ዜና እረፍት
የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወንድማችን ዲያቆን ፋሲል አለማየሁ በእህታቸው ወይዘሮ ወርቅዬ አለማየሁ ኅልፈት ከትናትናው ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬው የቀብር ጊዜ ድረስ አብረው በመሆን ያጽናኗቸውን ዘመድ ወዳጆች አመስግነዋል።
ይልቁንም የአድባራቱን አገልጋዮች ላደረጉላቸው መልካም አገልግሎት ወንድማዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የእህታችንን ነፍስ በዓጸደ ቅዱሳን ያሳርፍልን።
#MSKLideta
#ቅድስት_ልደታ
#ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

❤1👍1
ጸሎተ ሐሙስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ቁርባንን የሰራባት ይህች ዕለት ክብርት ናት። ለሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ህይወት የሚሆነውን ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን እንካችሁ ብሎ የሰጠን በዚህች ዕለት ነውና።
ዳግመኛም ጌታችን በትህትና ዝቅ ብሎ የሐዋርያትን እግር አጥቦ ከእርሱ ጋራ በሰማያት ያለንን ክፍል ያስተማረበትና ትሕትና የክርስትና መሰረት መሆኑን "አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ" ብሎ ያጸናበት አስተምህሮ ይታሰብባታል።
ይህ በዓል በማኅደረ ስብሕት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን ክቡር አስተዳዳሪው ቆሞስ መልአከ ስብሐት አባ ገብረ ሥላሴ አማረ በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።
በነገው ዕለተ የጌታችን የስቅለት መታሰቢያ በዓል ትውፊቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአድባራቱ የሚከበር ሲሆን መላው ህዝበ ክርስቲያን በዕለቱ በመገኘት በዓሉን በአንድነት እናከብር ዘንድ መንፈሳዊ መልእክታችንን ከወዲሁ እናስተላልፋለን።

❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተዝካረ ስቅለቱ ለመድኃኔ ዓለም
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተዝካረ ስቅለት በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን ተከብሮ ውሏል።
በዕለቱም ለቁጥር የበዙ ህዝበ ክርስቲያን በቅጽረ ግቢው አራቱ ማዕዘን ከውስጥና ከውጪ በመሆን መንፈሳዊ ስርዓቱን ሲፈጽሙ ውለዋል።
የጸሎቱ መርሐ ግብር በአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ አማረ የተመራ ሲሆን ዕለቱን የተመለከተ ቃለ ወንጌልም በሰፊው ተሰጥቷል።
በምእመናንን የተከበበችው ታላቂቷ ደብራችን መጪውን የትንሳኤ በዓልና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓልን ለማክበር እየተሰናዳች ትገኛለች።
ከወዲሁ መላው ህዝበ ክርስቲያን በአድባራቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የስቅለት በዓል በሰላም እና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ይከናወን ዘንድ የአድባራቱ ካሕናትና ሊቃውንት ፣ የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችና ይልቁንም አካባቢውን በማጽዳትና ለምእመኑ ምቹ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡት የአጥቢያው ወጣቶች ምስጋና እናቀርባለን።

👍3
#ልደታ_ለማርያም
በዘመነ ብሉይ ነቢያቱ በብዙ ኅብረ አምሳል የመሰሏት ፣ ጌታን ለመውለድ የበቃች ሆና የተገኘች ፣ ከፍጥረታት ሁሉ የስጋና የነፍስን ድንግልና የያዘች ንጽህት ድንግል ማርያም በሊባኖስ ተራራ ግንቦት አንድ ቀን ከፀሐይ እና ከጨረቃ ሰባት እጅ አብርታ ፣ ለጨለመው ዓለም ብርሃን ትሆነው ዘንድ ተወልዳለች።
አስቀድሞ ነቢዩ ሰሎሞን በመሐልዩ "ለእናቷ አንዲት ናት" ብሎ እንደተናገረላት በምክነት ለነበሩት ለሀና እና ለኢያቄም የደስታቸው መፍሰሻ ትሆን ዘንድ ከመርገመ ሔዋን ንጽህት ሆና ተወለደች።
የእመቤታችን መወለድ ለዓለም ሁሉ ታላቅ የምስራች እና ደስታ ነው። የዓለሙን ንጉስ ለመውለድ የተመረጠችው ንጽህት ድንግል በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንደተነገረላት የደስታ ምንጭ ናትና።
ይህ የከበረ በዓል እንደ ወትሮው ሁሉ በከተማችን ያሉ ህዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በታላላቆቹ አድባራት ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን ከዋዜማው ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።
ከሚያዝያ 27 ጀምሮ እስከ ግንቦት 1 ቀን ድረስ ደግሞ በአድባራቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ፣ በተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤትና በአጥቢያው ወጣቶች አስተባባሪነት ዐቢይ ጉባኤ ተዘጋጅቷል።
ስለሆነም መላው ህዘበ ክርስቲያን የእመቤታችንን ልደት በቤቷ ተገኝተን እናከብረው ዘንድ ከወዲሁ መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

👍2
ሰኔ ፩
በዓለ ጰራቅሊጦስ ከእመቤታችን የልደት በዓል መታሰቢያ ጋር በአንድ ውሏል። የሰኔ የመጀመርያ መዓልትም በዕለተ እሁድ (አሚሩ ለሠርቀ ዕለት) አንድ ብሎ ጀምሯል።
ይህን የከበረና የመንፈስ ቅዱስን ርደት የምናስብበትን በዓል ከእመቤታችን የልደት መታሰቢያ በዓል ጋር በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን በመገኘት ያከብሩ ዘንድ ከወዲሁ መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

❤3
ተዝካረ በዓሉ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
ሰኔ ፲፪ ቀን የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል ይከበራል። ይህ በዓል በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን ታቦታተ ህጉም ከመንበረ ክብራቸው በመነሳት ህዝበ ክርስቲያኑን ይባርካሉ። ሁላችንም በዕለቱ በመገኘት በዓሉን እናከብር ዘንድ ከወዲሁ መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

❤8
ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት በአድባራቱ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ አባቶችን የሚዘክር ሲሆን በ2017 ዓ.ም ወርኃ ጳጉሜን መባቻ በአድባራቱ ለረጅም ዓመታት የቅኔ እና የመጽሐፍ መምህር በመሆን ያገለገሉትን መምህር ዘካርያስ አምባውን የሚዘክር ይሆናል።
መምህር ዘካርያስ አምባው ለመምህርነት ከተሰየሙበት 1949 ዓ.ም ጀምሮ ለ68 ዓመታት ያለ ድካምና መሰልቸት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር የቅኔ ፣ የመጽሐፍና የዘመን ቀመር ትምህርቶችን አስተምረዋል።
በዘመናቸውም ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ መነኮሳትን ፣ መምህራንን እና በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል።
ጳጉሜን አንድ ቀን 2017 ዓ.ም በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የአስተዳደር ህንጻ አራተኛ ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ በመገኘት ታላቁን የቤተ ክርስቲያን ሊቅ መምህር ዘካርያስ አምባውን እና በህይወተ ስጋ የተለዩንን አባቶች እንድንዘክር መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት

❤7
ዝምተኛው ሊቅ
በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን ለረጅም ዓሰርት ዓመታት ያለ ድካምና ያለመሰልቸት ሲያገልግሉ የነበሩት ሊቁ ሊቀ ጠበብት አእመረ ጸጋዬ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ዝምተኛ ሊቅ ፣ የማኅሌት ሞገስ ፣ የመዝገብ ቅዳሴ መምህር ፣ የአቋቋም ተጠያቂ ፣ የቅኔ መድበል ፣ ሐታቴ መጻህፍት ነበሩ። ሊቅነታቸው ከአድባራቱ ባሻገር ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን አድባራትና ገዳማት በመጽሐፍ የተገለጠ ነው።
ስርዓተ ቀብራቸው በታላላቆቹ አድባራት ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያን በነገው ዕለት ማለትም 19/02/2018 ዓ.ም ይፈጸማል።
የህይወት ታሪካቸውን እና የስርዓተ ፍትሐቱን መርሐ ግብር በዚሁ ገጽ ላይ የምናሳውቅ ይሆናል። መላው የአድባራቱ አገልጋዮችና የአስተዳደር ክፍል ሰራተኞች በአባታችን ኅልፈት የተሰማንን ታላቅ ሀዘን ለመግለጽ እንወዳለን።

😭5❤2
በመስቀልከ ወበቃልከ ይባርኩከ ጻድቃኒከ ፤ ስብሐት ይብሉ ለመንግስትከ
ጌታችን ሆይ! ስለ መስቀልህ እና በመስቀል ላይ ስለተናገርከው ቃል ጻድቃን ሁሉ ያመሰግኑሃል። ለመንግስትህም ምስጋናን ያቀርባሉ።
አቡን ዘምኩራብ
#MSKLideta
#ቅድስት_ልደታ
#ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
ጌታችን ሆይ! ስለ መስቀልህ እና በመስቀል ላይ ስለተናገርከው ቃል ጻድቃን ሁሉ ያመሰግኑሃል። ለመንግስትህም ምስጋናን ያቀርባሉ።
አቡን ዘምኩራብ
#MSKLideta
#ቅድስት_ልደታ
#ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
❤4
መጋቢት ፩
ዛቲ ይእቲ ኢየሩሳሌም ማኅደረ ስብሐት ሀገሮሙ ለነቢያት
"ይህች የነቢያት የሊቃውንት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ማኅደረ ስብሐት ናት!"
የመጋቢትን አሚሩን ከታላቁ ጾም ጋር የእመቤታችንን ወርኃዊ የልደት በዓል መታሰቢያ ጋር ተቀብለነዋል። ወሩን የበረከት ያድርግልን።

❤5