ትልቅ ጌታ ያለው...
ትልቅ ጌታ ያለው፣ ትንሽ አይመኝም፤
አላህን የያዘ፣ አያጣም ምንንም።
ሲሉ ሰማሁና፣ ለትልቁ ጌታ፤
ዘወትር ለሚሆን፣ ለባሪያው አለኝታ።
ምኞቴን አስፍቼ፣ መለመንን ያዝኩኝ፤
"የኔ ትልቅ ጌታ!" ኢላሒ እያልኩኝ።
አዎን ትልቅ ጌታ ነው፣ የኔ አላህዬ፤
በባዶ አይሸኘኝም፣ አንዱ ፈጣሪዬ።
የጠየቅኩትን ሁሉ፣ ትልቅ አድርግና፤
ስጠኝ "ያ ረዛቁ!" ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ትልቅ ጌታ ያለው፣ ትንሽ አይመኝም፤
አላህን የያዘ፣ አያጣም ምንንም።
ሲሉ ሰማሁና፣ ለትልቁ ጌታ፤
ዘወትር ለሚሆን፣ ለባሪያው አለኝታ።
ምኞቴን አስፍቼ፣ መለመንን ያዝኩኝ፤
"የኔ ትልቅ ጌታ!" ኢላሒ እያልኩኝ።
አዎን ትልቅ ጌታ ነው፣ የኔ አላህዬ፤
በባዶ አይሸኘኝም፣ አንዱ ፈጣሪዬ።
የጠየቅኩትን ሁሉ፣ ትልቅ አድርግና፤
ስጠኝ "ያ ረዛቁ!" ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
#አደራ
አንተን ተመክተው፣ አንተኑ ተማምነው፤
የጀመሩት ጉዳይ፣ አዎን ያማረ ነው።
ወደ አንተ ዞረው፣ አንተኑ ለምነው፤
የጀመሩት ጉዞ፣ መጨረሻው ድል ነው።
አላህዬ...
ለኔ እኮ ነህ ተስፋ፣መደገፊያ፣መሸሽያዬ፤
አሁንም ነህልኝ አለኝታ፣መጠጊያዬ።
የጀመርኩትን መንገድ፣ ለኔ ገር አድርግልኝ፤
ከጠበቅኩት በላይ፣ መልካም ይሁንልኝ።
ካሰብኩት በላይ፣ ደግሞም አሳካልኝ፤
ያለሀኝ አንተው ነህ፣ አደራ ደግፈኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
አንተን ተመክተው፣ አንተኑ ተማምነው፤
የጀመሩት ጉዳይ፣ አዎን ያማረ ነው።
ወደ አንተ ዞረው፣ አንተኑ ለምነው፤
የጀመሩት ጉዞ፣ መጨረሻው ድል ነው።
አላህዬ...
ለኔ እኮ ነህ ተስፋ፣መደገፊያ፣መሸሽያዬ፤
አሁንም ነህልኝ አለኝታ፣መጠጊያዬ።
የጀመርኩትን መንገድ፣ ለኔ ገር አድርግልኝ፤
ከጠበቅኩት በላይ፣ መልካም ይሁንልኝ።
ካሰብኩት በላይ፣ ደግሞም አሳካልኝ፤
ያለሀኝ አንተው ነህ፣ አደራ ደግፈኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
...ብለው ሲጠይቁኝ!!
ማነው ላንተ ያለህ- ብለው ሲጠይቁኝ፣
አላህ ብዬ መለስኩ- ልቤን ደስ እያለኝ።
አዎን ደስ ይለኛል- አንተን ሳስታውስህ፣
አዎን ደስ ይለኛል- እኔ ስመካብህ።
የኔ ጌታ አላህ- የኔ ፈጣሪዬ፣
እገዛህን ይሻል- ሁሌም ነፍስያዬ።
ስኬቴ ባንተ ነው- እኔን አትተወኝ፣
እባክህ ጌታዬ- ከጎኔ ሁንልኝ።
ማነው ያለህ ብለው- የጠየቁኝ ለታ፣
አንተን ነው የምለው- በጠዋትም በማታ።
ዛሬም ሆነ ነገ- አንተው ነህ ተስፋዬ፣
ነገሬን አደራ- አንዱ ፈጣሪዬ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ማነው ላንተ ያለህ- ብለው ሲጠይቁኝ፣
አላህ ብዬ መለስኩ- ልቤን ደስ እያለኝ።
አዎን ደስ ይለኛል- አንተን ሳስታውስህ፣
አዎን ደስ ይለኛል- እኔ ስመካብህ።
የኔ ጌታ አላህ- የኔ ፈጣሪዬ፣
እገዛህን ይሻል- ሁሌም ነፍስያዬ።
ስኬቴ ባንተ ነው- እኔን አትተወኝ፣
እባክህ ጌታዬ- ከጎኔ ሁንልኝ።
ማነው ያለህ ብለው- የጠየቁኝ ለታ፣
አንተን ነው የምለው- በጠዋትም በማታ።
ዛሬም ሆነ ነገ- አንተው ነህ ተስፋዬ፣
ነገሬን አደራ- አንዱ ፈጣሪዬ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
አደራ ያአላህ!!
ሆዷን ብሶት ብሶት፣ ለሷ አላትና፤
ማልቀስ ፈልጋለች፣ ከመስጅዱ ሆና።
ገባች ከመስጅዱ፣ ጥግ ላይ ቁጭ አለች፤
ጌታዋን ለማውጋት፣ እጅግ ጓጉታለች።
የኔ ጌታ ብላ፣ መናገር ጀመረች፤
ክፍት ስላላት፣ ደግሞም ታነባለች።
ከአባቴ በላይ፣ ሁንልኝ ጌታዬ፤
ከእናቴ በላይ፣ እዘን አለኝታዬ።
ከእህቴ በላይ፣ ያረብ አስብልኝ፤
ከወንድሜ በላይ፣ ከጎኔ ሁንልኝ።
አደራ! አደራ! አደራ! ትላለች፤
እራሷን ለአላህ፣ አደራ እየሰጠች።
እኔም አልኳት፣ ለሷ አብሽሪ እህቴ፤
እንዲህ ለምነሽው፣ አይተውሽም እቴ።
አደራ ብለሽው፣ ጌታሽን ለምነሽ፤
እመኚኝ እህቴ፣ ፍፁም ነው ማይረሳሽ።
እሺ አለችና፣ እምባዋን ጠራርጋ፤
ማውጋቷን ገታችው፣ ከአንድዬዋ ጋ።
ተነስታም ሔደች፣ ወጣች ከመስጅዱ፤
አላህ ይዘንላት፣ ይቅለላት መንገዱ።
እኔም አደራ፣ አልኩህ የእህቴን ነገር፤
አንተው አክምላት፣ የልቧን መሰበር።
አደራ እንዳለችህ፣ ሁንላት «ያአላህ!»
ካሰበችው በላይ፣ አድርግላት እባክህ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ሆዷን ብሶት ብሶት፣ ለሷ አላትና፤
ማልቀስ ፈልጋለች፣ ከመስጅዱ ሆና።
ገባች ከመስጅዱ፣ ጥግ ላይ ቁጭ አለች፤
ጌታዋን ለማውጋት፣ እጅግ ጓጉታለች።
የኔ ጌታ ብላ፣ መናገር ጀመረች፤
ክፍት ስላላት፣ ደግሞም ታነባለች።
ከአባቴ በላይ፣ ሁንልኝ ጌታዬ፤
ከእናቴ በላይ፣ እዘን አለኝታዬ።
ከእህቴ በላይ፣ ያረብ አስብልኝ፤
ከወንድሜ በላይ፣ ከጎኔ ሁንልኝ።
አደራ! አደራ! አደራ! ትላለች፤
እራሷን ለአላህ፣ አደራ እየሰጠች።
እኔም አልኳት፣ ለሷ አብሽሪ እህቴ፤
እንዲህ ለምነሽው፣ አይተውሽም እቴ።
አደራ ብለሽው፣ ጌታሽን ለምነሽ፤
እመኚኝ እህቴ፣ ፍፁም ነው ማይረሳሽ።
እሺ አለችና፣ እምባዋን ጠራርጋ፤
ማውጋቷን ገታችው፣ ከአንድዬዋ ጋ።
ተነስታም ሔደች፣ ወጣች ከመስጅዱ፤
አላህ ይዘንላት፣ ይቅለላት መንገዱ።
እኔም አደራ፣ አልኩህ የእህቴን ነገር፤
አንተው አክምላት፣ የልቧን መሰበር።
አደራ እንዳለችህ፣ ሁንላት «ያአላህ!»
ካሰበችው በላይ፣ አድርግላት እባክህ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
እገዛህ አይለየኝ!!
መች አዘነ ብለህ፣ አንተን የያዘ ሰው፤
መች ወደቀስ ብለህ፣ የተደገፈህ ሰው።
መችስ ኋላ ቀረ፣ ቢሆን እንጂ ከፊት፤
መችስ ፈራ ብለህ፣ ለወደፊት ህይወት።
ሀሳቡን ለአንተ፣ የውስጡን አካፍሎህ፤
ጌታዬ እገዛህ፣ አይለየኝ ብሎህ።
ጉዞውን ጀምሮ፣ የተጓዘውን ሰው፤
እርዳታህ አለለት፣ ማይካድ ሀቅ ነው።
የኔ ጌታ አላህ፣ የኔ መከታዬ፤
መሸሽያ፣መጠጊያ፣አለኝታ፣ተስፋዬ።
አንተን ተመክቼ፣ ጀምሬያለሁ መንገድ፤
ከጠየቅኩህ በላይ፣ አግራልኝ ያወድድ።
ካሰብኩትም በላይ፣ ስኬታማ አድርገኝ፤
አደራ ጌታዬ፣ እገዛህ አይለየኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
መች አዘነ ብለህ፣ አንተን የያዘ ሰው፤
መች ወደቀስ ብለህ፣ የተደገፈህ ሰው።
መችስ ኋላ ቀረ፣ ቢሆን እንጂ ከፊት፤
መችስ ፈራ ብለህ፣ ለወደፊት ህይወት።
ሀሳቡን ለአንተ፣ የውስጡን አካፍሎህ፤
ጌታዬ እገዛህ፣ አይለየኝ ብሎህ።
ጉዞውን ጀምሮ፣ የተጓዘውን ሰው፤
እርዳታህ አለለት፣ ማይካድ ሀቅ ነው።
የኔ ጌታ አላህ፣ የኔ መከታዬ፤
መሸሽያ፣መጠጊያ፣አለኝታ፣ተስፋዬ።
አንተን ተመክቼ፣ ጀምሬያለሁ መንገድ፤
ከጠየቅኩህ በላይ፣ አግራልኝ ያወድድ።
ካሰብኩትም በላይ፣ ስኬታማ አድርገኝ፤
አደራ ጌታዬ፣ እገዛህ አይለየኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ከእናቴ በላይ...
እማ ብዬ እኔ፣ እናቴን ስጠራት፤
ስራዋን አቁማ፣ ትለኛለች አቤት።
ከፍቶኛል እናቴ፣ ከእቅፍሽ አስገቢኝ፤
እምባዬ ይወርዳል፣ እናቴ አባብይኝ።
ብዬ ባጫውታት፣ መጣች ፈጠን ብላ፤
እኔን ልታፅናና፣ የያዘችውን ጥላ።
እናት ካለች ከጎን፣ እንዲህ ታደርጋለች፤
ግና ሆድ ይብሳል፣ እሷ ከተለየች።
ከእናቴ በላይ፣ የምታዝነው ጌታ።
ሁሌም ያለህልኝ፣ ጠዋትም በማታ።
ከፍቶኛል፣ደክሞኛል፣አልቀሼ፣አልቅሼ፤
ከቤት ቀርቻለሁ፣ ትራስ ተንተርሼ።
የኔ ባሪያ ብለህ፣ እኔን ቀና አድርገኝ፤
ጌታዬ አልቻልኩም፣ እባክህ ደግፈኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
እማ ብዬ እኔ፣ እናቴን ስጠራት፤
ስራዋን አቁማ፣ ትለኛለች አቤት።
ከፍቶኛል እናቴ፣ ከእቅፍሽ አስገቢኝ፤
እምባዬ ይወርዳል፣ እናቴ አባብይኝ።
ብዬ ባጫውታት፣ መጣች ፈጠን ብላ፤
እኔን ልታፅናና፣ የያዘችውን ጥላ።
እናት ካለች ከጎን፣ እንዲህ ታደርጋለች፤
ግና ሆድ ይብሳል፣ እሷ ከተለየች።
ከእናቴ በላይ፣ የምታዝነው ጌታ።
ሁሌም ያለህልኝ፣ ጠዋትም በማታ።
ከፍቶኛል፣ደክሞኛል፣አልቀሼ፣አልቅሼ፤
ከቤት ቀርቻለሁ፣ ትራስ ተንተርሼ።
የኔ ባሪያ ብለህ፣ እኔን ቀና አድርገኝ፤
ጌታዬ አልቻልኩም፣ እባክህ ደግፈኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ያረብ!!
በሐዘን ጭለማ፣ ብርሀን ሲጠፋብን፤
በተከፋን ጊዜ፣ ለሆኑ አብረውን።
ጥለውን ሳይሔዱ፣ ከኛው ለዘለቁ፣
ጭንቀታችንን አይተው፣ ለተጨናነቁ።
ምክንያት ለሆኑልን፣ ለዛሬው ፈገግታ፤
ክብር ይገባቸው፣ በጠዋትን በማታ።
ውለታችሁ በዝቶ፣ መክፈል ሲያቅተን፤
ለምስጋና ሚሆን፣ ስናጣ ቃላትን።
«ያረብ!» በማለት፣ እጃችን ተነሳ፤
እናንተን በዱዓ፣ ፍጹም አንረሳ።
ያረብ!ያአላህ!ያጀባር!ጌታዬ፤
እሺ በለን ለእኛ፣ እባክህ አንድዬ።
ለእነዚያ ደጋጎች፣ ለቅን አሳቢዎች፤
የወደቅን ለታ፣ ላበረቱን ሰዎች።
መልካምን ስጣቸው፣ ደስም አሰኛቸው፤
ህይወታችሁን ሁሉ፣ ውብ አድርግላቸው!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
በሐዘን ጭለማ፣ ብርሀን ሲጠፋብን፤
በተከፋን ጊዜ፣ ለሆኑ አብረውን።
ጥለውን ሳይሔዱ፣ ከኛው ለዘለቁ፣
ጭንቀታችንን አይተው፣ ለተጨናነቁ።
ምክንያት ለሆኑልን፣ ለዛሬው ፈገግታ፤
ክብር ይገባቸው፣ በጠዋትን በማታ።
ውለታችሁ በዝቶ፣ መክፈል ሲያቅተን፤
ለምስጋና ሚሆን፣ ስናጣ ቃላትን።
«ያረብ!» በማለት፣ እጃችን ተነሳ፤
እናንተን በዱዓ፣ ፍጹም አንረሳ።
ያረብ!ያአላህ!ያጀባር!ጌታዬ፤
እሺ በለን ለእኛ፣ እባክህ አንድዬ።
ለእነዚያ ደጋጎች፣ ለቅን አሳቢዎች፤
የወደቅን ለታ፣ ላበረቱን ሰዎች።
መልካምን ስጣቸው፣ ደስም አሰኛቸው፤
ህይወታችሁን ሁሉ፣ ውብ አድርግላቸው!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ያ አላህ!!
ከቤቴ ወጥቼ፣ መጓዝ ጀምሬያለው፤
ደግሞም ፈልጌያለዉ፣ ጌታዬን ላወጋው።
ተጓዝኩ ተጓዝኩና፣ መልሼ አረፍ አልኩ፤
በጥልቅ ሀሳብ ውስጥ፣ ሳላስበው ሰመጥኩ።
የኔ ጌታ! ብዬ ጀመርኩ ንግግሬን፤
እኔ እወደዋለሁ፣ አንድዬ ጌታዬን።
ታውቃለህ ጀሊሉ፣ ምን ብዬ ልንገርህ፤
ሆዴን ይብሰኛል፣ ለአንተ ሳወራልህ።
ማልቀስም ያምረኛል፣ ደግሞም አለቅሳለሁ።
«ያ አላህ!» በማለት፣ ዛሬም እጣራለሁ።
እባክህ «ያ አላህ!»ዛሬም እባከህን፤
አቤት ብለህ በለኝ፣ ምስኪን ባሪያህን።
እባክህ «ያ አላህ!» ሁሉን አሳካልኝ፤
የኔ ባሪያ ብለህ፣ እኔን ቀና አድርገኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ከቤቴ ወጥቼ፣ መጓዝ ጀምሬያለው፤
ደግሞም ፈልጌያለዉ፣ ጌታዬን ላወጋው።
ተጓዝኩ ተጓዝኩና፣ መልሼ አረፍ አልኩ፤
በጥልቅ ሀሳብ ውስጥ፣ ሳላስበው ሰመጥኩ።
የኔ ጌታ! ብዬ ጀመርኩ ንግግሬን፤
እኔ እወደዋለሁ፣ አንድዬ ጌታዬን።
ታውቃለህ ጀሊሉ፣ ምን ብዬ ልንገርህ፤
ሆዴን ይብሰኛል፣ ለአንተ ሳወራልህ።
ማልቀስም ያምረኛል፣ ደግሞም አለቅሳለሁ።
«ያ አላህ!» በማለት፣ ዛሬም እጣራለሁ።
እባክህ «ያ አላህ!»ዛሬም እባከህን፤
አቤት ብለህ በለኝ፣ ምስኪን ባሪያህን።
እባክህ «ያ አላህ!» ሁሉን አሳካልኝ፤
የኔ ባሪያ ብለህ፣ እኔን ቀና አድርገኝ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
እሱን ለአንተ አደራ!!
ፍፁም አልከፍልህም፣፤ ጠንቅቄ አውቃለሁ፤
አዎን አልክስህም፣ ይህንን አምናለሁ፤
ለኔ የሆንከውን፣ እንዴት እረሳለሁ።
እባክህ«ያጀባር »የኔ ጌታ አላህ፤
ልመናዬን ስማኝ፣ እባክህ እባክህ።
እሱ ማለት ለኔ በቃ፣ አልገልፀውም፤
ብዕር ብጨብጥም፣እሱን አልፅፈውም።
እናማ ጌታዬ፣ ከደጉ ይግጠመው፤
በሔደበት ሁሉ፣ ጥበቃህ አይለየው።
እሱ ማለት ለኔ፣ የተለየ ሰው ነው፤
እድሜውን አርዝመህ ፣በጤና አቆየው፤
በሁሉ ተግባሩ፣ እገዛህ አይለየው፤
በሁለቱም አለም፣ ደስተኛ አድርገው!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ፍፁም አልከፍልህም፣፤ ጠንቅቄ አውቃለሁ፤
አዎን አልክስህም፣ ይህንን አምናለሁ፤
ለኔ የሆንከውን፣ እንዴት እረሳለሁ።
እባክህ«ያጀባር »የኔ ጌታ አላህ፤
ልመናዬን ስማኝ፣ እባክህ እባክህ።
እሱ ማለት ለኔ በቃ፣ አልገልፀውም፤
ብዕር ብጨብጥም፣እሱን አልፅፈውም።
እናማ ጌታዬ፣ ከደጉ ይግጠመው፤
በሔደበት ሁሉ፣ ጥበቃህ አይለየው።
እሱ ማለት ለኔ፣ የተለየ ሰው ነው፤
እድሜውን አርዝመህ ፣በጤና አቆየው፤
በሁሉ ተግባሩ፣ እገዛህ አይለየው፤
በሁለቱም አለም፣ ደስተኛ አድርገው!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
አላህዬ የኔ አላህ...
አላህዬ የኔ አላህ፣ የኔ መከታ፤
የኔ ጋሻ፣የኔ ተስፋ፣የኔ አለኝታ።
ጠይቄህ መች አፈርኩኝ፤
አንተን ብዬ መች አዘንኩኝ።
እጄን አንስቼ፣ ያረብ ብዬ፤
ፊቴን አዙሬ፣ ወደ አንተው ጌታዬ።
ከምኞቴ በላይ፣ ሰጥተሀኛል፤
ከጠበቅኩት በላይ፣ አስደስተሀኛል።
ዛሬም ያአላህ፣ ያለሀኝ አንተው ነህ፤
ልክ እንደ አመሌ፣ መጣሁኝ ከደጅህ።
እሺ እንደምትለኝ፣ እርግጠኛ ሆኜ፤
መጠየቅን ያዝኩኝ፣ አንተን ተማምኜ።
እናማ አላህዬዋ፣ ነገሬን አግራልኝ፤
ልክ እንደ ትናንቱ፣ ዛሬም አለሁ በለኝ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
አላህዬ የኔ አላህ፣ የኔ መከታ፤
የኔ ጋሻ፣የኔ ተስፋ፣የኔ አለኝታ።
ጠይቄህ መች አፈርኩኝ፤
አንተን ብዬ መች አዘንኩኝ።
እጄን አንስቼ፣ ያረብ ብዬ፤
ፊቴን አዙሬ፣ ወደ አንተው ጌታዬ።
ከምኞቴ በላይ፣ ሰጥተሀኛል፤
ከጠበቅኩት በላይ፣ አስደስተሀኛል።
ዛሬም ያአላህ፣ ያለሀኝ አንተው ነህ፤
ልክ እንደ አመሌ፣ መጣሁኝ ከደጅህ።
እሺ እንደምትለኝ፣ እርግጠኛ ሆኜ፤
መጠየቅን ያዝኩኝ፣ አንተን ተማምኜ።
እናማ አላህዬዋ፣ ነገሬን አግራልኝ፤
ልክ እንደ ትናንቱ፣ ዛሬም አለሁ በለኝ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ኢላሒ...
የቀልቤ ሀጃ፣ ሁሉም ተሟልቶልኝ፤
ያሰብኩት በሙሉ፣ ለእኔ ተሳክቶልኝ።
ያደረግኩት ፀሎት፣ ጠቅላላ ሰምሮልኝ፤
ያስጨነቀኝ ሁሉ፣ መስመርም ይዞልኝ።
ከጠበቅኩት በላይ፣ ነገሮች ገር ሆነው፤
ከእቅዴ በላይ፣ ጉዳዮች ተውበው።
ለካ ለዚህ ነበር፣ እንድያ መጨነቄ፤
ለካ ለዚህ ነበር፣ የጠፋብኝ ሳቄ።
አመሰግናለሁ፣ የኔ ጌታ ብዬ፤
ከከጀልኩት በላይ፣ ሰጠሀኝ አንድዬ።
ብዬ ሱጁድ ልውረድ፣ የለም የሚሳንህ፤
ያሀን ቀን አቅርበው፣ እባክህ እባክህ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
የቀልቤ ሀጃ፣ ሁሉም ተሟልቶልኝ፤
ያሰብኩት በሙሉ፣ ለእኔ ተሳክቶልኝ።
ያደረግኩት ፀሎት፣ ጠቅላላ ሰምሮልኝ፤
ያስጨነቀኝ ሁሉ፣ መስመርም ይዞልኝ።
ከጠበቅኩት በላይ፣ ነገሮች ገር ሆነው፤
ከእቅዴ በላይ፣ ጉዳዮች ተውበው።
ለካ ለዚህ ነበር፣ እንድያ መጨነቄ፤
ለካ ለዚህ ነበር፣ የጠፋብኝ ሳቄ።
አመሰግናለሁ፣ የኔ ጌታ ብዬ፤
ከከጀልኩት በላይ፣ ሰጠሀኝ አንድዬ።
ብዬ ሱጁድ ልውረድ፣ የለም የሚሳንህ፤
ያሀን ቀን አቅርበው፣ እባክህ እባክህ!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
#ያአላህ!!!
ልቤን አስጨንቆ... እረፍት የነሳኝን፣
ልክ እንደ ተራራ... ገዝፎ የታየኝን።
እንቅልፍ ለመተኛት...ሚከነክነኝን፣
በሀሳብ ባህር ውስጥ... ወስዶ የሚከተኝን።
ቢሆንልኝ ብዬ... ዘወትር የምመኘው፣
እጄን እያነሳሁ... «ያአላህ» የምለው።
ታውቃለህ ሀጃዬን... ምን ብዬ ልንገርህ፣
ከጠበቅኩት በላይ... አሳካው እባክህ።
ለአንተ የሚከብድህ... አንዳች ነገር የለም፣
ጠንቅቄ አውቃለሁ... ትናንትናም ዛሬም።
ህልሜ እውን... ሆኖ አሳየኝ ጌታዬ፣
አንተው ነህ ረዳቴ... መከታ፣ጋሻዬ።
ልፋቴን እይና..ድካሜን ቁጠረው፣
ከጥረቴ በላይ... ሁሉንም አሳካው።
በማለት ለመንኩህ... እኔ ምስኪን ባሪያህ፣
ምንም አይሳንህም... ሁሉን ትችላለህ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ልቤን አስጨንቆ... እረፍት የነሳኝን፣
ልክ እንደ ተራራ... ገዝፎ የታየኝን።
እንቅልፍ ለመተኛት...ሚከነክነኝን፣
በሀሳብ ባህር ውስጥ... ወስዶ የሚከተኝን።
ቢሆንልኝ ብዬ... ዘወትር የምመኘው፣
እጄን እያነሳሁ... «ያአላህ» የምለው።
ታውቃለህ ሀጃዬን... ምን ብዬ ልንገርህ፣
ከጠበቅኩት በላይ... አሳካው እባክህ።
ለአንተ የሚከብድህ... አንዳች ነገር የለም፣
ጠንቅቄ አውቃለሁ... ትናንትናም ዛሬም።
ህልሜ እውን... ሆኖ አሳየኝ ጌታዬ፣
አንተው ነህ ረዳቴ... መከታ፣ጋሻዬ።
ልፋቴን እይና..ድካሜን ቁጠረው፣
ከጥረቴ በላይ... ሁሉንም አሳካው።
በማለት ለመንኩህ... እኔ ምስኪን ባሪያህ፣
ምንም አይሳንህም... ሁሉን ትችላለህ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ደረሰ ሰአቱ...
ጉዳዩን ሰብስቦ፣ አንተን ለመጠየቅ፤
ብዙ አይነት ሰው አለ፣ ጁመአን ሚናፍቅ።
ስንት ባሪያ አለ፣ ሀጃው የበዛበት፤
ከጌታው ጋር ብቻ፣ ሚፈልግ ሊያወራት።
በጥርሱ እየሳቀ፣ ውስጡ የቆሰለ፤
ዘወትር ሚማፀን፣ አንተን እየከጀለ።
ወላሒ፣ወላሒ ብዙ አይነት ሰው አለ!!
በተለይ በተለይ፣ አርብን የሚናፍቅ፤
ከአስር በኋላን፣ በጉጉት ሚጠብቅ።
ይሀው ደረሰለት፣ ለምስኪኑ ባሪያህ፣
ከሰው ተነጥሏል፣ የልቡን ሊያወጋህ።
ደግሞም ተስፋ አለው፣ እንደምትሰማው፤
ካለበት መከራ፣ እንደምታወጣው።
እዘንለት ለሱ አዛኝ ነህና፣
ሁሉን አሳካለት ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ጉዳዩን ሰብስቦ፣ አንተን ለመጠየቅ፤
ብዙ አይነት ሰው አለ፣ ጁመአን ሚናፍቅ።
ስንት ባሪያ አለ፣ ሀጃው የበዛበት፤
ከጌታው ጋር ብቻ፣ ሚፈልግ ሊያወራት።
በጥርሱ እየሳቀ፣ ውስጡ የቆሰለ፤
ዘወትር ሚማፀን፣ አንተን እየከጀለ።
ወላሒ፣ወላሒ ብዙ አይነት ሰው አለ!!
በተለይ በተለይ፣ አርብን የሚናፍቅ፤
ከአስር በኋላን፣ በጉጉት ሚጠብቅ።
ይሀው ደረሰለት፣ ለምስኪኑ ባሪያህ፣
ከሰው ተነጥሏል፣ የልቡን ሊያወጋህ።
ደግሞም ተስፋ አለው፣ እንደምትሰማው፤
ካለበት መከራ፣ እንደምታወጣው።
እዘንለት ለሱ አዛኝ ነህና፣
ሁሉን አሳካለት ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
የኔ ጌታ አላህ!!
ህመማቸውን፣ በውስጣቸው ሸሽገው፤
ቢከፋቸው እንኳ፣ በጥርሳቸው ስቀው።
ለሰዎች ፈገግታ፣ ዘወትር ሚለፉ፤
በበጎ ተግባራት፣ ከደጅህ ላልጠፉ።
አንተን ለማስደሰት፣ ሁሌ ለሚጥሩ፤
ፊትህን ፈልገው፣ መልካም ለሚሰሩ፤
ሀዘን ሲገጥማቸው፤ ለሰው ማይናገሩ።
ለነዚያ ባሮችህ፣ ለቅን አሳቢዎች፤
ከሰውም ሰው አለ፣ ለሚባሉ ምርጦች።
የኔ ጌታ አላህ፣ አንተ እዘንላቸው፤
ያስጨነቃቸውን፣ አንተው አንሳላቸው።
ህመማቸውን ሙሉ አሽርና፤
ደስታቸውን አምጣው ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ህመማቸውን፣ በውስጣቸው ሸሽገው፤
ቢከፋቸው እንኳ፣ በጥርሳቸው ስቀው።
ለሰዎች ፈገግታ፣ ዘወትር ሚለፉ፤
በበጎ ተግባራት፣ ከደጅህ ላልጠፉ።
አንተን ለማስደሰት፣ ሁሌ ለሚጥሩ፤
ፊትህን ፈልገው፣ መልካም ለሚሰሩ፤
ሀዘን ሲገጥማቸው፤ ለሰው ማይናገሩ።
ለነዚያ ባሮችህ፣ ለቅን አሳቢዎች፤
ከሰውም ሰው አለ፣ ለሚባሉ ምርጦች።
የኔ ጌታ አላህ፣ አንተ እዘንላቸው፤
ያስጨነቃቸውን፣ አንተው አንሳላቸው።
ህመማቸውን ሙሉ አሽርና፤
ደስታቸውን አምጣው ትችላለህና!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ሰዎችም አይደለን...
እስካለን በህይወት፣ ካልወጣ ሩሐችን፤
አንተን ይከጅላል፣ ደካማው ልባችን።
ከሰው ተሸሽጎ፣ አይናችን ያነባል፤
እጃችን ከፍ ብሎ፣ አላህዬ ይላል።
ሰዎችም አይደለን...
ያንተኑ እርዳታ፣ ዘወትር የምንሻ፤
ወደ አንተ ቢሆን፣ እንጂ የሌለን መሸሻ።
ከፋንም፣ደላንም፣አመመንም፣ዳንም፤
አልቅሰን፣ብንስቅም፣አጥተን፣ብናገኝም።
ሁል ጊዜ ወደ አንተ፣ ይዞራል ፊታችን፤
አግዘን፣ደግፈን፣በሁሉ ሐጃችን።
ዛሬም ሆነ ነገ፣ ባንተ ነው ተስፋችን!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
እስካለን በህይወት፣ ካልወጣ ሩሐችን፤
አንተን ይከጅላል፣ ደካማው ልባችን።
ከሰው ተሸሽጎ፣ አይናችን ያነባል፤
እጃችን ከፍ ብሎ፣ አላህዬ ይላል።
ሰዎችም አይደለን...
ያንተኑ እርዳታ፣ ዘወትር የምንሻ፤
ወደ አንተ ቢሆን፣ እንጂ የሌለን መሸሻ።
ከፋንም፣ደላንም፣አመመንም፣ዳንም፤
አልቅሰን፣ብንስቅም፣አጥተን፣ብናገኝም።
ሁል ጊዜ ወደ አንተ፣ ይዞራል ፊታችን፤
አግዘን፣ደግፈን፣በሁሉ ሐጃችን።
ዛሬም ሆነ ነገ፣ ባንተ ነው ተስፋችን!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
...ለናፈቀ
ሀጃው ተደራርቦ፣ ጉዳይ ለበዛበት፤
ጁመአን ለናፈቀ፣ ይሀው ደረሰለት።
የልቡን መጨነቅ፣የሐሳቡን መብዛት፤
ለአላህ ይንገረው፣ እጆቹን በማንሳት።
ሰአቱ መጣለት፣ ይሀው ደረሰበት፤
ከአስር በኋላ፣ ያውጋ ከጌታው ፊት።
ነብዪ እንዳሉን፣አለው ተቀባይነት፤
ሰላት ሰላም ይውረድ፣ በአለሙ መብራት።
እናማ ውዶቼ፣ እንዳታመልጣችሁ፤
ጠይቁት ጀሊሉን፣ ያረብ እያላችሁ።
አንተኑ ተማምነው፣ እንደምትሰማቸው፤
ከደጅህ ለጠኑ፣ ሰአቷን ጠብቀው።
አንተው አለሁ ብለህ፣ ምላሽን ስጣቸው፤
ከለመኑህ በላይ፣ ያረብ ለግሳቸው።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ሀጃው ተደራርቦ፣ ጉዳይ ለበዛበት፤
ጁመአን ለናፈቀ፣ ይሀው ደረሰለት።
የልቡን መጨነቅ፣የሐሳቡን መብዛት፤
ለአላህ ይንገረው፣ እጆቹን በማንሳት።
ሰአቱ መጣለት፣ ይሀው ደረሰበት፤
ከአስር በኋላ፣ ያውጋ ከጌታው ፊት።
ነብዪ እንዳሉን፣አለው ተቀባይነት፤
ሰላት ሰላም ይውረድ፣ በአለሙ መብራት።
እናማ ውዶቼ፣ እንዳታመልጣችሁ፤
ጠይቁት ጀሊሉን፣ ያረብ እያላችሁ።
አንተኑ ተማምነው፣ እንደምትሰማቸው፤
ከደጅህ ለጠኑ፣ ሰአቷን ጠብቀው።
አንተው አለሁ ብለህ፣ ምላሽን ስጣቸው፤
ከለመኑህ በላይ፣ ያረብ ለግሳቸው።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
የኔ ጌታ!!!
ከፋኝ አዘንኩና... አይኔም እምባ አቆረ፣
ውስጤም ደከመና... ልቤ ተሰበረ።
ፈልጌያለሁ እኔ... ከአንተ ጋር ለማውጋት፣
ወላሒ እወዳለሁ... ከጀሊሉ ማወራት።
የኔ ጌታ ብዬ... ልንገርህ ጌታዬ፣
ወደ አንተ እዞራለሁ... ነህና ጋሻዬ።
ከጎኔ ማትጠፋ... ለእኔ መከታዬ፣
ተስፋ፣አለኝታዬ... ደግሞም መጠጊያ።
የልቤን ሙላልኝ... ታውቃለህ ስለ እኔ፣
እዝነተ-ሰፊ ነህ... እዘንልኝ ለእኔ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ከፋኝ አዘንኩና... አይኔም እምባ አቆረ፣
ውስጤም ደከመና... ልቤ ተሰበረ።
ፈልጌያለሁ እኔ... ከአንተ ጋር ለማውጋት፣
ወላሒ እወዳለሁ... ከጀሊሉ ማወራት።
የኔ ጌታ ብዬ... ልንገርህ ጌታዬ፣
ወደ አንተ እዞራለሁ... ነህና ጋሻዬ።
ከጎኔ ማትጠፋ... ለእኔ መከታዬ፣
ተስፋ፣አለኝታዬ... ደግሞም መጠጊያ።
የልቤን ሙላልኝ... ታውቃለህ ስለ እኔ፣
እዝነተ-ሰፊ ነህ... እዘንልኝ ለእኔ።
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
እሷን ለአንተ አደራ!!
በዱአሽ አለችኝ፣ እጅግ ተክዛለች፤
ምክንያቷን ባላውቅም፣ በጣም ተከፍታለች።
አብሽሪ እህቴ፣ ይህም እኮ ያልፋል፤
አላህዬ አለ፣ አይዞሽ ያግዝሻል።
አውቃለሁ አዝነሻል፣ ተረድቼሻለሁ፤
ደግሞ አልረሳሽም፣ ዱአ አደርግልሻለሁ፤
ብዬ አፅናንቻት፣ ተሰነባበትኳት፤
የልቧን መሻት፣ እባክህ ሙላላት።
ሀዘኗን በደስታ፣ ያረብ ቀይርላት፤
ፊቷን በፈገግታ፣ ዘወትር አድምቅላት።
ይህ ነው የኔ ምኞት፣ ሁሌ ደስ ይበላት፤
እሷን ለአንተ አደራ፣ ከጎኗ ሁንላት!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
በዱአሽ አለችኝ፣ እጅግ ተክዛለች፤
ምክንያቷን ባላውቅም፣ በጣም ተከፍታለች።
አብሽሪ እህቴ፣ ይህም እኮ ያልፋል፤
አላህዬ አለ፣ አይዞሽ ያግዝሻል።
አውቃለሁ አዝነሻል፣ ተረድቼሻለሁ፤
ደግሞ አልረሳሽም፣ ዱአ አደርግልሻለሁ፤
ብዬ አፅናንቻት፣ ተሰነባበትኳት፤
የልቧን መሻት፣ እባክህ ሙላላት።
ሀዘኗን በደስታ፣ ያረብ ቀይርላት፤
ፊቷን በፈገግታ፣ ዘወትር አድምቅላት።
ይህ ነው የኔ ምኞት፣ ሁሌ ደስ ይበላት፤
እሷን ለአንተ አደራ፣ ከጎኗ ሁንላት!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
አልሀምዱሊላህ!!
ጠይቀንህ... ለምትሰጠን ጌታ፣
አቤት ለምትለን... በጠዋትም በማታ።
አዛኙ ጌታ ሆይ... ክብርህ ከፍ ይበል፣
ከማመስገን ውጭ... እኛ ምንም አንል።
ያሀ ጊዜ አልፎ... ከዛሬ በቅተናል፣
አልሀምዱሊላህ... ለአንተ ምን ይሳናል።
ሁሉን ትችላለህ... መቼ ያቅትሀል፣
የዱአችን ምላሽ... በአይናችን ታይቷል።
እልፍ አእላፍ ምስጋና...ጌታዬ ይድረስህ፣
አሁንም ደጋግመን...እኛ አመሰገንህ!!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
ጠይቀንህ... ለምትሰጠን ጌታ፣
አቤት ለምትለን... በጠዋትም በማታ።
አዛኙ ጌታ ሆይ... ክብርህ ከፍ ይበል፣
ከማመስገን ውጭ... እኛ ምንም አንል።
ያሀ ጊዜ አልፎ... ከዛሬ በቅተናል፣
አልሀምዱሊላህ... ለአንተ ምን ይሳናል።
ሁሉን ትችላለህ... መቼ ያቅትሀል፣
የዱአችን ምላሽ... በአይናችን ታይቷል።
እልፍ አእላፍ ምስጋና...ጌታዬ ይድረስህ፣
አሁንም ደጋግመን...እኛ አመሰገንህ!!!
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0
https://t.me/Munajah0