የነፍሴን ጩኸት በስንኝ
38 subscribers
14 photos
1 video
5 links
ፍቅር
ኑሮ
ሀገር
እምነት
እውቀት
ህይወት
ጥላቻ
*
*
*
በወዛም ስንኞች
ለእይታዋቻቹ ለአስተያየታቹ እንዲሁም ፅሁፎቻችሁን እና ግጥሞቻችሁን ለመላክ
@kingofmoriyam
Download Telegram
ምን አለበት እቱ
ጥልጥል እንዳለችው
እንዳጭሯ #ቦዲሽ
ክፋትና ንቀት አልዳረስ ብሎ
ልክሽ አልሆን ቢልሽ
፨፨፨፨፨፨፨
ምን አለበት እቱ
በሰውነትሽ ልክ ጥብቅብቅ እንዳለው
እንደ #ሀይዌስት ሱሪሽ
ፍቅር ሙጥኝ ብሎ
አልላቀቅ ቢልሽ
፨፨፨፨፨፨፨
ምን አለበት እቱ
ወገብሽ ጋ እንዳለው
እንደ #ሁማንሄርሽ
ወይም ደሞ
እንደተቀጠለው እንደ ረዥሙ ፀጉርሽ
ደግነትሽ በዝቶ ከሰዎች ቢያበልጥሽ
፨፨፨፨፨፨፨
ምን አለበት እቱ
ትልቅ #ሂል እንዳለው እንደ ታኮ ጭማሽ
መልካም ስራ ሰርተሽ አለም እላይ ሰቅሎ ዘወትር ቢጠራሽ።
፨፨፨፨፨፨፨
ምን አለበት እቱ
ያንቺ እንደማይመስለው እንደ #ክፍቱ እምብርትሽ
ማሰብ ማስተዋልሽ ስጋ ሳይሸፍነው ወቶ ቢታይልሽ
፨፨፨፨፨፨፨
ምን አለበት እቱ
እንደ መስታወቱ ፊትሽ አስር ጊዜ
ምነው ብታቆሚኝ
ከዛም ጠጋ ብለሽ እንዴት ነኝ
ብትይኝ






እነግርሽ ነበረ አወጋሽ ነበረ ከመስታወት በላይ
በገላ መሽሞንሞን ውስጥ እንደማይታይ



ቅዱስ በላይነህ
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
#የሽቅብ_እይታ
አንቺ እላይ ወተሽ እኔ ታች ወርጄ
እንዳልመጣ ደጅሽ እርቆ ከደጄ
እኔ ላይ ወጥቼ አንቺ ታች ስትወርጂ
እኔና ቤትሽን በድንገት ብታጪ
አደራ እንዳታዝኚ ኋላ እንዳትቆጪ
የኔን ልብ እንደጣልሽ ያንቺን እንዳታጪ
ቅዱስ በላይነህ
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
#እኔና_ሀገሬ
ብዙሀኑ አቅልለው ከበታች የጣሉን
ከራብተኞች ተርታ ከስር የመደቡን
እኔና ሀገሬ
ተጥለን ያልወደቅን
ተገፍተን ያራቅን
በትላንት ታንፀን ነገን የወጠንን
እኔና ሀገሬ ነን
ከላይ እይታችን የደሀ ቢመስልም
ጥቁር በሚል ቀለም ክብራችን ቢቀልም
በጎጠኞች አፍ ግን ተንቀን አንቀርም

ቅዱስ በላይነህ
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
የጥበብ ስብስብ @yetbebsibsb አጠር አጠር ያሉ ግጥሞች እንዲሁም ስዕሎችና የተለያዩ ፅሁፎች በቻናላችን ይገኛሉ @yetbebsibsb አሁኑኑ ይህንን link በመጫን አባል ሆነው ይከታተሉን እንዲሁም ደግሞ የተለያዩ ሀሳቦችን ለመሰንዘር፣አስታየት ለመስጠት በተጨማሪም አብሮ ለመስራት እምትፈልጉ @kidus_belayneh ይህንን username በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን መሰንዘር ይችላሉ በምርጫዎ ይቀላቀሉን
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
yetbebsibsb
Forwarded from የጥበብ ስብስብ (ቅዱስ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ አቤል ፀጋዬ @abeltsgaye
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebesibsb ፎቶአቹ እግዲሳልላችሁ የምትፈልጉ @abeltsgaye ወይም @kidus_belayneh ላይ ይላኩልን
Forwarded from የጥበብ ስብስብ (ቅዱስ)
#ዘመን

መኖር ባለመኖር
መሆን ባለመሆን
ሲታካ ቆይቶ
የሀጥያት ወራሽ ሞትን
እስከመች ተፈርቶ


የእውነት ተባርካ ተሰታን ምድሪቱ
የውሸት እየኖርን ቢበዛ መዐቱ
ክደን ዋሽተን ሽጠን
ከሀብቱ ጣራ ላይ ካናት ተቆልለን
ፀሎታችን እንኳ አልሰማ ሲለን

መች ታውቆን መች ገብቶን
ሁሉ አልሆን ማለቱ
ደግ ሲሉት ክፉ ቅራኔ መብዛቱ
የስጋችን ርክሰት መዐት መሸመቱ

ቅዱስ በላይነህ

መረዳት በምትፈልጉበት መንገድ ሳይሆን መልካም በሆነው መንገድ አንብባችሁ ብትረዱልኝ ደስ ይለኛል ለሀሳብ አስተያየት @kidus_belayneh

@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
Forwarded from የጥበብ ስብስብ (ቅዱስ)
የጥበብ ስብስብ @yetbebsibsb አጠር አጠር ያሉ ግጥሞች እንዲሁም ስዕሎችና የተለያዩ ፅሁፎች በቻናላችን ይገኛሉ @yetbebsibsb አሁኑኑ ይህንን link በመጫን አባል ሆነው ይከታተሉን እንዲሁም ደግሞ የተለያዩ ሀሳቦችን ለመሰንዘር፣አስታየት ለመስጠት በተጨማሪም አብሮ ለመስራት እምትፈልጉ @kidus_belayneh ይህንን username በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን መሰንዘር ይችላሉ በምርጫዎ ይቀላቀሉን
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
yetbebsibsb
ስንፈተ ትውልድ

የመኖር ትርጉሙ ጭራሽ የጠፋበት
ክብር የሚለው ቃል ስህተት የሆንበት
ለቁራሽ እንጀራ ለሽራፊ ዳቦ ለእጥፍጣፊ ወጥ
ማንነት እውነቱን እምነቱ ና ክብሩን ለመለወጥ
የማይደራደር የማይልመጠመጥ
ትውልድ ሲፈጠር
በሀገርህ መኖር እፍረት ይሆንና
ኩራት እንደ እራት መሆኑ ይቀርና
ተረግጠህ መብላትህ ያስብልሀል ጀግና

🙏🙏🙏🙏🙏 መልካም የኩራት ቀን እና ምሽት ይሁንላቹ
ሌሎች የምንነጋገራቸው ነገሮች ቢኖሩም መልካም ቀን

ናብሊስ
እይታ

እዮሀ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መስከረም ሲጠባ
ወደ ሀገሬ ልግባ

ሐሜት ባይሆንብኝ ስር የሌለው ወሬ
መኖርን እሻለው እኔስ በሀገሬ

እኔን የገረመኝ
በዚህች ሀገር ውስጥ ሰርክ የሚለፈለፍ
መስከረም በጠባ በወራቱ ግዜ ሁሌ የሚለፈፍ
ይህ መዝሙር መልክቱ በሌላ ስናየው
ብዙ ያልተመለሰ ግዙፍ ጥያቄ አለው

ለምሳሌ
አንድ ሀገር ላይ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልግባ ምን አይነት ፈሊጥ ነው
አንድ ሀገር ውስጥ
ሆኖ ወደ ሀገሬ ልሂድ ማለትስ ምንድነው
አንዳች ነገር ባይኖር ድብቅ ሴራ ነገር
ባለ ሀገሩ ህዝቤ እንዲህ አይልም ነበር

በዛኛው ጫፍ ሆነን ነገሩን ስናየው
ግጥሙ ሲገጠም
ስንኝ ሲደረደር ክልል እና ብሄር አለ እንደማለት ነው
አለበለዚያ ግን
ገጣሚው ሰውዬ
ወይ ይጠነቁላል ወይ ነብይ ነበር ብሎ መመስከር ነው


መልካም አዲስ አመት
ናብሊስ
@nablis12
@nablis12
@nablis12
@nablis12
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
ለሀገሬ ለዕንቁጣጣሽ የተላከ ደብዳቤ

እንዴት ነሽ ሀገሬ
እንደምነሽ ኢትዮጵ
እኔ አለው በደህና
ጤና ብትነሺኝም ሰላም ይስጥሽና
ለወቀሳ ያብቃሽ ድነሽ ተነሺና
እንደው ግን ሀገሬ ኑሮ እንዴት ይዞሻል
ድሮም እንዳሁኑ ይበጠብጡሻል
በፊት እንደዛሬ ብርሀን ናፍቆሽ ያውቃል
ሁሌ ብርሃን ነበር ወይስ ነው ጨለማ
ራቅ ላለ ሀገር ደምቆ የሚሰማ
ሀሳብ ነበረሽ ወይ ህዝብ ኖሮሽ ያውቃል
ይሄን ግን መጠየቅ እጅግ ያሳፍራል

ቢሆንም ቢሆንም ግድ የለም መልሺ
ወሎ አድሮ ደግሞ ከሌሎቹ ጋራ እኔን ከምቶቅሺ
ገድ የለም መልሺ
ዳቦ በሌለበት የኩራት ጎህ ብለሽ ቀን ትሰይሚያለሽ
ሰላም በሌለበት የሰላም ቀን እያልሽ ትደሰኩሪያለሽ
በወደቀች ሀገር የብልፅግና ቀን ታስከብሪናለሽ
ፍቅር በጠፋበት የፍቅር ቀን አያልሽ ታስጎመጂናለሽ
ፍትህ ባልኖረበት የፍትህ ዕለት ብለሽ ታስቀጥፊናለሽ

ሁሉም ቀናቶችሽ በሌሉ ነገሮች እየተሰየሙ
ልብን ያደማሉ ሀሳብ ያጠፋሉ ደዌ ያፈጥናሉ
ለኑሮ ታጋዩን ተስፋ ያሳጣሉ
እምነት ያስክዳሉ ውሸት አስወድደው ግፍ ያስለምዳሉ

አና እንዴት ነሽልሽ
ጤና እንዴት ይዞሻል
ዛሬም እንዳማረርሽ ይመሻል ይነጋል
እኔ ግን የምልሽ
መሪ ግን አለሽ ወይ
መሪው እንኳን ተይ
አትንገሪኝ በቃ ፓለቲካ ብለው እንዳይጠፈንጉኝ
አይኔን ባይኔ ሳላይ ዘሬን እንዳይቀሙኝ
ስለ መሪ ማጣት ተይው እንዳትነግሪኝ

አነማ

አነማ ነው ያልሽው
አንቺ ምን አለብሽ ኔትወርኩ ነው መሰል መረጃ አይደርስሽ
ኢሜልሽ አይሰራ ያስቸግራል ስልክሽ
ኦላይን የለሽም ችግር ላለመስማት
ፌስብክ ላይ አትኖሪ ሰውን ላለማማት
ታዲያ እንዴት ልንገርሽ
እኔ ግን ሀገሬ በጣም ስላዘንኩኝ
ነፍሴን የሚያሳጣ ሚስጥሬን ልነግርሽ ሰሞኑን ወሰንኩኝ

ምን መሠለሽ እሱ
በአሁኑ ሰአት ላይ የሚመራሽ የለም
መሪ የሚባል እንጂ መሪ ልጅ የለሽም
ሳትሞቺ ተስካርሽ በቁምሽ ሲበላ
ለሰማኒያሽ እንጃ ለአርባሽ መቶ ሰው በቁሙ ሲቀላ
ወዳንቺ እያየው አለሁኝ ከኀላ
ምክንያቱም
እንደ ሀገሬ ሰው እሬሳን አልወቅስም በሚለው በሀሉ
ለወዳጁም ሆነ ለመሠሪው ጎዱ እንሚለው ሁሉ
ሀገሬ ጥሩ ናት ሞትማ ቀደማት
ለስንቱ መዳኒት ለስንቱ ሸማ ናት
ብዬ ልፅፍልሽ ኀላሽ ሆኛለው
ህዝብሽን ስኮንን አቺን ደሞ ስረግም ይኸው እኖራለው

ሀገሬ አንደምነሽ
ህመሙ እንዴት ነው ዛሬስ ተሽሎሻል
ወይስ እንደ ድሮው ያቅለሸልሽሻል
ሆስፒታሉ እንዴት ነው
የህዝቦችሽ ጋር ነሽ ወይስ የግል ነው

እንደዛ ከሆነ

ዶክተሮቹ አሉ
በሰርጀሪ ግዜ ድንጋይ ኮብልስቶን ሆድሽ ውስጥ አረሱም
ለራስ ምታት ህመም ሽንት እና ሰገራ ምርመራ አልጠየቁም
ደምሽን ለመቅዳት ሀያ ስምንት ግዜ ደግመው አሎጉሽም

የውልሻ እኔ የልብ አውቃ ልጅሽ እንዲ ነኝ እወቂ
ህዝብሽ ይሰቃያል እንትና ይጨፍራል አንቺ ስትማቅቂ

እኔ ግን የምልሽ
ሽንት ቤቱ እንዴት ነው
ዛሬም እንደድሮው እንደነበረ ነው
የትም አትሂጂ ህዝብሽን ለማየት
መፀዳጃ ይበቃል ምሁር ለመለየት

እሱን ተይውና
ነርሶቹ እንዴት ናቸው
እንዴት አየሻቸው
ከዶክተሩ ናቸው ልባቸው ከማነው
ወይስ ካንቺ አሉ እንዴት ገመትሻቸው


አረ ሳልጠይቅሽ
እንዴት ልትገቢ ቻልሽ ዘበኛውን አልፈሽ
ወይስ እንደ ሰው ጉቦ መስጠት ለመድሽ

ጉቦ ይሰጣል ወይ

ህዝብሽ ተበሻቅጦ ያለ እጅ መንሻ የተሰራለት ለት
ስራውን አያምንም ጉቦ ካልሰጠበት

እንደው ግን እምዬ
አልጋ ከየት አገኘሽ
ወይስ እንደነሱ አንዱ ላይ ተደረብሽ
ወይስ እንደነዛ በጉልበት አስለቀቅሽ

ወንበር ላይ ነኝ አልሽኝ

ምነው እናት አለም የሚረዳሽ የለም
ዘመድ አልባ ነሽ ወይ ዘበኛው ዘመድሽ ይህንን አላየም

አሱ ምን ያረጋል ምንስ አቅም አለው
ምስኪን ተቀጣሪ ደህና ገንዘብ የለው

እሱን እንኳን ተይው
ከዳክተሩ በላይ ሆስፒታሉን የያዘው እሱ ነው ሚመስለው
ስትደመር ሚስቱ ያቺ ፅዳቱዋ ልጅ
ከተጣሉሽማ እንኳንስ ወንበሯን አትገቢም ከደጅ

እንዴት ነሽ አለሜ
እኔ አለው በጤና
ያው ታምሜም ቢሆን እግዜር ይመስገን ነው እኖራለው ደህና
የሸክላ በርበሬ በጀሶ እንጀራ አጥቅሼ
ዲታ የሆንኩ ቀን አህያ ቀምሼ
ባለ ብሩን ዳቦ አምስት ብር ገዝቼ
በ ሶስት ሺህ ብሬ ነጭ ጤፍ ሸምቼ
አለውኝ በደህና
ጤና ብትነሺኝም ሰላም ይስጥሽና
ለወቀሳ ያብቃኝ ድነሽ ተነሽና
እስከዛው ግን ቆይኝ
በአዲስ አመት ዜማ ባደይ ተንቆጥቁጠሽ
አዲስ ሳይፈጠር እድሜሽ ላይ ጨምረሽ
ግቡን የማይመታ ልጥጥ ስራ አቅደሽ
ልጆችሽን ማሰር ትውልድሽን መቅበር በደንብ ተምረሽ
ከብረሽ ቆይኝ ከብረሽ

ናብሊስ
መልካም እንቁጣጣሽ
ለ አስተያየቶ @kINGOFMORIYAM

@getem
@getem
@getem
Forwarded from ግጥም 🇪🇹
🌼🌼ፈጣሪ በአዲሱ አመት🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ታሞ ከመማቀቅ፣
በብድር ከመሳቀቅ፣
ተፈትኖ ከመዉደቅ፣
የምንወዳትን ቺክ ከመነጠቅ፣
ይሰዉረን !
🌼
ከሰዉነት አንሶ እንስሳ ከማከል፣
የራስ እያረረ የሰዉ ከማማሰል፣
ለዘር ለጎጠኝነት ዱላ ከማቀበል፣
በቸልተኝነት ጉዞ ሚስኪኑን ከመበደል፣
ይሰዉረን !!
🌼
ፈገግ ብለዉ ከሚገሉን፣
ጀነን ብለዉ ከሚያዋርዱን፣
ደንዘዉ ከሚያደነቁሩን፣
እሱ ይሰዉረን! 🙏
🌼
ሀብታም ሆኖ ሰገጤ፣
ድሃ ሆኖ አራዳ፣
አዕምሮ ይዞ ዘረኛ፣
ሀብት ይዞ ጎጠኛ፣
ከመሆን ይሰዉረን!! 🙏
🌼
ከባለሃብት ቋጣሪ፣
ከእነቅልፋም ታታሪ፣
ከበጥባጭ መሪ፣
ከወንድ ፈሪ፣
ከሴት አስነዋሪ፣
ይሰዉረን! 🙏
🌼
ከመሪ ሸረኛ፣
ከሴት ነገረኛ፣
ከወንድ ጉረኛ፣
ከማህፀን በረኛ፣
ይሰዉረን! 🙏

#መልካም_አዲስ_አመት
ሳምሶን
@kidapoim
@kidapoim
@kidapoim
@kidapoim
ስላንቺ ስቀኝ ስላኝቺ ስፅፍ
ስረግጥ የውበትሽን ፅንፍ
ስቀርብ ለደጃፍሽ ስዘምር ለክብርሽ
ሳረግድ ለገላሽ ዛዜም ለከንፈርሽ
ስጭር ስለፊትሽ

ስውር ውበትሽን ሸራ ላይ ሳሰፍረው
ስድስት መቶ ሉክ ላይ ጠርዤ ሳቀርበው

የውበትሽን ልክ
ልፅፍልሽ ሳስብ
ልስልለሽ ሳስብ

ሌሎቹ እንዳሉት
ፀሀይ አትመጣም በሀሳቤ
ጨረቃን ይጠላል ቀልቤ

ስለ ድምፅሽ ደሞ
መላዕክትን አንጃ ምንም ናቸው ወፎች
የሰርግ ለት ማታ ሟርት ሙሾ አውራጆች

ለጥርስሽ መፍካቱ ሲደመር ንጣቱ
አይስተካከልም አይመጣም ልኬቱ
ልክ አይሆንም ንፅሩ
ጎዶሎዋች ናቸው መላ ከዋክብቱ

መቀነትሽ መብረቅ ሻሽሽ ነው ደመና
ብዬም አልልሽም ይሆናሉ መና
ብልጭታና ዝናብ አይገልፁሽምና

ለጠረንሽ ምሳሌ
አልገባም ቤተስኪያን አልሄድ ቤተ ቅኔ
አልገዛ ሉባንጃ አልቀጥፍም አሪቲ
አላጨስም ዕጣን አልቆርጥም አሽኩቲ

የፀጉርሽ ማማር በሀር አይለካም
ዘንፋላ ጎፈር ስፍሩን አይሞላም

ስለ ፍቅርሽማ ሰለ መውደድሽ ጥግ
ምን ስንኝ ቢሰናኝ ምን ቃላት ቢፋተግ
አይደርስም ከጫፍሽ አይመጣም ዉጤትሽ
ሲደመር ቢባዛ አይደርስም ደጃፍሽ

ታስፈልገኛለች መዳኒቴ እሱዋ ናት
ኑራ ምታኖረኝ ሞቼም የማነግሳት
ብዬ ለመናገር
እያልኩ ለመመስከር
እልም ከለ ሜዳ ጭው ከለ በረሀ
መካከል ላይሳይደርስ
ምግብ ላስፈለገው ለተጠማ ውሀ
ከሰማይ የሚወርድ መና ብዬ ብልሽ
በቃ አይሆንልኝም አይመጣም ልኬትሽ

እንደውም ልንገርሽ
ቃል አጠረኝ ብዬ ቃል ሰጥቼ አላልፍም
ልገልፅሽ ካልቻልኩም እንደውም አልፅፍም
መናገር አቃተኝ ፍቅርሽ አፍኞኛል
ቃላት በሞሉባት ቃላቶች ያጥሩኛል
ስላንቺ ምፅፍ ቀን ብዕሬ ይለግማል
ፊደሎች ታመሙ ቅብርጥሴ ብዬ
ወዳንቺ አልቀርብም ክብርሽን ደጅ ጥዬ

እና እኔ ስፅፍሽ
እና እኔ ስስልሽ
ትርጉምሽን ውጪ ጭራሽ አላስብም
ሰማይ አልቧጥጥም ምድርን አልቆፍርም
ለገዛ ውበትሽ ምሳሌ አልሻም ንፅር አልፈልግም
እራስሽን ፅፌ እራስሽን ስዬ እራስሽን ግጥም

ናብሊስ ነኝ
ለአስተያየቶ @kingofmoriyam
#ሳስበው

ልብማ ነበረን ሀያል የነበረ
አሁን ስለጣልነው ነበር ሆኖ ቀረ

በዘመን መሰልጠን ማንነት ተጥሎ
ባህል ቅርስና እምነት
የኋላ ተንጋሎ
ሀገር ትንሽ ሆነች ህዝቧ ብዙ ሆኖ

ቅዱስ በላይነህ
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
@yetbebsibsb
ኖርማል ነው እራሱ ኖርማል ነው ወይ??????????

ኖርማል ነው ብለን ኖርማል ስላረግናቸው ኖርማል ያልሆኑ ነገሮች ነው ዛሬ የማወራው ማለቴ የምፅፈው
ምን ሊል ነው ምናምን ልትል ትችላለህ አያገባኝም
የማውቀውን ነው የሚፅፈው ልትል ትችላለህ አይገርመኝም
ግን ልብ ብለኸው ካልሆነ ብታነበው ባይጠቅምህም አይጎዳህም
ኖርማል ነው
የአለማችን አስጠሊ አባባል ማነው አለምን መች አየው አፉ በሉኝ የሀገራችን መጥፎ አባባል ምናልባት ኖርማል የሚለው ከእንግሊዘኛ የተዘረፈው ቃል ሌላ ትርጉም ያለው መስሎንም ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለው (እራስን ማፅናናት ይሉታል ይሄ ነው)እዚህ ሀገር ኖርማል የሆኑ ነገሮች በዝተዋል በኢኮኖሚው ዘርፍ በፖለቲካው አቅጣጫ በስራዎች አከባቢ ብቻ በሁሉም ዘርፍ ኖርማል ነው የሚሉት ጤነኛ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን ለሞት እያጣጣረ ያለ አባባል መስማት ለጆሮ አዲስ አደለም ወደ ፊትም አዲስ ይሆናል ብለን አንጠብቅም ይሄ ፅሁፍም ብዙ ሰው ይለውጣል ብዬ አላስብም እንዲው ብያለው ለማለትም ይሆናል የተፃፈው ወይም ደግሞ እስቲ እዝች መሀበራዊ ሚዲያ ላይ ያው (የሚያነብ ከተገኘ) ትንሽ ላይክ እና ኦው ልክ ነው ድንቅ ሀሳብ የሚሉ እና የመሳሰሉ ኮሜንቶችን ለማግኘትም ይሆናል
ብቻ ኖርማል ነው የምንላቸው ነገሮች ከመብዛታቸው ኖርማል ያልሆነ ነገር የሌለ ነው የሚመስለው ሁሉ ትክክል ሁሉ ሸጋ ሁሉ መልካም እንዳለ ጥሩ የሆነ ነው የሚያስመስለው አነጋገራችን
አንድ የእስማርት ፎን ተጠቃሚ የሆነ ልጅ ስልክ ውስጥ 400 እራቁት ቀረሽ የሙዚቃ ማለቴ የብልግና ቪዲዮዎች ማስተማር አደለም ብልግናን ማሳየት አደለም ብልግናን የማበረታታት አጀንዳ ያላቸው ዘፈኖች (ከባህል ውጭ ብቻ አደለም ከሰውነት ውጭ የሆኑ )ሲገኙ ኖርማል ነው
ኔት ወርክ በማይሰራባት ሀገር መብራት በሌለባት ምድር sex የሚለው ቃል ወደ መረጃ መሰብሰቢያው የተላከው እዚው ሀገራችን ውስጥ ነው ሲባል ኖርማል ነው
የ10 አመት ልጅ ስልክ ሲሰጠው ኖርማል ነው (የሚያረግበት እየታወቀ)
አብዛኞቻችን ስልክ ውስጥ sex video በብዛት እየተገኘ (ለዚያውም ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳይ )ከኖርማል sexual inter corse የወጡ አካሄዶችን በግልፅ የሚያሳይ የሚያስተምር ቪዲዮዎች ምስሎች ሲገኙ ኖርማል ነው
ውርስ (የወንድምን ሚስት ወንድሙ ሲሞት ማግባት )ኀላ ቀርነት ነው ብሎ የሚያስብ ትውልድ የሌላ ሰው ሚስት ሲያማግጥ የጓደኛውን ሚስት ሲቀማ የወንድሙን ሚስት በጎን ሲያስኮበልል የሰፈሩን ልጅ ለጎደኛው ሲሸጥ ኖርማል ነው
ክለብ ሲጠጣ አግኝቷት በአንድ ቀን አብሯት የተኛውን ልጅ ጀግና መጠጥ አትጠጪ ብጠጪም በልክ ብሎ የሚመክረውን ሰው ፋራ ማለት ኖርማል ነው
እራሷን በቴሌግራም የፎቶ ውድድር አንደኛ መሆን (እዚጋ ብትናደዱ አያገባኝም) በፌስብክ ላይክ በኢንስታግራም ፎሎወር ብዛት በቁንጅናዎ የምትለካ እራሷን እንደሸቀጥ የምታይ (እዚጋ እንደዚ አይነት ሴት ከሆናቹ ፅሁፉን ማንበብ ይብቃቹ ምክሬ ነው)ክብሯ የወረደ እውቀት የለሽ እምነት አልባ ሴቶች ሲታዩ ኖርማል ነው
እራሱን በለበሰው ልብስ ብራንድነት በያዘው ስልክ ማርክነት ባደረገው ጫማ ውድነት የሚለካ የአስተሳሰብ እከካም ወንድ ሲበዛ እውነተኛ ሲጠፋ ኖርማል ነው
እንድ ፎቶ መስክ ላይ የሚያነሳ ጓደኛህ ጋር ሆነህ ወይ እራስህ ፎቶ ግራፈር ሆነህ ገላዋን አደባባይ አስጥታ ዳሌዋን ጡቶቻን አጋልጣ ሰጥታህ ፎቶ ተነስታ እነ ፌስብክ መንደር ፎቶዎቿን ወርውራ አንድ ብር በማያወጣ ላይክ እራሷን የምትገምት እንከፍ ስትመጣ ስትኖር በራስ መተማመን ሳይገባት ስትነጥር ኖርማል ነው
በለከፏት ወንዶች አለባበስ በያዙት መኪና ውድነት ደረጃዎን የምትመድብ ጀረጃ አልባ ሴት ከተማው ውስጥ ማንገስ ኖርማል ነው
በገንዘቤ እገዛሻለው የትም ብትሄጂ ገንዘቤን ይጭነቀው የሚል እብቅ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው ስታይ ኖርማል ነው
በራሱ አስተሳሰብ ሳይሆን ውጪው በቀደደለት የሚራመድ ዘመናዊ ባርያ እዛ የተለበሰውን እዚ እሚያደርግ የራሱ ፊት አስጠልቶት ሲጋራ እያጨሱ በሀያ ሴት ተከበው የሚዘፍኑ ዘፋኞችን መልኩ የሚያደርግ የሚለጥፍ ሰው ስታይ ኖርማል ነው
እንከፍ እከካም አተላ የሆኑ አስተሳሰቦችን የሚያስብ የሚያካፍል ሰው ሴት ወንድ ሲታይ ኖርማል ነው
ኖርማል ነው
ኖርማል ነው
ኖርማል ነው
ኖርማል ያልሆነ ኖርማል ነው የሚል ኖርማል ምን እንደሆነ የማያውቅ አባባል ገና ኖርማል ነው ብሎ እየፈላ ያለ ዘይት ውስጥ ይጨምረናል ይጨምርሻል ይጨምርሀል
ለዛሬ አበቃው ይሄንንም ከጥቂት ሰዎች ውጪ የሚያነበው የለም ግን ይሄም ኖርማል ነው እንዳልል ኖርማል አደለም
በል አንብበህ ከጨረስክ አስተያየት ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ሀሳብህን ቁጭ አርግ ባይሆን ይህ ኖርማል ነው
በል በቃ ቻው አልልህ ነገር ገና ብዙ ያልጨረስነው ነገር አለ
ገና ያልዘጋነው
ገና
ገና
ስለዚህ እንቀጥላለን በል ብሀላ ሀ ብዬ ከምጀምር ከነበርንበት እንድንቀጥል ብዬ ሳልሰናበትህ ጨዋታዬን ማነው ፅሁፌን ሳልዘጋ ነው የሄድኩት
ገባህ ይሄም ኖርማል ነው
:
:
:
:
:
በል ግን አስከዛው ይቺን እያሰብክ ቡና ጠጣ ቡና መጠጣት ደሞ ሱስ ነው የሚሉ አሉ (እዚጋ በጣም ይሳቃል) ምክንያቱም ከቡና ሱስ በላይ የሚያሳስበን የኖርማል ነው ሱስ ነውና ቡናህን ዝም ብለህ ጨልጥ ሂሳብ እኔ ጋር ነው ደሞ የሰው ገንዘብ ነው ብለህ ጨጓራህ እስኪላጥ ተጋት አሉህ ደሞ

ለአስተያየቶ በሬ ክፍት ነው ማለቴ @kingofmoriyam ላይ አድርሱኝ
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (“ናካይታ” (Nagayta))
Nablis Derese:
እኔና-- ቤቴ

ያ ትንቡክብክ ገፅሽ
ያ ድንቡሽብሽ ፊትሽ -ውበቱ ቢከዳው ~ፈገግታው ቢያጥጥም
ያልባስጥሮስ ሽቶን
የወረሰው ገላሽ _በቡኩን መናኛ ~በቆሻሻ ሽታ ~መአዛው ቢፋቅም

ከጨረቃ ድምቀት
እጅግ የረቀቀ_ከነፋስ የራቀ~ ከዋክብቱን ሁላ- በግፍ ያደባየ
በነፋስ ውሽንፍር
በንዳድ ፀሀይም~ በቁሩም በብርዱም ~ውበቱ የታየ
ያ ቅኔ ውበትሽ-
መላእክትን ሁሉ- ከሰማይ መንቅሮ -ከመሬት ያቆየ

ከምድር ያዋደደ
ካፈር ያዋሀደ- በእቶን ያቃጠለ -ከህልም ያካካደ
የከበረ ገላን -
የተለየች ነፍስን- በልዩ ተአምር -ከሳት የማገደ
ያ ድንቁ ውበትሽ
ግዙፈ ግዙፋን < ረቂቃን-ነፍሶችሽ> መጋረፍ ቢያቆሙሙም
"እኔና ቤቴ ግን "አንቺን በመደገፍ -በፍፁም አናፍርም

በጊዜ አዙሪት-ሰከንዷ ብታረፍድ -ሰአቱ ቢደክምም
ፀሀይ ጠፈር ከድቷት -እመሬት ብትነድም
ባዘቶው ደመና- እንደ በጋ አበባ -ውበቱ ቢረግፍም
የውቅያኖስ ገላ- እንደ ጭንጫ መሬት -ውሀ ቢናፍቅም
"እኔና ቤቴ ግን"- አንቺን ከማፍቀር- ቦዝነን አናውቅም

አውቃለው ፍጡር ነሽ _ገብቶኛል ጌታሽ ነው _ግን የሆነው ሆኖ
ከሀያላን መዝገቡ -ከድኩማን ጦማር -በንፍገትሽ ብዛት -ጌታሽ ቢረሳሽም
ቁመተ ስጋሽ -ግዝፈተ ገላሽ -በድክመተ ነፍስሽ- ሳይሞት ቢገነዝም
ዝንት አለም ቢነፍዝም
" እኔና ቤቴ ግን "_ወድ አንችን ከመውደድ _ለቅፅበት አንሰንፍም

እኔ እና ቤቴ ግን እንወድሻለን
ንጉስ ደረሰ
@Kingofmoriyam

@getem
@getem
@getem
Forwarded from Deleted Account
@hasabnamuget
@hasabnamuget
@hasabnamuget

ሰላም ውድ ተከታታዮች፣ተሟጋቾች፣የሀሳብ ባለቤቶች እንዲሁም ታዳሚዎች

እነሆ ካቆምነው ብዙ ጊዜያት የሆነውን የሀሳብ ልውውጥ እና የሀሳብ ሙግት ልንቀጥል መሆኑን ከወዲሁ እያበሰርኳችሁ

ሰናዛሪዎች ያለችሁን እንካችሁ እንድትሉን ተሳታፊዎችም በብርቱ ለመሞገት እንድትታጠቁ አሳስባለው

ሙግታችን የደራ እንዲሆን ደግሞ
የግሩፓችንን ሊንክ ለብዙዎች በመላክ እንድትጋብዙ በትህትና ጠይቃለው።🙏
@hasabnamuget
@hasabnamuget
@hasabnamuget
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 17 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 10 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.