Nahom Tilahun
883 subscribers
439 photos
14 videos
11 links
በዚህ channel አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ታገኛላቹ ቤተሰብ እየሆናቹ ለሰውም አጋሩ
Download Telegram
Nahom Tilahun
Photo
የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።

ልብ ይበሉ፦ ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማጣመር (Harmonization) በነዚህ ሊንኮች ይጠቀሙ።

💸 ዳሽን ባንክ: https://dashensuperapp.com/dashen-fayda

💸 ዘመን ባንክ: https://fayda.zemenbank.com

💸 ሒጅራ ባንክ: https://apps.hijradigital.com/fayda/v2

💸 ሕብረት ባንክ : https://services.hibretbank.com.et/fayda

💸 ብርሀን ባንክ: https://nationalidharmonization.berhanonline.et:9095/fayd...

💸 አዲስ ባንክ: https://fayda.addisbank.com.et

💸 አቢሲኒያ ባንክ: https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect

💸 አዋሽ ባንክ : https://fayda.awashbank.com

💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ: https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization

💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ https://cbefayda.cbe.com.et/

💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡ https://obfayda.oromiabank.com/

💸 ወጋገን ባንክ : https://fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization

💸 ንብ ባንክ፡ https://fayda.nibbank.com.et/

💸 ፀሀይ ባንክ፡https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home

💸 ስንቄ ባንክ : https://fayda.siinqeebank.com:7443

💸 ዘምዘም ባንክ : https://fayda.zamzambank.com.et

💸 አማራ ባንክ : https://fayda.amharabank.com.et
9
ለነፃነት ወርቅነህ (ነፂ) ቤተሰቦች የድጋፍ ጥሪ!

#Ethiopia | ሁሌም በሳቁ ለሚያሳቀን፣ በስራዎቹ ለሚያዝናናን ነፂ... ዛሬ ለቤተሰቦቹ አለን እንበላቸው!

​ በኢቢኤስ (EBS) በተላለፈ ልዩ ፕሮግራም ላይ የአርቲስቱ የቅርብ ጓደኛ የሆነው አርቲስት አስኔ፤ የነፂን ባለቤት እና ሦስት ልጆች ለመደገፍ የታቀዱ ወሳኝ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

ይፋዊ የጎፈንድሚ (GoFundMe) ድጋፍ:
ለቤተሰቡ ቋሚ ድጋፍ ለማድረግ የተከፈተውን ይፋዊ ሊንክ በመጠቀም አቅምዎ የፈቀደውን ይለግሱ፡
👉 https://gofund.me/c3a0a4d72

የዩቲዩብ ገቢ ለቤተሰቡ:
ነፂ ህይወቱ ካለፈበት ጊዜ ጀምሮ በEBS የሚተላለፉ እሱ ያለበት ፕሮግራሞች የዩቲዩብ ገቢ በሙሉ ለቤተሰቡ እንዲሰጥ ተወስኗል። (ቪዲዮዎቹን ማየት እና ማጋራትም ድጋፍ ነው)

3️⃣ የልደት ቀን ልዩ ዝግጅት:
በፊታችን የካቲት ወር በሚከበረው የነፂ የልደት ቀን፤ እሱን የሚዘክር እና ለቤተሰቦቹ ገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ታላቅ መርሃ-ግብር ይካሄዳል።

​ነፂ በስራዎቹ ሁሌም በልባችን ይኖራል፤
አሁን ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጎን በመቆም ፍቅራችንን በተግባር እናሳይ!

8😢3
" በአሁኑ ሰዓት በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ውስጥ (በአውሮፕላን ማረፊያ) የቆመ ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የለም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ወደ አንዳንድ ከተሞች የሚደረጉ በረራዎችን በጊዜያዊነት የሚያቋርጥ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት እና የፀጥታ ስጋት ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንዳንድ ከተሞች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለጊዜው የሚያቋርጥ መሆኑን አየር መንገዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የአየር መንገዱ ከፍተኛ ሃላፊ " በክልሉ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና ከሚመለከታቸው አውሮፕላን ማረፊያዎች ካሉ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት ጋር የሚመካከር መሆኑን " ገልጸዋል።

በምክክሩም መሰረት " በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ከተሞች የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው ያቋርጣል " ብለዋል።

በተጨማሪም " በአሁኑ ሰዓት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ውስጥ (በአውሮፕላን ማረፊያ) የቆመ ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የለም " ተብሏል።

Via:tikvahethiopia

@nahome93
2
ሰበር ፦ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አዲስ አሁን የተላከ የሚሳኤል ጥቃትን ማክሸፏ ተገለጸ

የኤምሬትስ የዜና ወኪል (WAM) እንደዘገበው፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የመከላከያ ሰራዊት አዲስ የተተኮሱ የኢራን ሚሳኤሎችን በተሳካ ሁኔታ መትቶ ጥሏል።

የሀገሪቱ የጸጥታና የመከላከያ ሰራዊት የዜጎችንና የነዋሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

Via WAM
@ጉርሻ page

@nahome93
👍2
ጦርነቱ ተባባሰ፡ እስራኤል በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ፈጸመች

የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ ቴህራንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ የሚባል የአየር ጥቃት አድርሳለች።

1. እስራኤል ወደ 200 የሚጠጉ የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም በኢራን ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።

2. ከ500 በላይ ኢላማዎች ተመተዋል። ከነዚህም መካከል የኢራን ሚሳይል ማስወንጨፊያ ጣቢያዎች፣ የአየር መከላከያ ስርዓቶች እና የኑክሌር ተቋማት ይገኙበታል።

3. በጋርምዳሬህ፣ ኡርሚያ፣ ቡሼር እና ኮም ከተሞች ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

4. በምዕራብ ኢራን የሚገኘውና ለሚሳይል ማስወንጨፊያነት ያገለግል የነበረ የታብሪዝ ቦታ ሙሉ በሙሉ መመታቱ ተዘግቧል።

5. ጥቃቱ "የኢራንን የሚሳይል አቅም ለማዳከም" እና የእስራኤልን ደህንነት ለማስጠበቅ የተወሰደ እርምጃ ነው ብሏል።

የኢራን ጦር በበኩሉ አጸፋዊ እርምጃ እንደማይቀረው በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛል።

Via The National
ጉርሻ page

https://www.facebook.com/share/17zzRD9GxU/?mibextid=wwXIfr
4
ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ለተፈጸመባት ጥቃት የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን ቀጥላለች።

በእስራኤል እና በአሜሪካ አጋሮች ላይ የሚሳኤል ናዳ እያወረደች ትገኛለች።

ከኢራን ጥቃት ሰለባዎች አንዷ የተባበሩት አረብ ኤሬትስ (UAE) ስትሆን ከጥዋቱ የቀጠለ ጥቃት ምሽቱን እያስተናገደች ነው።

በተለይ በዱባይ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት (DXB) በአንድ የመንገደኞች ማረፊያ ላይ ጥቃት ደርሶ 4 ሰዎች ተጎድተዋል።

መጠነኛ የንብረት ጉዳትም ደርሷል።

ከላይ የተያያዘውንና ኤርፖርቱ ውስጥ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪድዮ አልጀዚራ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ዱባይ እንዲሁም አቡዳቢ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሁሉም በረራዎች ለጊዜው ተቋርጠዋል። 

የመንገደኞች ደህንነትን ለመጠበቅም የኤምሬትስ አየር ክልል በከፊል ተዘግቷል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) መንግስት ሁሉም በረራዎች እስከሚቀጥለው ማስታወቂያ ድረስ ስለተሰረዙ ሰዎች ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ከመሄድ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ የሀገሩ መከላከያ ሚኒስቴር ከኢራን የተተኮሱ 132 ሚሳይሎችን ማውደሙን እና 195 ድሮኖችን ጥቃት ሳያደርሱ ማክሸፉን አስታውቋል።


Via:tikvahethiopia

@nahome93
7
2
ከ5ኛ ፎቅ ወድቃ በተአምር የተረፈችው ህፃን እና የፈጣሪ ጥበቃ 🙏

በአዲስ አበባ ከተማ የፈጣሪን ማዳን እና በህፃናት ላይ ያለውን ጥበቃ ያሳየ አስገራሚ ክስተት ተፈጥሯል።

የዛሬ አምስት ቀን ከመንታዎቹ አንዷ የሆነችው የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ሊዮ ማሃሪ በአዲስ አበባ ከቤተሰቦቿ ጋር በምትኖርበት አፓርትመንት ውስጥ ከእህቷ ጋር በረንዳ ላይ እየተጫወተች ነበር።

ነገር ግን በበረንዳው መከላከያ ብረቶች መሃል የነበረው አንደኛው ክፍተት ሰፊ በመሆኑ ህፃኗ አዳልጧት ከ5ኛ ፎቅ ላይ ወደ ታች ልትወድቅ ችላለች።

ህፃኗ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰደች ሲሆን ለጥቂት ሰዓታት ትንፋሽ ከማጠር ውጪ ምንም ዓይነት ከባድ አደጋ ሳይደርስባት በተአምር ልትተርፍ ችላለች።

የህፃኗ አባት አቶ ማሃሪ ስለተፈጠረው ክስተት ሲናገሩ ልጃቸው ከዚህ ሁሉ አደጋ በፈጣሪ ቸርነት እና ርህራሄ ብቻ ምንም ሳትሆን መትረፏን ገልጸው ፈጣሪን አክብረዋል።

አባትየው አክለውም ይህ ድንገተኛ ክስተት የፈጣሪን ታላቅነት እና በህፃናት ላይ ያለውን ልዩ ጥበቃ በግልፅ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ ህፃን ሊዮ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆና ከቤተሰቦቿ ጋር ትገኛለች።

ይህ አጋጣሚ ምንም እንኳን በፈጣሪ ቸርነት ያለምንም ጉዳት ቢጠናቀቅም ለሁላችንም ግን ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው።

ወላጆች ልጆች ሲጫወቱ በጥንቃቄ እንዲከታተሉ እና ከአይናቸው እንዳያርቋቸው እንዲሁም በረንዳ ላይ ብቻቸውን እንዳይወጡ በሮቹን በመቆለፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እኛም መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

በተጨማሪም የፎቅ ላይ በረንዳ ብረቶች ለልጆች አደጋ በማያመጣ መልኩ መሰራታቸውን እና ሰፊ ክፍተት የሌላቸው መሆኑን ደጋግሞ መፈተሽ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Via ዛሬ ታዲያስ አዲስ ላይ የቀረበ ነው::
@ጉርሻ Page

@nahome93
9
Nahom Tilahun
Photo
የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል 

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ 

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡ 

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
3
Channel name was changed to «Nahom Tilahun»
በዛሬው ዕለት በአዋሽ 7 ከተማ መግቢያ ላይ በአንድ ተሳቢ ከባድ መኪና እና ነዳጅ በያዘ ቦቲ መካከል እጅግ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል።

ተሽከርካሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ በመጋጨታቸው ምክንያት በመንገዱ ላይ ብርቱ እሳት የተነሳ ሲሆን፣ በአደጋው ሳቢያ የአንዱ መኪና አሽከርካሪ ህይወት ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።

ይህ ዓይነቱ ድንገተኛ መርዶ የሁላችንንም ልብ የሚሰብር እና በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ያለብንን ከባድ ሃላፊነት በድጋሚ የሚያስታውስ ነው።

እያንዳንዱ አሽከርካሪ በኃላፊነት ስሜት እንዲጓዝ እና የራሱንም ሆነ የሌሎችን ወገኖች ህይወት ለመጠበቅ ሲል በከፍተኛ እርጋታ እንዲያሽከረክር ከልብ እንማጸናለን።

ከመቅጽበት የሚከሰት መዘናጋትና ፍጥነት የማይተካውን የሰው ህይወት የሚቀጥፍ በመሆኑ፣ እባካችሁ ሁላችንም በትዕግስት እና በጥንቃቄ እንንዳ።

Via ዘመን ተሻጋሪው
@ጉርሻ Page

@nahome93
4
በአዲስ አበባ ከተማ የሲጋራ ቁራጭ መንገድ ላይ መጣል 2 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሲጋራ ቁራጭ በመንገድ፣ በአደባባይ ወይም በማንኛውም የህዝብ መገልገያ ቦታ ላይ የሚጥል ግለሰብ በ2 ሺህ ብር እንደሚቀጣ ገልጿል።

ይህ እርምጃ የከተማዋን ንፅህና፣ የህዝብን ጤና ለመጠበቅ እና የትምባሆ ተጠቃሚነትን ለመቀነስ የሚደረገው የቁጥጥር አካል መሆኑ ተገልጿል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ቅጣቱ የሚተገበረው በከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ነው።

ደንቡ የትምባሆ ምርቶችን አጠቃቀም ለመቆጣጠርና ከጭስ ነፃ የሆነ የከተማ አካባቢን ለመፍጠር የወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ 79 በመቶ የሚሆኑት የህዝብ መገልገያ ተቋማት ከጭስ ነፃ መሆናቸውን ገልጿል።በከተማዋ የአጫሾች መጠን ከ5.3 በመቶ ወደ 4.6 በመቶ መቀነሱን በመግለጽ እየተወሰዱ ያሉ የቁጥጥርና የግንዛቤ ማስጨበጫ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን አመልክቷል።

Via በሳምራዊት ስዩም
©️ዳጉ_ጆርናል
🤝ጉርሻ Page


@nahome93
3
በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ ይሆናል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ ይደርጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፈተናውን በአጭር ጊዜ አርሞ ይፋ ማድረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንደሚያስችል ገልጿል፡፡

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናው ከሰኔ 8 -10 /2018 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 199 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት መሰጠቱን ትምህርት ቢሮው ባወጣው መረጃ አስታውሷል፡፡

Via AMN


@nahome93
2