት ያኔ ምንም ትበል
ከተቀበለችኝ በፍቅሯ ልጠለል
ካልተሣካልኝም ከፊቷ ልገለል
ብትችልም ባትችልም
ያኔ አይጨንቀኝም
ይሁን ግድ የለኝም(2)

ዳንኤል ጉታ(ከዮህናን ደጅ)
@yohnanda
@yohnanda
@yohnanda
አይንሽ እርቦኛል፦

ፍቅሬ የጠዋቷ
የልቤ ጥማቷ
የመኖር ምኞቴ የህልሜ እውነታ
ትዝታሽ ታሽጎ ሆነብኝ ትዝታ

ከገነት የሚፈሥ እንዥቅዥቅ ድምፅሽ
አምሣለ መላእክት አምላክ የኳለሽ
ጨረር አፈንጣቂ ተዋጊ አይንሽ
አድምጪኝ ፍቅርዬ ልቤ ተራበሽ

ደሞም ከነገሩኝ...
ትገኛለሽ ካሉኝ ከጠቆሙኝ ቦታ
ሣልታክት ጠብቄ በፀሀይ ሥመታ
ዝናብ ሢወርድብኝ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ
በእዝነ ህሊና መምጣትሽን ሥዬ
ፎቶሽ ተለጥፎ ከፊት ይታየኛል
ሀውልትሽ ላይ ሆኖ ዝም ብሎ ያየኛል
እኔ አወራዋለው እሡ ያፈጥብኛል
ዝምታ መልሥ ነው ብሎ ይነግረኛል
የፍቅርዬ ቤትዋ እዚህ ነው ይለኛል
ታድያ ምን ሆነሽ ነው ???

አትወጪም አትገቢም
አንቺን መጠበቁ አላታከተኝም
ሥትወጪ ሥትገቢ ምነው አትታይም
እንደዚህ ገርጥቼ
አንቺን በመጠበቅ ቆሽሼ ገርጥቼ
አይንሽን ናፍቄ አይንሽን ተርቤ
በቅዥት አለሜ ላገኝሽ አሥቤ
እፋጠጣለውኝ ከፎቶሽ ፊትለፊት
መኖሪያሽ ነው ካሉት ሀውልትሽ ላይ ካሉት

አይንሽ እርቦኛል
ፍቅሬ ናፍቀሽኛል
ንገሪው ለልቤ ከየት ያገኝሻል

ዳንኤል ጉታ (ከዮህናን ደጅ)

@yohnanda
@yohnanda
@yohnanda
እነሆ ግብዣ

ለ ግጥም አፍቃሪዎች በሙሉ እነሆ ለግጥም ጥም መቁረጫ ይሆነን ዘንድ በ202 ገፆች 106 ጥዑም ግጥሞችን ከትባ በገበያ ላይ ውላለች

ከዚህ በላይ ጥም መቁረጫ አለ???

የየራሳችሁን ያዙ አያምልጣችሁ
​​እነሆ ግብዣ

ለ ግጥም አፍቃሪዎች በሙሉ እነሆ ለግጥም ጥም መቁረጫ ይሆነን ዘንድ በ202 ገፆች 106 ጥዑም ግጥሞችን ከትባ በገበያ ላይ ውላለች

ከዚህ በላይ ጥም መቁረጫ አለ???

የየራሳችሁን ያዙ አያምልጣችሁ
በዝግ በር

እንደድሮ ቀሚስ መሬት እየጠረግሁ
የእግርሽን አሻራ ተግቼ እየፈለግሁ
እንደጉም
ሳዘግም
እንደሰርዶ ስሳብ
ባካል ብታመልጪኝ ደረስኩብሽ ባሳብ
ልብአይገታም በሩ ልብአይገታም መስኮት
በዝግ ቤትሽ ገባው ልክ እንደ መለኮት

>ሼር ያድርጉ>

በውቀቱ ስዩም

@nanmak
@nanmak
@nanmak
 «በጠራ ጨረቃ»

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት
«ሳማት ! ሳማት !» አሉት
«እቀፍ ! እቀፋት።»
አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ
ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ
ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ
ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
ዋ ጀማሪ መሆን ! ዋ ተማሪነት ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት !
በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት...

መንግስቱ ለማ

@nanmak
@nanmak
@nanmak
አንች ብዙ (1)

አንችነትሽን የቀመሰ--አኗኗርሽን ያወቀ፤
መጠቀ፡፡

አዋዋልሽን የመሰከረ፤
አኗኗርሽን የተናገረ፤
ከሰረ፡፡

ያንች አዋዋል--ሚስጥር ነው--ትርጓሜው የሰፋ፤
ከልብ ላይ ውል እያለ--ከንፈር ላይ የሚጠፋ።

ሀሁ

@nanmak
@nanmak
@nanmak
ከአዱንያ ጋጋታ፤
ተነጥሎ ላፍታ፤
አለም በቃኝ ብሎ ፥ ከአይንሽ ላይ ለዋለ፤
ሁሉን ያካተተ ፥ የአለም ሚስጥር አለ፡፡

ሀሁ
ሌቦች ሌቦች ሳይሆኑ ግብዞች ናቸው። ሳታወላውል የምታምነው ሰዎች ዛሬ የሚሰሩትን ስህተት ሁሉ ሳይሳሳቱ በፊት ይሰድቡት እንደነበር ነው። ዛሬ ሌባ የነበረው ትላንት ሌባ አሲዟል። ከሃዲዎች ከመካዳቸው በፊት ከሃዲ ሲያሙ ነበር።...

አማሌሌ

አዳም
#የፈረሱ_መልኮች

( ኤፍሬም ስዩም )

ከዘመናት ኋላ
ድንገት ባጋጣሚ አንድ ቀን ያየኋት
እሷን እያሰብኩኝ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ።
ገረመኝ
ደነቀ…
ለካ . .
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ጠፍቷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያ አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ በበኩሌ… ከዚህ የበለጠ ላወራ ምችለው
አንድም ቃል የለኝም
ፈርሶ ለማየው ቤት አራት ኪሎ ላለው
ሁኔታው…

ክፍት የእንጨት አጥር
ትንሽ ገደድ ያለ… ልሙጥ ቆርቆሮ በር
መላ ቅጥ የሌለው
ለቅሶና ሙዚቃው የማይለይ ሰፈር
ነበር …
ግን…
ፈገግታ የሞላው
በቤቱ ጥበት ልክ… ደስታ የማያጣው
ግድግዳውን የሚያልፍ ሃዘን የወረረው
ላ'መት በዓልና
ላ'መት በዓል ዋዜማ ብቸኛ ቀናቸው
እፎይ የሚሉበት
ህፃናት ተጫውተው
ጠግበው የሚያድሩበት አዋቂዎች በልተው
ሰፈር…
እዚያ ነበር።
አሁን ግን የለችም
ውበቷ ተረስቶ የገባችበትን አንድም የሚያውቅ የለም
የትገባ - ያ - ውበት
የትገባ- ያ - ቁመት
ሲያስጨንቅ የኖረው ወንዱን ሁሉ ባምሮት
ተስፋ የነበረው ለመንደሯ ጭንቀት።
እልፍ መአት ወንዶች በበሯ አልፈዋል
ባይተኟትም እንኳ
አይኗን አይተው ብቻ እድሜ ቀጥለዋል
ግና…
ያሳዝናል…
እድሜ የጠገቡ ጉልበተኛ ወንዶች ቤቷን አፍርሰዋል
እንኳን ቤቷ ፈርሶ
አንድ ቀን ስታኮርፍ እድሜ እንደምትቀንስ መች ይገባቸዋል።

ድንገት ባጋጣሚ
አንድ ቀኑን ያየኋት እሷን እያሰብኩኝ
ከዛማ ኋላ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ
ገረመኝ
ደነቀኝ
ለካ…
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ሄዷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያው አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ … በበኩሌ…
ከዚህ የበለጠ ልናገር የምሻው
አንድም ቃል የለኝም ፈርሶ ለማየው ቤት . . አራት ኪሎ ላለው
ልደታ ላይ ላለው
ሰንጋ ተራ ላለው
የትም ሰፈር ላለው።
ስለሷ ግን ላውራ
ውበት ጠፍቶ እዳይቀር ከግድግዳው ጋራ
በእርግጥም መንደሯ
ተስፋው የሞተላበት
ጦር የወደቀበት
በተራ ወታደር የተረታ ንጉሥ የሚመስል አይነት።
ሞቱን የሚጠብቅ
ታስሮ የሚማቅቅ
መሞት አለመሞት የኑሮ ትንቅንቅ
እሷ መንደር መሃል ይታያል ይሄ ሃቅ።

የፈረሱ መልኮች
የገጠጡ ገፆች … የወየቡ እጆች … ያፈጠጡ አይኖች
የጠቆሩ ቀዮች
ወዝ አልባ ጥቁሮች
ቆዳውን የበላ እረዣዥም አጥንት
ብዙዎች የሞሉበት
ሞልተው ሚሞቱበት
ከሕይወት ተፋተው በተስፋ እጦት ምክንያት።
ሕዝቡ ሚደርበው
ነጠላና ጋቢው
ሀዘን የሸመነው ጨለማ ብርድልብስ
ግራ ጎረቤቷ ህፃን የሚያለቅስ
እናቱን የሞተች በዐዋላጅ እጦት።
የቀኝ ጎረቤቷ እናት ምታቃስት
ሴት ልጇ ያበደች የምታስታምማት።
እወዲያ ጥግ ላይ…
ቤት አልባ- ጎልማሳ
በረሃቡ ምክንያት. . አካሉ የከሳ
ከዘመና በፊት…
በሺህ ዘጠኝ መቶ . . ዘጠና ሁለት ዓመት
ሁለት ዓይኑን ያጣ …በወንድሞቹ ቀስት…
ወዲህ ከትቦው ጎን
ያገሩ ቆሻሻ በሚያልፍበት በኩል
መምጫው ያልታወቀ… አንድ ትንሽ ህፃን…
እድሜው የሚመጥን አስር ዓመት ያህል
የሰውና የከብት ቆሻሻ ካለበት
ትቦ- ጎንሚተኛ
በልጅነት እድሜ የሌሉት ወላጆች
በልጅነት ዕድሜው የሽማግሌ አይኖች
ችግር የሰራበት…
ትንሽ ግንባሩ ላይ አንድ ሺህ መስመሮች
መንተራሻው ድንጋይ ፍራሹ ኮረኮንች
በጀርባዋ በኩል

ሰባት የወለደ አባት የሚያነክስ
ሰባቱን ልጆቹን ድንጋይ ፈልጦ ሚያጎርስ
ሰባቱን ልጆቹን. . ለምኖ የሚያለብስ።
ከፊቷ ትንሽ ሱቅ
ሃሊማና ከድር
ሁለት ባለትዳር… የሰፈሩ ህይወት. . የሰፈሩ አለኝታ
በጭልፋ የሚሸጡ የሃምሳ ሳንቲም ፓስታ
ይህን የሚመስሉ ብዙዎች የሞሉበት
በቁም የሚያለቅሱ ብዙዎች የሞቱበት
የፈረሱ መልኮች. . የሕይወት ግምጃ ቤት።

ነበረ…
ዛሬ ፈርሶ ማየው
መንደሯን የሞላው
የሚገርመው ግና?…
መሶብ ሙሉ ስቃይ . . እንስራ ሙሉ እምባ
የሆነው ይህ ቦታ
የመንገድኛውን. . ዓይን. . የመንገደኛውን. . ልብ ባዘን እያጓጓ
እሷ ግን ነበረች ቀይ ፅጌረዳ የእሾህ ማል አበባ
እናም በዚያ ሰፈር
እናም በዚያ መንደር
የርሷ መኖር ብቻ ለሰፈሩ ሰዎች ሳቅ ይፈጥር ነበር
ተስፋ ይሰጥ ነበር
ጥጋብ ይሆን ነበር
*
ባለማወቅ እንጅ
ጤዛውን ለማበስ
ፅጌውን መቀንጠስ… ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ እንጂ…
ላንድ ዝግባ ሲባል
እልፍ አበባ መቁረጥ እልፍ አበባ መጣል
ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ ነው እንጅ
ያለማወቅ እውቀት ስልጣኔ መስሎን
ልማት ነው እያልን የሙጥኝ ስላልን
እንጂ…
ብናውቀው ኖሮማ ውበት ቅርስ እንዲሆን…
ብናውቀው ኖሮማ. .
በህይወት ግምጃ ቤት.. ተጥሎ የሚኖር ተምሳሌት እንደሆን
ብናውቀው ኑሮማ
በውበት ብናምርን ቅርስን ብናከብር
ያን ያህል ጨክኖ ይህን የርሷን መንደር
ይህን የእርሷን ሰፈር
ማን ያፈርሰው ነበር።…

ዛሬ…
በዚያ መንደር
ከልጅት መኖሪያ ፍርስራሽ ጣውላ ስር
ከቤተ-መንግስቱ አረንጓዴ ሰፈር
ክፉ ጠረንይዞ ነፋስ ይጓዝ ነበር።

(ኑ፦ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦84 - 88)

@nanmak
~ስንብት~
....
(በአቤል ምሕረት)
....
የውልሽ አለሜ
የውልሽ ቀለሜ
በዘናጭ ፊደላት
በደማቅ ቀለማት
ፍቅርሽን ለማድመቅ
የተንተባተብኩት
ፊትሽ ተሰይሜ የተንቀጠቀጥኩት
ፍቅር ኮ' ነው ያልኩት ...
የቃል ሽንገላ እንጅ ~ አልነበረም እውነት
ለውበትሽ ማማር ~ ሰርክ መንሰፍሰፌ
ከጫማዎችሽ ስር ~ አጉል መነጠፌ
ከኔነት መሐላ ~ ላንችነት የቆምኩት
እመኝኝ ውሸት ነው ~ ሁሉንም የሆንኩት
~~~
አልወድሸም በቃ
ትቼሻለሁ በቃ
~~~
ከህይወትሽ መዳፍ ~ እንዳልነበርሁ እርሽኝ
የዘመንሽን ህመም ~ በሽኝት ደብዳቤ ጠቅልለሽ አጉርሽኝ
ትቼሻለሁ ~ እርሽኝ
~~~
ድጋሚ ላልወድሽ ~ መሐላ አቁሜያለሁ የበተስኪያን ደጃፍ ~ በጄ መትቻለሁ
አልወድሽም ብዬ ~ ለራሴ ምያለሁ!
አዎ...ን ~ ትቼሻለሁ!
.... ... ....
ስሚኝ እየውልሽ!
ለፍቅርሽ ማሳያ ~ ቃላት ሸሹኝ ያልኩሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት ነው ልንገርሽ
ለምን 'ደው ታውቂያለሽ?
ወድጄሽ ~ ባፈቅርሽ?
ውስጠቴን ~ ብሰጥሽ?
በዕምነት ~ ብከተልሽ?
~~~~
☞ልቤን ገፈተርሽው
ዕምነቴን በላሽው
ውስጠቴን ጎዳሽው
አሁን ትቼሻለሁ ~ እኔነቴን እርሽው
ባጎደፍሽው ዕምነት ~ ጠፍንገሽ ያሰርሽው
ውስጤ ጉድፍ በቅሏል ~ በዕብለት የዘራሽው
~~~
አሁን እርሽኝ በቃ
ትቼሻለሁ በቃ ብትመጣም ጨረቃ።
~~~
በፈቀድሽው ንጎጅ
ላፈቀርሽው ስገጅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።
( FB አቤል ባርች)

@nanmak
አባትነት እኮ

ቅብዓ-ሰማያት ሆኖ ደህንነት ቢረቅም
የሕፃን ትንንሽ እጅ ከካህን ይባርካሉ።
ልጄ ሆይ! አባትህን ባርከኝ
ልጄ ሆይ! ፍቅሬ ሆይ! ላከኝ
"አቤት!" ልበልህ "እንዳልከኝ!"

እርግብግብ ልበ ርግብ የሚታዘዝ ልኮ
አባትነት ልጄ አባትነት እኮ
የቆሙ መምሰል ነው ድሆ ተንበርክኮ።
ምጥን አለመጮህ ፍርሀትን መደለል
እያሰቡ ኖሮ ያላሰቡ መምሰል
አብነት ነው ልጄ የነገን ተላሚ
ትሁት ቸልታ ነው ከቋሚ ጋር ቋሚ።

አባትነት እኮ አባትነት ማለት
ተኮሳትሮ መሮ ለመድሀኒትነት
በልብ ማፍሰስ ነው የ'ሹሩሩ ጅረት
እሹሉሉ ልጄ...እምንድነው እሹ
እሹሉሉ ልጄ...ትንሹ ቅዱሹ
ኸለ ኸነ ገታ ኸለ ኸነ ሽኮ
መኮለታተፍ ነው አባትነት እኮ።

መዘክር ግርማ

@nanmak
@nanmak
@nanmak
ደማምዬ ልጅ ናት

ከዘፈን ገላ'ና ከለምለም እወዳ
ቀምሞ የሰራት እሪኩም ዘመዳ
ደማምዬ ልጅ ናት...በደማምነቷ
የተከለከለ በተስኪያን መግባቷ...

መድረኩን ቢነሷት
ማኅሌት ቢገፏት ባይሰጧት ዲቁና
ከንፈሯ ለሃሌ ዐይኗ ለትወና...

የጻፈችም እንደሁ ጥርሷን አስመስላ
ያወራችም እንደሁ ልብ ጨርቅ አስጥላ
የሳቀችም እንደሁ ክራር ተኮልኩላ
የተቆጣች እንደሁ እርግፍ እንደ ሾላ!

እርግፍ እንደ ሾላ ቁጣዋን ሰምቼ
እሆዷ እንድገባ በ'ጇ ተነስቼ።

መዘክር ግርማ ከ ወደ መንገድ ሰዎች


@nanmak
@nanmak
@nanmak
👉 ፈሶ ምታየው
ከ እህቴ ቀሚስ ስር
አለው ትልቅ እንባ
አለው ትልቅ ሚስጥር
እንዲህ የማይባል
እንዲህ 'ማይነገር
አለው አንዳች ነገር

✍️ሚዳጉ(ዳንኤል ጉታ )
የብዕር ስሜ(®) pinned «፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ ከእለታት አንድ ቀን ስም እየተሰጠ ለፍጥረታት ሁሉ እየተመረጠ አንድ ሰው መጥቶ መድረክ ላይ ቆመና ”አባት” ነህ ተባለ ምግባሩም ታየና . ከዛም ባለተራ አንዲት ሴት ብቅ አለች ”እህት” ነሽ ተብላ እሷም ተሰየመች ደግሞ አንዱ ሲመጣ እሱም ደርሶት እጣ ”ወንድም” ነህ ብለውት ከመድረኩ ወጣ ”አክስት፣አጐት፣አያት” ሁሉም ጥሪ አገኙ እንደ ምግባራቸው…»