ከምጡቃን አንደበት
759 subscribers
120 photos
128 links
የታላላቅ ሰዎችን ንግግር እያደንን እንለወጣለን!!!❤️❤️❤️❤️
ትጋት ለውጤት ያበቃል!ተስፋ ለስኬት ያበቃል!

ከምጡቃን አንደበት ጥበብን ከምንጩ፣ እውቀትን ከምጡቃን። ለተሻለ አስተሳሰብ እና ለታላቅ ህይወት!

📩 ለጥያቄ፡ @kiimbos52
Download Telegram
አሪስቶፋነስ (Aristophanes)

— ይህ ተናጋሪ የሰውን ልጅ አፈጣጠር በተረት መልክ ያቀርባል። "በጥንት ዘመን የሰው ልጅ አራት እጅ፣ አራት እግር እና ሁለት ፊት የነበረው አንድ ሙሉ ፍጡር ነበር ይላል። ነገር ግን አማልክት በሰዎች ጥንካሬ ቀናተው በሁለት ከፈሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እያንዳንዱ ሰው በዓለም ላይ የሚንከራተተው የጠፋውን ሌላኛውን ክፍሉን ለማግኘት ፈልጎና ሙሉ ለመሆን ነው" በማለት ፍቅርን የሙሉነት ፍለጋ አድርጎ ያቀርበዋል።

https://t.me/mtuk_hasab
4👏21
🪣 የዝነኛው ባልዲ ጦርነት፡ የሁለት ከተሞች እልህ

በሰሜን ኢጣሊያ የሚገኙት ሞዴና (Modena) እና ቦሎኛ (Bologna) የተባሉ ሁለት በሀብት የበለጸጉ ከተሞች ለብዙ ዘመናት በከባድ ጠላትነት ይኖሩ ነበር። ጠላትነታቸው የድንበር ብቻ አልነበረም፤ የፖለቲካና የሃይማኖትም ጭምር ነበር። የሞዴና ህዝብ የሮማን እምፓየር ንጉሥ ደጋፊ ሲሆን፣ የቦሎኛ ህዝብ ደግሞ የሮሙን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፖፕ) ይደግፍ ነበር።

በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለው ውጥረት ልክ እንደ ባሩድ ክምር ሆኖ ጥቃቅን ምክንያቶችን ይፈልግ ነበር።

በ1325 ዓ.ም. መባቻ ላይ፣ የሞዴና ከተማ ወታደሮች እየተሳለቁና እየፎከሩ በምስጢር ወደ ቦሎኛ ከተማ ድንበር ሰርገው ገቡ። ዓላማቸው ትልቅ ውድመት ማድረስ አልነበረም፤ ይልቁንም የቦሎኛን ህዝብ ክብር መንካት፣ እነርሱን ማዋረድና ማበሳጨት ነበር።

ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ መሃል በሚገኘው ዋና የውሃ ጉድጓድ ጋ ደረሱ። እዚያም ተቀምጦ የነበረውን፣ ከኦክ እንጨት የተሰራና በብረት የተጠፈረ አሮጌ የውሃ መቅጃ ባልዲ አዩ።

የሞዴና ወታደሮች መሪ ሳቀና "ይህንን ባልዲ እንውሰደው። የቦሎኛ ሰዎች የኛን የበላይነት በየቀኑ እንዲያስታውሱ ያደርጋቸዋል" አለ። ባልዲውን ዘርፈው ወደ ከተማቸው ተመለሱ።

የቦሎኛ ከተማ መሪዎች ባልዲው መዘረፉን ሲሰሙ ቁጣቸው ከሰማይ ደረሰ። ነገሩ ስለ ባልዲው ዋጋ አልነበረም፤ የከተማቸው ክብርና ኩራት በጠላቶቻቸው እግር ስር መረገጡ ነበር።

ወዲያውኑ ወደ ሞዴና ከተማ መሪዎች መልዕክተኛ ሰደዱ "ያነሳችሁትን ባልዲ በአስቸኳይ መልሱ! ካልሆነ ግን በመካከላችን ከባድ ደም መፋሰስ ይሆናል!" ሲሉ አስጠነቀቁ።

የሞዴና መሪዎች ግን መልዕክቱን በሳቅና በፌዝ ተቀበሉት። "ባልዲውን ማየት ከፈለጋችሁ ወደ ከተማችን መጥታችሁ በነጻ መቅዳት ትችላላችሁ" በማለት መለሱላቸው።

ይህ የፌዝ ምላሽ የቦሎኛን ህዝብ ይበልጥ አስቆጣ። የቦሎኛ አስተዳደር የጦር አዋጅ አወጀ። አንድን አሮጌ ባልዲ ለማስመለስ ሲባል 32,000 እግርኛ ወታደሮች እና 2,000 ፈረሰኞች የተሳተፉበት ታላቅ ሰራዊት ተደራጀ። በወቅቱ ይህ ሰራዊት በአውሮፓ ካሉት ትላልቅ ሰራዊቶች አንዱ ነበር።

ሞዴና በበኩሏ ጥቃቱን ለመከላከል 5,000 እግርኛ ወታደሮችንና 2,000 ፈረሰኞችን አሰለፈች።

በህዳር ወር 1325 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ፣ ሁለቱ ሰራዊቶች ዛፖሊኖ (Zappolino) በተባለ ስፍራ ላይ ፊት ለፊት ተገናኙ። የቦሎኛ ሰራዊት በቁጥር እጅግ ይበልጥ ነበር። ነገር ግን የሞዴና ሰራዊት በተጠናና በተደራጀ ስልት ማጥቃት ጀመረ።

ጦርነቱ ጥቂት ሰዓታትን ብቻ የፈጀ ቢሆንም እጅግ ጨካኝና አሰቃቂ ነበር። ሰይፎች ተመዘዙ፣ ጋሻዎች ተሰባበሩ። በቁጥር አናሳ የነበሩት የሞዴና ወታደሮች በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት የቦሎኛን ሰራዊት መሀል ለመሀል ሰንጥቀው በመግባት መበተን ቻሉና ድል አደረጓቸው።

በዚያች አጭር የጦርነት ምሽት ብቻ ወደ 2,000 የሚጠጉ ወታደሮች ህይወታቸውን አጡ።

የቦሎኛ ሰራዊት በድንጋጤ ወደ ከተማው ግንብ ሲሸሽ፣ የሞዴና ወታደሮች እያሳደዱ እስከ ከተማዋ በር ድረስ መጡ። ከተማዋን ሰብረው ከመግባት ይልቅ ግን፣ በድጋሚ በቦሎኛ ህዝብ ላይ ለመሳለቅ ወሰኑ። ከከተማው በር ውጪ በነበረ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ላይ የነበረውን ሁለተኛ ባልዲ ጨምረው ዘረፉት!

ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ሁለቱ ከተሞች የሰላም ስምምነት አደረጉ። ሞዴና የያዘቻቸውን የቦሎኛን ምርኮኞችና መሬቶች በሙሉ መለሰች። ነገር ግን አንድ ነገር ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆነችም ያንን ታሪካዊ ባልዲ!



የሚገርመው ያ ጦርነት የተነሳበት የእንጨት ባልዲ ዛሬም ድረስ አለ! ከ700 ዓመታት በኋላ ዛሬም ድረስ በሞዴና ከተማ ውስጥ በሚገኘው "ፓላዞ ኮሙናሌ" (Palazzo Comunale) በተባለው ታሪካዊ ህንፃ ማሳያ ክፍል ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የቦሎኛ ህዝብ ግን ያንን ባልዲ ዛሬም ድረስ አላስመለሰውም።😁

https://t.me/mtuk_hasab
😍31👍1
በስህተት መንገድ ላይ በፍጥነት ከመሮጥ፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ በዝግታ መጓዝ ይሻላል። ምክንያቱም ስኬት ፍጥነት ሳይሆን አቅጣጫ ነው።

💬 እናንተስ በህይወት ውስጥ ትልቁ ስኬት ምንድነው ትላላችሁ? Comment

🔗 Join: @mtuk_hasab
🥰21
በልጁ የተከዳው ታላቁ የዴንማርክ ንጉስ ንጉስ ሀራልድ ብሉቱዝ

በ960 ዓ.ም. የክረምቱ ቅዝቃዜ በዴንማርክ የነገሥታት መቀመጫ በነበረችው ጄሊንግ ከተማ ላይ እንደ ከባድ ጭነት ተጭኖ ነበር። በቤተመንግስቱ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ፣ የእንጨት እሳቱ እየነደደ ይጨሳል። የዴንማርክ እና የኖርዌይ ንጉሥ የሆነው ሃራልድ ጎርምሰን (Harald Gormsson) በጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ሆኖ በትልቁ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጧል።

ሰዎቹ በስተጀርባው "ብሉቱዝ" (ሰማያዊ ጥርስ) እያሉ በሹክሹክታ ይጠሩታል። ይህንን ስም ያገኘው በአንድ የጦርነት አደጋ ምክንያት በሰበሰበውና ሰማያዊ ቀለም በያዘው የፊት ጥርሱ ወይም ደግሞ ሰማያዊ የሐር ልብሶችን አዘውትሮ ስለሚለብስ ነበር። ነገር ግን ማንም ፊት ለፊት ሊናገረው አይደፍርም፤ እሱ ጨካኞቹንና የተበታተኑትን የቫይኪንግ ጎሳዎች በአንድ ግዛት ስር የሰበሰበ ኃያልና ታላቅ ንጉሥ ነው።

ንጉሥ ሆይ፣" አለ ከጎኑ የቆመው ታማኝ የጦር አዛዡ ቶርኬል። "ልጅህ ስዌይን ከባህር ማዶ ዘመቻ ተመልሷል። ነገር ግን ብቻውን አይደለም። መርከቦቹ በወርቅና በምርኮኞች የተሞሉ ናቸው። በከተማው ውስጥ ያሉ ወጣቶች ስሙን እየጠሩ እያጨበጨቡለት ነው።"

ንጉስ ሃራልድ ፊቱን አጨፈገገ። ልጁ ስዌይን (Svein Forkbeard) ገና በወጣትነቱ የጦርነት ጥማት ያለው፣ በባህላዊው የቫይኪንግ አማልክት (ኦዲን እና ቶር) የሚያምን ጨካኝ ተዋጊ ነበር። ሃራልድ ግን በቅርቡ የሀገሪቱን ህዝብ ወደ ክርስትና እምነት ቀይሮ ነበር። ይህ የሃይማኖት ለውጥ በአባትና በልጅ መካከል ትልቅ የጥላቻ ግድግዳ ጥሎ ነበር።

ስዌይን ሁልጊዜ ከእግሬ ስር ስልጣንን ለመንጠቅ ይፈልጋል፣" አለ ሃራልድ በዝቅተኛ ድምፅ። "ነገር ግን እኔ የዴንማርክን ድንበር ያጠናከርኩ፣ ታላቁን ግንብ (Danevirke) የገነባሁ ንጉሥ ነኝ። የገዛ ልጄ ሊያጠፋኝ አይችልም።"

ዓመታት አለፉ። በአባትና በልጅ መካከል ያለው ውጥረት እየገነፈለ መጣ። ስዌይን የአባቱን የሰላምና የክርስትና ፖሊሲ አልወደደውም። "አባታችን የቫይኪንጎችን የጀግንነት መንፈስ እየገደለው ነው! ወደ አሮጌው አማልክቶቻችን እና ወደ ወረራ ህይወታችን መመለስ አለብን!" እያለ ወጣቶቹን የቫይኪንግ ተዋጊዎች ማነሳሳት ጀመረ።

በ985 ዓ.ም. ክረምት ላይ፣ ስዌይን ከእንግሊዝ የባህር ላይ ወረራ ተመለሰ። በዚህ ጊዜ ግን ወደ አባቱ ቤተመንግስት የሄደው ለመቀመጥ ሳይሆን በምስጢር ሰራዊት ለማደራጀት ነበር። የጄምስቪኪንግስ (Jomsvikings) የሚባሉትን እጅግ ጨካኝና ቅጥር ነፍሰ ገዳይ የቫይኪንግ ሰራዊቶችን በገንዘብ ገዛ።

አንድ ምሽት ሃራልድ በቤተመንግስቱ ሳለ፣ የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በድንጋጤ ወደ አዳራሹ እየሮጡ ገቡ።

"ንጉሥ ሆይ! ክህደት ሆኗል!" አለ ጠባቂው እየተንተባተበ። "ልጅህ ስዌይን ትልቅ የጦር መርከብ ይዞ በባህር በኩል እየመጣ ነው። የከተማው መኳንንትም አሳልፈው ሰጥተውታል። ህዝቡ አንተን ጥሎ ከእሱ ጋር ቆሟል!"

ሃራልድ ደነገጠ። የገነባት ሀገር፣ አንድ ያደረጋቸው ጎሳዎች ሁሉ በአንዴ ፊታቸውን አዞሩበት። እድሜው ገፍቶ የነበረ ቢሆንም፣ የቫይኪንግ ደሙ ገነፈለ። ጋሻና ሰይፉን አንስቶ፣ አሁንም ለእሱ ታማኝ ከሆኑ ጥቂት ወታደሮች ጋር ወደ ባህር ዳርቻው አመራ።

በባህር ዳርቻው ላይ የጦርነቱ ነጋሪት ተጎሰመ። አባትና ልጅ ፊት ለፊት ተገናኙ። ጦርነቱ እጅግ አሰቃቂ ነበር። የሃራልድ ታማኝ ወታደሮች በቁጥር በበዛው የስዌይን ሰራዊት ተደቆሱ።

ንጉሥ ሃራልድ ብሉቱዝ በሰይፍ እየተከላከለ ሳለ፣ በጫካው ውስጥ የተሸሸገ አንድ የስዌይን ቀስት ወርዋሪ መርዛማ ቀስቱን አዘጋጀ። ቀስቱ ተለቀቀች። የሃራልድን ትከሻ ሰንጥቃው ገባች። ንጉሡ በከባድ ህመም መሬት ላይ ወደቀ። ታማኝ ወታደሮቹ ንጉሣቸውን በቁስለኛነቱ ተሸክመው በጨለማ ወደ ጫካው ሸሹ።

የቆሰለው ንጉሥ ወደ ፖሜራኒያ (የአሁኗ ፖላንድ የባህር ዳርቻ) በምስጢር በጀልባ ተሻገረ። ይሁንና ቀስቱ ያስከተለው ቁስል ሊድን አልቻለም።

ባረፈበት ምስጢራዊ ክፍል ውስጥ ሆኖ፣ ሃራልድ የመጨረሻ ትንፋሹን እየወሰደ ለታማኝ አገልጋዩ እንዲህ አለው፦
"ሀገሬን አንድ አደረግኳት... ህዝቤን ከጨለማ አወጣሁ... ነገር ግን የገዛ ማህፀኔ ፍሬ ጠላቴ ሆነ።"

በ986 ዓ.ም. ታላቁ የቫይኪንግ ንጉሥ ሃራልድ ብሉቱዝ በስደት አለፈ። አስከሬኑም በምስጢር ተወስዶ በገነባት የጄሊንግ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀበረ። ልጁ ስዌይን ፎርክቤርድ ዙፋኑን ወረሰ።

የሚገርም እውነታ፦ ዛሬ በስልካችንና በኮምፒውተራችን የምንጠቀምበት ብሉቱዝ (Bluetooth) ቴክኖሎጂ የተሰየመው በዚህ ንጉሥ ስም ነው! ልክ ንጉሥ ሃራልድ ብሉቱዝ የስካንዲኔቪያን (ዴንማርክና ኖርዌይን) ጎሳዎች አንድ እንዳደረገ ሁሉ፣ የብሉቱዝ ቴክኖሎጂም የተለያዩ የኮምፒውተርና የስልክ መረጃዎችን አንድ ላይ ስለሚያገናኝ በስሙ ተሰይሟል። የብሉቱዝ ምልክት (ß) ራሱ የሃራልድ ብሉቱዝ ስም የመጀመሪያ ፊደላት የቫይኪንግ ጥንታዊ ጽሕፈት (Runes) ውህደት ነው።


https://t.me/mtuk_hasab
https://t.me/mtuk_hasab
🤩4
"አቧራ የተገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አደለም። የሰውንም ስህተት የምትነግረው ስህተቱን እንዲያርም እንጂ ሰውየው በስራው ተስፋ እንዲቆርጥ አደለም።"

_ አበው _



https://t.me/mtuk_hasab
👍4
ንጉሱ ብልሀት እና የማረው እስረኛው

በአንድ ወቅት ወንጀል የሚሰሩ አመፀኞች ተይዘው ሲታሰሩ በግራ ቀኝ እጃቸው መቅዘፊያ ይዘው በጉልበታቸው ኃይል እየቀዘፉ የመንግሥትን መርከቦች በባሕር ላይ እንዲነዱ ይገደዱ ነበረ፡፡ አንድ ቀንም አንድ ንጉስ÷ ክፉ ስራ የሰሩ ወንጀለኞችን ታስረው ወደሚገኙበት መርከብ ገባ፡፡ እስረኞቹም የታሰሩበትን ከባድ ሰንሰለት ሲመለከት እጅግ አዘነላቸው፡፡ በልቡም "ከእነዚህ አንዱን ልፍታ" ሲል አሰበ፡፡

መፈታት የሚገባውንም ለማግኘት "አንተ! ወደዝህ የመጣህበት ምክንያት ምንድነው?" እያለ እያንዳንዱን እስረኛ ሲጠይቅና ሲመረምር÷ እያንዳንዳቸው እጅግ እያዘኑ "ምንም ሳላጠፋና ሳልበድል ክፉ ሰዎች ነገር ሠርተው ወደ ሹማምንት አደረሱኝ እንጂ ከተባለብኝ ነገር ንፁሕ ነኝ÷ ጌታዬ ሆይ! ምህረት አድርጉልኝ ከዚህም ስፍራ ያውጡኝ" እያሉ አጠንክረው ለመኑ፡፡

ንጉሱም እያለፈ ሲመረመር ወደ አንድ ወጣት ጎበዝ ደረሰና "አንተስ ምን አድርገህ ነው?" ሲለው ወጣቱ መልሶ÷ "ምህረተኛ ጌታዬ ሆይ÷ እኔ እጅግ ክፉ አሽከር ነኝ ለአባቴና ለእናቴ አልታዘዝም በማለት ብዙ ጊዜ ኮበልኩባቸው በጣም ክፉ ሥራም ሰራሁ ፣ ሰረቅሁ ፣ አታለልሁም ያደረግሁትን ክፋት ሁሉ ዘርዝሬ ለመተረክ እጅግ ብዙ ነው የተገባኝን አግኝቻለሁ ይህን ቅጣት ደስ እያለኝ እሸከማለሁ ከዝህ ሺህ ጊዜ የሚበልጥ እንደሚገባኝ ተረድቻለሁ" ብሎ እውነቱን የሰራውን ሀጥያት ተናዘዘ፡፡

ንጉሱ ግን እያንዳንዱ እስረኛ ለጥፋቱ የተገባውን ቅጣት እንደተቀበለ አረጋግጦ በቀልድ ሲነግራቸው "ኧረ በእነዚህ ደጋግ ሰዎች እንዳያበላሽ ቢወጣ ይሻላል!!" በማለት በክፉው ስራው አፍሮ ለተናዘዘው ሰው ምህረት አደረገለት፡፡
እርሱም ደስ ብሎት ሄደ፡፡

https://t.me/mtuk_hasab
3🏆3
አንዳንድ ጊዜ በህይወት ውስጥ "አላውቅም" ማለት እራሱ መልስ ነው። ሁሉም ነገር ግልፅ መሆን የለበትም። ግራ መጋባት የመማር አንዱ ክፍል ነው። ዛሬ ባይገባህ፣ ነገ ይገባሃል።

Relax!😊
🔗Join - @mtuk_hasab
🔥4🎉1
👉 ስለ ፍርሃት ማወቅ ያለብህ 3 ነገሮች፦

1.ፍርሃት ውሸታም ነው፦ ፍርሃት ሁልጊዜ "አትችልም፣ ትወድቃለህ፣ ይሳቁብሃል" ይላል። ነገር ግን አንዴ እርምጃ ስትወስድ ፍርሃቱ እንደ ጭጋግ በኖ ይጠፋል።

2.የስኬት ምልክት ነው፦ የምትፈራው ነገር ካለ፣ ያ ነገር ለእድገትህ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ምልክት ነው። ፍርሃትህ ወዴት መሄድ እንዳለብህ ያሳይሃል።

3.ድፍረት ማለት አለመፍራት አይደለም፦ ድፍረት ማለት እየፈራህም ቢሆን እርምጃ መውሰድ መቻል ነው።

ከምጡቃን አንደበት
🔗share - @mtuk_hasab
🔥4👍1
🙏 ያለህን ቁጠር

ብዙ ጊዜ የሌለንን ነገር ስንቆጥር፣ ያለንን እንረሳለን። • የሚመታ ልብ ❤️ • የሚተነፍስ ሳንባ 🫁 • ተስፋ ያለው አእምሮ 🧠

እነዚህ ተአምር ናቸው። ሌላው ይደርሳል።

ተመስገን ብለህ ተኛ። ነገ ሌላ ቀን ነው!

https://t.me/mtuk_hasab
👌32
ከምታምነው በላይ ጀግና ከምትገምተው በላይ ጠንካራ ከምታስበው በላይ ብልህ ከምትመኘው እጥፍ ቆንጆ መሆንህን አትርሳ!

#ሩሚ

https://t.me/mtuk_hasab
https://t.me/mtuk_hasab
🙏3
ወገን መረጣችሁ? 😂😂
🤣4👏2👍1🥰1
Forwarded from ꧁༒☬ INFINITY ☬༒꧂ (📚𝖙ⓞя𝖕𝕒🧣▿▻🌬🏴‍☠)
የቤቱ ግርግዳ ላይ የእመብርሐን ምስለ-ስዕል ሰቅሏል....ሲገባና ሲወጣ ጭንቁን ያዋያታል።

አንድ ቀን ተንበርክኮ የወደዳትን ልጅ ትሰጠው ዘንድ ምስለ-ስዕሏን እያዬ ለመነ....ተደረገለት ፤ የወደዳትን አገኘ!...

የእመብርሐንን ምስለ-ስዕል አውርዶ የሷን ፎቶ ከግርግዳው አኖረው....ደመወዙን ሲቀበል ለቤተክርስቲያን የሚሰጠውን አስራት ትቶ ፀጉሯን እንድትሰራበት ይልክላት ጀመረ...!

ከጊዜ በኋላ እሷም ሄደች....እሱም
ማርያምን ብሎ መማሉን ተወ...

✍🏽ኪሩቤል


#𝕚𝕟𝕗𝕚𝕟𝕚𝕥𝕪

Join🥰🥰🥰
https://t.me/itsinfinity0
🙏51
Forwarded from Bethel Support
እንዴት ናቹህ  ቤተሰብ 👋
ዛሬ ደሞ  አስገራሚ ቻናል  ላሳያችሁ   ቻናሉ  ትዕማር  ይባላል  በውስጡ እንደ ስሙ  ማር ማር  የሆኑ  አጫጭር እንዲሁም እረጃጅም ታሪኮችን  ከቅመም ከሆኑ  ግጥሞች ጋር በተጨማሪም የተለያዩ  ትዝታዎች እያነሳ   ያጋራችዋል  ታሪክን በእውቀት ቀላቅሉ  የሚያጎርሰን  ቻናል ነው አሁኑኑ  ተቀላቀሉ👇👇
https://t.me/tehmar2
🥰5😁1
አእምሮህን የሚቀይሩ ህይወትህን የሚገነቡ ጥልቅ ይዘቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት እንደምትችሉ ብነግራችሁስ?

​ይህ ቻናል የኔ ምርጦች ከምላቸው አንዱ ነው!
📚 የታላላቅ መጽሐፍት ዳሰሳ
🏛 ጥልቅ ፍልስፍናዎችን በታዋቂ አንደበቶች የሚያስረግጥ
🌎 ህልውናችንን የሚጠይቅ እና እራሳችሁን ከተገደበው እይታ አሳልፎ የሚያሳያችሁ
​ጊዜያችሁን ከንቱ ከማባከን ወጥታችሁ እራሳችሁን ማሳደግ ለምትፈልጉ ሁሉ ይሄንን ቻናል ጋብዣችኋለሁ ዛሬውኑ ተቀላቀሉት
👉 @viper_progress
2🙏2
አትስረቅ ብሎ ሚያስተምረው አካል ከሰረቀ ፣ አታመንዝር ያለውም ካመነዘረ፤ ተፋቀሩ ያሉት ከተጣሉ ፣ አንድ ሁኑ የሚሉት ከተከፋፈሉ ፤ ሁላችንም አንድ የፈጣሪ ልጆች ነን የሚሉት በዘርና በጎሳ ከተባሉ ፤ የመነኑት የስልጣን ጥም ከያዛቸው ፤ ሞተዋል የተባሉት የየራሳቸው ቪላ ከገነቡ ፤ የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ የያዙት የቢሮውን ቁልፍ ከዘጉ ፤ ሌላ ልሳን እንናገራለን እያሉ የህዝቡን ልሳን ካላዳመጡ  ፤ የነገው ትንቢት ተገለጠልን እያሉ የዛሬው ችግር ከጠፋቸው ፤ በሽተኛ እንፈውሳለን እያሉ እነርሱ ራሱ ማይፈወሱ በሽተኞች ከሆኑ ፤ እንግዲህ "ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል ፣ ውሃ ቢያንቅ በምን ይውጡታል "የተባለው ደርሷል ማለት ነው።

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

https://t.me/mtuk_hasab
😢3😁21
ለተሳሳተ ሰው መሳሳቱን መንገር ፈራጅ መሆን ነው??፤ የሚያውቁትን ማስረዳትስ መታበይ ነው??..
🔥2
ሞኝን ሁለቴ እባብ ነደፈው.....ሚለው ደረሰብኝ 😂
🐳5
"መቻል እንደምትችል ካመንክ ወይንም እንደማትችል ካሰብክ፤ በሁለቱም ልክ ነህ።"

— ሄንሪ ፎርድ

💡ውጤቱ የሚወሰነው ከውጭ ባለው ተጽዕኖ ሳይሆን ከውስጥህ ባለው እምነት ነው። ዓለም "አትችልም" ቢልህ እንኳ አንተ "እችላለሁ" ካልክ መንገዱ ይከፈታል።
ትልቁ እስር ቤት የአእምሮህ "አልችልም" ባይነት ነው።


🔗share - @mtuk_hasab
1🥰1
😅ጥርሳችሁ እስኪያገጥ ድረስ  ነዉ የምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰባብሮ ክፈል የለም 😁 request ላኩና አብረን እንሳቅ

https://t.me/+CniYkmZC_sE5NGY0
https://t.me/+CniYkmZC_sE5NGY0
😁1💯1