Ministry of Trade and Regional Integration-Ethiopia
20K subscribers
5.63K photos
17 videos
13 files
851 links
An Official Channel of Ministry of Trade and Regional Integration. ይህ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር ኦፊሴላዊ ቻናል ነው።
Download Telegram
ሀገራዊ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ዘርፍ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
==============

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ)የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "ቀጣናዊ ትስስር እና አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለንግድ ዘርፍ እድገት" በሚል መሪ ቃል ከክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሃላፊዎች፣ ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የዘርፉን የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው።

በግምገማ መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በዘርፍ ደረጃ እየተገናኙ በመገምገምና አፈፃፀምን እያጎለበቱ ካሉ በመጀመሪያው ረድፍ ከሚገኙ ተቋማት አንዱ የንግዱ ሴክተር ነው ያሉ ሲሆን በዚህም በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበናል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘው እንደገለፁት በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና እየተገኘ ላለው ውጤት የንግዱ ሴክተር ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሴክተሩን ለማዘመን የተሳለጠ የግብይት ስርዓት ለመፍጠር እንዲሁም የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከተሰሩ የአሰራር ስርዓት ግንባታዎች ውስጥ የንግድ ፖሊሲና የጥራት ፖሊሲ የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ተዘጋጅተው ለውሳኔ የቀረቡ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተደራሽ ያደረገ የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት መሰጠቱንና አፈፃፀሙ ከ100% በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከክልል ንግድ ቢሮዎች ጋር በተሰራው የቅንጅት ስራ በአገር ደረጃ በ2.2 ሚሊዮን የንግዱ ማህበረሰብ ላይ የድረ ፍቃድ ኢንስፔክሽን ስራ በማካናወን ከእቅድ በላይ ፈፅሠናል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የተደረገውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስተዳደር ለውጥን ተከትሎ በተከሰተው ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከ110 ሺ በላይ ነጋዴዎችና የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ማረጋጋት ተችሏል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ 9ወራት 374 በላይ አዳዲስ የቅዳሜና እሁድ ገበያ መጨመር የተቻለ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ የነባሮቹንም ደረጃ የማስጠበቅ ስራ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል፡፡

ከወጪ ንግድ አፈፃፀም አንፃር ባለፉት 9 ወራቱ 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ይህም በ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው የላቀ አፈፃፀም መሆኑን በበጀት ዓመቱ ወደ 6 ቢሊዮን ገቢ ለማስገኘት እየተሰራ ነውም ብለዋል።

የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ሂደትን በተሳካ ሁኔታ እያካሄድን ነው ያሉት ሚኒስትሩ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመጀመር ከአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ጋርም የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት መፈራረም ጀምናል ብለዋል።

ጥራትን የማስጠበቅ ስራ ከማምረት የሚጀምር መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ

በጥራት መንደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተደራሽነት የማስፋትና በወጪና ገቢ ምርቶች ላይ የተደረገው የጥራት ቁጥጥር ሌላው ውጤት የታየበት ዘርፍ ነውም ብለዋል።

ለተጨማሪ መረጃ
Email: fdremotri@gmail.com

fdremotri@motri.gov.et
Facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
telegram channel :https://t.me/motri_gov_et
https://t.me/etrade_gov_et
https://www.youtube.com/Ethiopian Ministry of Trade& Regional Integration
Facebook (https://www.facebook.com/)
Twitter: https://x.com/MoTRI_Ethiopia
Tiktok: https://www.tiktok.com/@ethiopianministr
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርማችን መሳካት የበኩላችንን ድርሻ በብቃት ለመወጣት ያስቻሉን ውጤቶችን አስመዝግበናል- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር)

===================================
አዲስ አበባ 21/08/2017ዓ.ም (ንቀትሚ) “ቀጣናዊ ትስስር እና አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለንግድ ዘርፍ እድገት! ” በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርማችን መሳካት የበኩላችንን ድርሻ በብቃት ለመወጣት ያስቻሉን ውጤቶችን አስመዝግበናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ ከሃገር ውስጥ ንግድ አፈጻጸም አንጻር በኦንላይን ከ2.6 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች ለንግዱ ማህበረሰብ የተሰጡ ሲሆን አዲስ ንግድ ፍቃድ ማውጣት፣ የንግድ ምዝገባ፣ ነባር የንግድ ፍቃድ ማደስና መሰል አገልግሎት በኦንላይን የተሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘንድሮ በጀት አመት በክልሎች በተጀመረው የድህረ ፈቃድ አንስፔክሽን አገልግሎትም ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የንግድ ፈቃድ እንስፔክሽን የተከናወነ ሲሆን ከእቅድ በላይ መፈፀም እንደተቻለ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

ጠንካራ የነዳጅ ግብይት ሬጉላቶሪ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር አላግባብ ለመክበር በተንቀሳቀሱ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት የተጣለ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የሲሚንቶ ግብይት አሰራርን በማሻሻል የሲሚንቶ ዋጋ ከግማሽ በታች ከመቀነስ ባለፈ ለብዙሃን በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ እስከ ነገ እንደሚቀጥል ይጠበቃል::

ለተጨማሪ መረጃ
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
Facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
telegram channel :https://t.me/motri_gov_et
https://t.me/etrade_gov_et
https://www.youtube.com/Ethiopian Ministry of Trade& Regional Integration
Facebook (https://www.facebook.com/)
Twitter: https://x.com/MoTRI_Ethiopia
Tiktok: https://www.tiktok.com/@ethiopianministryoftrade