Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
103K subscribers
19.8K photos
5.56K videos
304 files
6.46K links
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Download Telegram
ይህ ክስተት በመንግስት ቢሮ ውስጥ ነው‼️
=========================
||
ነገሩ እንዲህ ነው፦
ባለፈ በደቡብ ክልል የሐድያ ዞን አስተዳደሮች የዞኑን ህዝብ፤
በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን በማለት ህዝቡን ይሰበስቡታል።
እናም ከታች በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት፤
ሁሉም ባለ ስልታናት በያዙት ላፕቶፕ ጀርባ ላይ፤
«ኢየሱስ ጌታ ነው!» የሚል ስቲከር ለጥፈው፤
ህዝቡን በመንግስት ተቋም ውስጥ በይፋ የራሳቸውን እምነት እየጫኑበት ይገኛሉ።

የሚገርመው ነገር፤
በቅርቡ በእነዚህ ባለ ስልጣናት አማካኝነት፤
በሐድያ ዞን የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች፤
ሒጃባችሁን ካላወለቃችሁ ተብለው ከትምህርት ቤት መባረራቸው ነው።

ሴኩላሪዝም በሚቀነቀንባት ሃገር ነው ይህ ክስትተ የታዬው።
የሴኩላሪዝም ህጉ ከሠራ መሥራት የነበረበት፤
አእንዲህ አይነት ፓስተር ባለስልጣናት እንጅ እምነታቸው ያዘዛቸውን አለባበስ ጠብቀው በለበሱ ሙስሊም እንስቶች ላይ አልነበረም።

ወደዬት እየሄድን ነው⁉️
ቦታው ከመንግስት ተቋምነት ይልቅ በግልጽ የፕሮቴስታንት እምነት መስበኪያ መድረክ ነው የሆነው።



እንደት በመንግስት ተቋም ውስጥ ከአንደበት በዘለለ መልኩ በመድረክ ላይ እንዲህ አይነት መፈክር ይስተጋባል⁉️

እነዚህ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ባለ ስልታናት ስማቸው፤
አቶ በፍ ኤርሚያስና እሸቴ ሔኖክ ናቸው።

የሴኩላሪዝም ህጉ እውነት የሚሠራ ከሆነ፤
እነዚህን ግለሰቦችና አብረዋቸው የነበሩትንም ጭምር ከስልጣን ማስወገድ ግድ ይለዋል።

||
Cc:
====
SNNPRs Government Communication Affairs Bureau
||

t.me/MuradTadesse
በነገራችን ላይ ይሄ ደብዳቤ አያስቆጣም‼️
========================
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምቤት በጻፈው ደብዳቤ ላይ፤
የመስጅድ ካርታዎችንና ሌሎች የህዝብ ንብረቶችን የያዙ አካላት ወደ ምክር ቤቱ ይመልሱ ዘንድ ጥሪ አስተላልፏል።

ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው።

ወደ ክፍለ ከተማዎችም ወርደው በአንድ አንጃ ብቻ የተያዙ መስጅዶችንና በወያኔ የተሾሙ ኢማሞችን እንዲሁም የመስጅድ ኮሚቴዎችንና አመራሮችን፤
በተሻሉ ሰዎች መተካት አለበት።
ብዙ መስጅዶች ከመስጅድነት ሚና ይልቅ የጫት መቃሚና መጨፈሪያ እንዲሁም የግለሰብ ቤት ሁነዋል።
ስለዚህ ለህዝቡ መመለስ አለባቸው።
ከፊል ግለሰቦች ደግሞ የመስጅዱን ቅጥር ግቢ መሬት ሸንሽነው እየሸጡ ኪሳቸውን ለማድለብና ቡድናቸውን ለመርዳት እያዋሉት ስለሆነ፤
የሚመለከተው የመጅሊስ አካል ሊረከባቸውና በአግባቡ ሊያስተዳድር ይገባል።

በዚህ ደብዳቤ የተቆጡ አካላት፤
እጃቸው መዝረፍ የለመደ መሆኑን ያሳብቅባቸዋል።
ጥፋት የሌለበት ንጹህ ሰው፤ አዎ ይመለስ ይላል እንጅ በዚህ ሊቆጣ አይገባውም።
*
ሲጀመር በዚህ ደብዳቤ እነማን እንደሚቆጡ አስቀድሞ መገመት አይከብድም።
የተቆጣ ይቆጣ እንጅ የህዝብ ንብረት ለህዝብ መመለሱ አይቀርም።
እንዳውም ከተቻለ፤
አሁን ላይ ይህን ካርታውንና ንብረቱን ከመመለስም ባሻገር፤
በፊት የዘረፉትንም ሒሳብ ቢያወራርዱ መልካም ነው።
የበፊቱን አወራርዱ ከተባሉ፤ ሲጨንቃቸው ያንን አውፍ ብሎ አሁን ላይ ያለውን ማትረፍ ይሻላል።
መጮኻቸው ካልቀረ፤
ጥያቄውን ማክበድ ነው።

ኸላስ!!
||
t.me/MuradTadesse
የኡስታዝ ሱለይማን ዐብደል'ሏህ የቴሌግራም ቻነል‼️
=======================================
በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደል'ሏህ እውቅና አዲስ የቴሌግራም ቻነል ተከፍቷል።
በቻናሉ ላይ የኡስታዙ ትምህርቶችና አጫጭር መጣጥፎች ይቀርቡበታል።
እርስዎች ወደ ቻናሉ በመቀላቀል ቤተሰብ ሁነው ከኡስታዙ ትምህርት ይጠቀሙ።
ለሌሎችም በመጠቆም ወደ መልካም ነገር ያመላክቱ።
*
ኡስታዝ ሱለይማን ዐብደል'ሏህ በተለይ ለሙስሊም ሴቶች በሚያስተላልፋቸው ልባዊ ምክሮቹና መሳጭ ተግሳጾቹ ይታወቃል።
በተለይ እህቶች ብትቀላቀሉት ብዙ ጥቅሞችን እንደምታገኙበት አምናለሁ።
||
Join: t.me/UstazSuleiman
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ያሳዝናል‼
=======================
ከውጭ በሙስሊም ጠል ጽንፈኞች ጦር ይሰበቅበታል።
ከውስጥ ደግሞ በአሕባሾችና በሱፍዮች ማዕበል ይናጣል።
↓
ታዲያ ከየትኛው ጠላት ጋር እንዋጋ?!
ከውስጡ ወይስ ከውጩ?!
★
የሁለቱም ዛቻና ፉከራ አልተቻለም።
♠
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ትክክለኛ አንድነት ፈጥሮ የውጭ ጠላቱን የሴራ ድግስ ማምከን ሲገባው፤ ያለውን ኃይልና ጊዜ እነርሱ ላይ እንዲያደርግ አሕባሾችና ሱፍዮች የቋንጃ ቁስል ሁነው እየበጠበጡት ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ‼️
==============
በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ መደብ ጉብዳ ቀበሌ መሎ ሐሙሲት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤
ሙስሊም ተማሪዎችን "የሙስሊም ስማችሁን ቀይሩ!"፣
"ሒጃብ ማድረግ ክልክል ነው!" በማለት ተማሪዎቹን የሚያሰቃዩት ር/መምህር አቶ ደሴ እና ምክትል ር/መምህር አቶ መሰረት ላይ የወረዳው ት/ት ቢሮ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው በማድረግ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
እናመሰግናለን!
*
ነገር ግን ሰዎቹ በህግ እንዲጠየቁ እና ከቦታው ተነስተው በምትኩ አንድነት እና የኃይማኖት መቻቻልን ባህል ያደረጉ ለቦታው ሚመጥኑ ሰዎች እንዲሆኑ እንጠይቃለን!!
*
መቼም የኛ ነገር ሁልጊዜ ዋይታ ነው።
መብታችንን ይቀሙናል፤ አልቅሰንም ቢሆን እናስመልሳለን።
ሙስሊሙ አንድ ከሆነ መብት ከመጠየቅ አልፎ ለሌሎችም መብት ሰጪ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።
*
በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ለማሸማቀቅ፤
ሒጃባቸው ተገፎ የጥቁር ሰሌዳ (Black Board) ማጥፊያ (ዳስተር) እየተደረገ ይሳለቁባቸው ነበር።
እጅግ ዘግናኝ በደል ነበር።
የወረዳውና የዞኑ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ሌሎች በቦታው ላይ የሚመለከታቸው አካላት፤
ትክክለኛ ፍትሕ መስጠት ከፈለጉ ይህን እኩይ ሥራ ለሰሩት ግለሰቦች ከባድ ማስጠንቀቂያ መስጠት ብቻ ሳይሆን ከናካቴው ከሥራ ሊያግዷቸው ይገባል።

አለበለዚያ ግን ነገም ማስጠንቀቂያ እንጅ ሌላ የሚመጣ ነገር አይኖርም በሚል እሳቤ ወይ ራሳቸው ይህን ሥራቸውን ጊዜ ጠብቀው ይደግሙታል፤ አሊያም ሌላው የነርሱ አምሳያ በዚሁ ቦታና በሌላውም ቦታ ሊደግመው ይችላል።
||
t.me/MuradTadesse
አትሳቁብኝና...‼️
=============

"ሪያዹ-ስ-ሷሊሒን" ኪታብ በመጠኑም ቢሆን በአማርኛ ከመተርጎሙ በፊት፤
ተብሊጞች የሚጠቀሙት ኪታብ ምንድን ነበር⁉️

በፊት ክፍለ ሃገር ኪታብ ላይ ስማቸውንና መገለጫቸውን እንጅ "ተብሊጝ" የሚባል አንጃ በአካል አላውቅም።
እዚህ አዲስ አበባ ግን ጥቂት በማይባሉ መስጅዶች ውስጥ በብዛት ጥግ ይዘው ታገኛቸዋለህ።
ታዲያ ብዙ ጊዜ ያቺኑ በአማርኛ የተጻፈች ሪያዽ ይዘው አንድ ሐዲሥ ሁለት ጊዜ አንብበው ትንሽ መሹራ ብለው ሲለያዩ አያለሁ።

ብዙ መስጅዶች ላይ ደግሞ እንኳን ዐረብኛው አማርኛውንም ማንበብ ከብዷቸው፤ ከነ ትርጉሙ ብልሽትሽት አድርገውት ይሄዳሉ።

በጣም ነው የሚገርሙኝ።
አንዳንዶቹ ከየዋህነታቸው ጥግ አንጻር ኢኽላስ ያላቸው ይመስላሉ።
ሁላቸውም ግን በሙታበዓ ጉዳይ የሉበትም።

አንድ ሥራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ደግሞ፤
እነዚህ ሁለት ነገሮች አንድ ላይ ሊገኙ ግድ ይላል።

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራቸው፤ እኛንም በሱንና ላይ ያጽናን።
*
ለማንኛውም ስለ ተብሊጞች ስህተቶችና ድክመቶች በቂ ግንዛቤ ይኖራችሁ ዘንድ፤
ይህን በፎቶው ላይ ያያዝኩትን የሐሙድ አት-ቱወይጂሪይ (ረሒመሁል'ሏህ) ኪታብ ጋብዣችኋለሁ።
ብዙ ሰው የተብሊጞችን ውጫዊ ሁኔታ ሲመለከት፤
ትክክለኛ የዲን ሰው እየመሰሉት ይሸወዳል።
*
እነርሱ እንደሆኑ ለእውቀት ጉጉት የሌላቸው አሳዛኞች ናቸው።
ከዛሬ አራት አመት በፊት የማውቀው አንድ ልጅ ያኔ ቁርኣን አስተካክሎ መቅራት አይችልም፤ ሻንጣውን ይዞ ግን ሶስት ቀን፣ አርባ ቀን እያለ ይወጣል።
ዘንድሮም ያው ነው። ሻንጣው ብቻ ከትከሻው ላይ አልወረደም።
በዕውቀት መጨመር ብሎ ነገር የለም እነርሱ ዘንድ።

አላህ መንገዱን ይምራቸው፤ ያሳመረ መስሎት በከንቱ ከሚለፋ ሰው በላይ አሳዛኝ የለም።
||
t.me/MuradTadesse
ልዪ የዳዕዋ ዝግጅት በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ‼️
====================================

🔖 የደስተኛ ህይወትን መንገዶች

🔖ትክክለኛ እምነት እና ተፃራሪው

🎙በተለያዩ ኡስታዞች

እሁድ ህዳር 21/2012 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 አደባባይ)

📌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
https://goo.gl/maps/oC7GZtpeLwkzxrVr8

https://t.me/merkezuna
||
መልዕክቱን ለሌሎችም ማስተላለፍን አይዘንጉ።
||
ፕሮግራሙ ሴቶችንም ወንዶችንም ያካትታል።
አሕባሾች ድብደባ ጀምረዋል‼️
=======================
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ተሁለደሪ ወረዳ ሰግለን 017 ቀበሌ፤
ዛሬ ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ይማም ሰይድ የተባለ ወንድም አሕባሾች ነን በሚሉ ጽንፈኛ ወጣቶች ሰግዶ ሲወጣ ተደብድቦ በአሁኑ ወቅት በሕክምና ላይ ይገኛል።
*
በዚህ ቦታ የሚገኘው መስጅድ ውስጥ ባለፈ ግርግር ተፈጥሮ ለ15 ቀናት ያክል በወረዳ ፖሊስ የታሸገ ቢሆንም፤ ኋላ ግን ተከፍቶ ነበር።
ነገር ግን አሕባሾቹ ውሃብያ በመስጅዳችን ውስጥ አይሰግድም በማለት ወንድሞችን ከመስጅድ ሲከለክሉ፤
ወንድሞች ግርግ ከመፍጠር ብለው ቤት ተከራይተው ሶላታቸውን መስገድ ጀምረው ነበር።
ነገር ግን ከመስጅድ ማባረራቸው አንሶ፤ የተከራዩበትን ግለሰብ አታከራይ፤ አባራቸው እያሉ እስከማስፈራራት ደርሰዋል።
ዛሬ ድብደባውን የፈጸሙት በዚሁ ተከራይተው በሚሰግዱበት ቦታ ሂደው ነው።
በድብደባው ላይ ኢብራሂም ሙሴ በተባለ ግለሰብ የተቀናጁ ሰይድ ረታና እያሱ የተባሉ ጽንፈኛ የአሕባሽ አቀንቃኞች መሳተፋቸው ታውቋል።
||
ቆይ አሕባሾች ሙስሊሙን በመበደል ከማኅበረ ቅዱሳን በምን ተሻሉ⁉️
*
የወንድም ይማም ሰይድን ድብደባ ሌሎች ወንድሞች ሲሰሙ፤
ከፍተኛ ግርግር በሙስሊሙና በአሕባሾቹ መካከል ተፈጥሮ ፖሊስ ጥይት ተኩሶ እንደበተናቸው ተነግሯል።
አስቡት እስኪ እስከዚህ ደረጃ በነርሱ የተነሳ ሲደረስ⁉️
*
አሕባሾች የኢትዮ ሙስሊም ነቀርሳ ከሆኑ ሰነበቱ።
ባለፈ ወረባቦ ውስጥ ቁርኣንና መስጅድ ልክ እንደ ካፊሮቹ ማቃጠላችው ይታወቃል።