ፍቅር ሰባኪ TemUd
15.4K subscribers
1.4K photos
140 videos
1 file
6 links
❤️ልብን እንድታፈቅር ላደረገ ጌታ♡

♡ምስጋና የተጋባ ይሁን!!!

አሚን🙏

ለአስተያየታችሁ👉 @TemUd_Bot
Download Telegram
ጁምዐኩም ሙባረክ!💞

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ሰምታችኋል እንዴ! …

ወንድ ልጅ ከሚስቱ ከተፋታ በኋላ የድሮ ሚስቱ የበለጠ ዉብ ሆና ትታየዋለች አሉ፡፡ ወይኔ ምን ሆኜ ነው የፈታኋት እያለ እጁን ይበላል አሉ፡፡

ሴት ልጅ ደግሞ ከወንድ ልጅ ከተለያየች በኋላ ሲጀመር ምን ነክቶኝ ነው ይህን ጅል፣ ጅላጀል፣ ጅላንፎ ያገባሁት ብላ ብቻዋን ትስቃለች አሉ፡፡

የኔ ጥናት አይደለም፡፡

በጠዋቱ ፈገግ እንድትሉ ብዬ ነው፡፡😁
©️ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!

አላችሁ ወይ?👋
በብዙ ሀጃዎች ዉስጥ ገብተን ብንጠፋፋም አሁንም አለን ለማለት ያህል ነዉ።

እንደበፊቱ active ለመሆን ሞክራለሁ፤ እናንተም በዱዐችሁ አግዙኝ።

ጀዛኩሙላህ🤎

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
የአለም እዝነት፣ የህወታችን ተምሳሌት የሆኑት የእኛ ነቢ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ወቅት ለባለቤታቸው፦
''ኸድጃ ሆይ ድሃ ሆኜ አገባሁሽ፣ አላህ ደግሞ በአንቺ አከበረኝ'' ብለው ውለታዋን በፍቅር ነገሯት።

በነገራችን ላይ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ባለቤታቸው ከድጃ (ረ.ዐ) በህይወት እያሉ ተጨማሪ ሚስት አልነበራቸውም፣ ብዙ ልጅም የወለዱት ከኸድጃ (ረ.ዐ) ነው።

اللهم صل وسلم على نبينا محمد❤️

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
የቦታ ርቀት ሰዎችን አይለያይም
ዝምታ እንጂ!

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ከምንወደዉ ጋር ፣ የተወደደ ስፍራ ላይ

አላህ ይወፍቀን!🥺❤️
ጁምዐኩም ሙባረክ!🕌

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
«ሁለተኛ ሚስት ማግባት እፈልጋለው» አላት ምን እንደምታደርግ ማየት ፈልጎ !

የመጀመርያው ቀን ምንም ነገር አልታየውም

ሁለተኛውም ቀን ምንም ነገር አላየም !

ሶስተኛው ቀን ላይ ቀኝ አይኑ ትንሽ ትንሽ ማየት ጀመረ!

አንዳንድ መልሶች ላይታዩ ስለሚችሉ መልሱን ለማየት ብለህ ከምናደርጋቸው ድርጊቶች እንቆጠብ😂
©️fiyameta

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ድኻ አግብታ በረሀብ የሞተች ሴት ገጥማን አታውቅም። ሀብታም አግብተው በዙልም፣ በውርደትና በብስጭት የሞቱ ግን በርካታ ናቸው።

ስለዚህ ዲን እና ስነምግባር አይታችሁ አግቡ! ሁለቱ ገንዘብ በሌለበት ራሱ ሀብትን ያጎናፅፋሉ!
©️Tofik bahru

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
አንዱ ሁለተኛ ሚስት ያገባል።

የመጀመሪያው ሚስቱ እሱን እጅግ ከመንከባከቧ የተነሳ ሀብሀብ ስትሰጠው ፍሬዎቹን በሙሉ ለይታ አውጥታ ነው።

ሁለተኛዋ ደግሞ ዝምብላ ከተፍ ከተፍ አድርጋ ትሰጠዋለች። ከዚያ እሱም ፍሬውን እየተፋ እየበላ…

«ቱፍ ቱፍ… ሐስቢየሏህ… ያቺማ ይህን ፍሬ እንኳ ከልክላኝ ነበር እኮ»🤣🤣🤣🤣
©️

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
እስኪ አባቴን ዱዓ አስደርጋለው ብዬ አንድ ሱቅ ገብቼ ጀለቢያ እጠይቃለው
"3500" 👀😳

አላህ ይስጥልኝ ወንድሜ ዱዓው እንደሆን እጅም አስታጠብኩ ጀለቢያም ገዛው ያው "አላህ ሷሊህ ትዳር ይስጥሽ ነው" 🚶‍♀️🚶‍♀️

©️mari

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
#አወይ_ፍቅር...💚

ለመልዕክተኛውም ለሰሐቦችም ከባድ የነበረው ዘመቻ ላይ የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ለመከላከል ወደሳቸው የገሰገሰው ጠልሓ ነበር። እሳቸውን በመከላከል ከጎናቸው ጦርነትን መካፈልን የተጠማው ጠልሓ ኡሁድ ላይ ጀግንነቱን አሳየ! በሙሉ አካሉ መልዕክተኛውን ይከላከል ነበር። ሐቢበላህ ﷺ በተጣሩ ቁጥር ቶሎ የሚመልሰውና ካጠገባቸው የማይጠፋው ጠልሓ ነበር። መልዕክተኛውም ﷺ እንዲህ በማለት ስለ አፍቃሪያቸው ይናገራሉ: 💚

"لقد رأيتُني يومَ أُحُدٍ ، و ما في الأرضِ قُرْبِي مخلوقٌ ، غيرُ جبريلَ عن يميني ، وطلحةَ عن يَسَاري"

"የኡሁድ ወቅት እራሴን ተመለከትኩት ማንም ለኔ ቅርብ አልነበረም። በቀኜ ከነበረው ሰይዲና ጂብሪልና በግራዬ ከነበረው ጠልሓ በስተቀር።" ብለው ነበር ...🥹

ጠልሓ ወደሚወዳቸው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሚወረወሩትን እያንዳንዱን ቀስቶች በአንድ እጁ እየተከላከለ በአንድ እጁ ደግሞ በሰይፍ ይዋጋ ነበር። አስባቹታል? ህልም ይመስላል አይደል? ... አሁን ላለነው እኛ ፊልም የሚመስሉ ትዕይንቶችን መስማት እንግዳ ነው አይደል?

...የመልዕክተኛው አፍቃሪ ጠልሓ ቁስል ቁስል ላይ ተደራረበበት። እስከሚችለው አቅም ሐቢቢን ﷺ ተከላከለላቸው። የቆሰሉትን ሸፊዒ በቆሰለው ጀርባው ላይ ተሸክሞ ተጓዘ! እሳቸውን ማትረፍ ላይ ቁዋው መጣለት። ሙሉ ሰውነቱ ቁስል ብቻ የሆነው ጠልሓ የአለሙ መድህን የሆኑትን ውዱ ነብዩን ﷺ የነበሩበት ሁናቴ ዳግም ሩህ ዘራበት፤ እግሮቹ ተንቀሳቀሱለት። ተሸክሟቸውም ወደ ተራራው ወጣ! ይህንን ክስተት ከሩቅ የተመለከቱት አቡበክር አስሲዲቅ እና አቡ ኡበይዳ ኢብን አል ጀራህ መልዕክተኛው ﷺ እና ጠልሓ ወዳሉበት ገሰገሱ! 😢

ወደ ረሱል ﷺ ሲጠጉ ግን እሳቸው በደከመው አንደበት ወደ ጠልሓ እየጠቆሙ "እኔን ትታቹ ጓድ'ኣቹ ጋር ሂዱ!" አሏቸው። አባበክርም እንዲህ ይላሉ: "ጠልሓ'ን ስናየው ሙሉ ሰውነቱ ቁስል በቁስል ነበር። ከእያንዳንዱ ሰውነቱ ደም ይፈስ ነበር! ከቀስት፣ ከድንጋይ፣ ከጦር፣ ከጎራዴ ብዙ ቁስሎች አርፈውበት ነበር። እራሱንም ስቶ ከአፉም ደም እየተፋ ነበር።" ይላሉ አባበክር። ግን በህይወት ተርፎ ነበር። መልዕክተኛውም ﷺ በአፅዕኖት: "ጀነት ጠልሓ ላይ ዛሬ ወጅቦበታል!" አሉ። 😭... አወይ ፍቅር! መሐባ የማያደርገው የለም! የረሱለላህ ባልደረቦች የነበራቸው መስዋትዕነትና ፍቅር ደግሞ አይገለፅም! 💚

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድ!

ረሱሊ'ኮﷺ! ፍቅርዎ ሁሌም አዲስ ነው 💚💚
©️Nadia

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
አንዳንዴ የሚያስፈልግህ ዣንጥላ ☂️የሚሰጥህ ሰው ሳይሆን አብሮህ የሚበሰብስ ሰው ነው።
ስሜትን የመጋራት ሜዳ ከመስጠት ሜዳ ይበልጣል።💞
©️fuad

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
አንድ ወፍ አበባ ወደደ አሉ።
አበባዋ ነጭ ነበረች። "መልኬ ቀይ ሲሆን እኔም እወድሃለሁ አለችው።" አሉ።
ታድያ ወፉ ለወደዳት አበባ የትኛዉንም መስዋዕት ሊከፍል ዝግጁ እንደሆነ ሊያሳያት ወሰነ። ክንፉን ቆረጠና ደሙን አፈሰሰላት። አበባዋም ቀይ ሆነች።
አበባዋ ወፉ ምን ያህል እንደሚወዳት አወቀች።
ልትወደዉም ወሠነች።

ግና ጊዜው አልፎ ነበር። ዘገየ። ወፉ በፈሰሰው ደም ብዛት የተነሳ ሞቷል።
አብዝቶ ላሰበልህ አስብለት። ቦታ ለሠጠህም ቦታ ስጠው። የወደደህንም ሰው በፍቅሩ አታሹፍ ተረዳው።
በጣም የወደደህን ሰው ካጣህ እንደርሱ የሚወድህ ሰው መልሰህ አታገኝም እወቅ። የተሰበረ ቀልብ መልሶ አይጠገንምና።
©️ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
🥹❤️‍🩹

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
እጅህን ከያዝኩማ
….. አንተ ካለሀኝማ

መች ልለቅህ?
….መች ሊከፋኝ?❤️

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
እንዴት ቀጣሽዉ?

ሁሉንም ቦታ እመለከት ነበር …. ከእሱ ፊት በስተቀር

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ለምን ዓለምን አትመራም
ለምን ዱንያን አትገዛም
ለምን ሰባት ድግሪ አይኖራትም

"ሴት ልጅ ባል ከሌላት ሚስኪን ናት ሞገስ የላትም።" ይላሉ ዓኢድ አል-ቀርኒ
©️ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ከምንወደዉ ጋር ፣ የተወደደ ስፍራ ላይ

አላህ ይወፍቀን!🥺❤️
ጁምዐኩም ሙባረክ!🕌

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
ወዳጆች ሁሉ ለዚህ ታላቅ የረመዷን ወር ፆም እንኳን አደረሳችሁ ። ነገ ሰኞ የመጀመሪያ የፆም ቀናችን ይሆናል ። ዛሬ ተራዊሕ ይጀመራል ። መልካሙን ሁሉ ይወፍቀን።
©️ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል እሮብ ሚያዝያ 2 መሆኑ ተገልፆል::

ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 የረመዳን የመጨረሻው 30ኛ ቀን ሆኗል

አላህ ፆማችንን ይቀበለን!🌙

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd