Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
20.5K subscribers
2.82K photos
80 videos
13 files
428 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር

የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ የሚደረግ ቁጥጥር

ፍቃድ በተሰጠው አምራች ፊብሪካ ውስጥ የሚገኙ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው

ዕቃዎች በታክስ ባለሥልጣኑ የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ቁጥጥር የሚደረገው ከሚከተለት በቀደመው ጊዜ ይሆናል:-
— ፈቃድ በተሰጠው አምራች ፊብሪካ ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከፋብሪካው እስከሚወጡ፣
— ዕቃዎቹ ከኢትዮጵያ ውጪ እስከሚላኩ፣ ወይም
— ዕቃዎቹ ከአገልግሎት ውጪ እስከሚደረጉ ወይም እስከሚወገዱ ድረስ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/wecy0h
"ገቢያችን ህልውናችን" (15ኛ ዓመት የሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም ቁጥር 172 እትም ጋዜጣ)
ግንቦት 12/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
"ገቢያችን ህልውናችን"በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እየተዘጋጀች የምትሰራጭ ወርሃዊ ጋዜጣ ስትሆን ጋዜጣዋን ለማገኘት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://rb.gy/50kv8i
የስትራይድ ኢትዮጵያ 2016 ( STRIDE Ethiopia 2024) አመታዊ ኤክስፖ ጉብኝት

ግንቦት 14/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒሰቴር አመራሮችና ሰራተኞች የስትራይድ ኢትዮጵያ 2016 (STRIDE Ethiopia 2024) አመታዊ ኤክስፖ ጎብኝተዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሳይስ ሙዝየም እየተካሄደ በሚገኘው የስትራይድ ኢትዮጵያ 2016 (STRIDE Ethiopia 2024) አመታዊ ኤክስፖ ጉብኝት ተሳታፊ የሆኑ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሠራተኞችም ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጽው የገቢ አሰባሰቡን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ በማድረጉ ሂደት እንደሀገር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://www.facebook.com/ERCA.info/posts/758403769797356?ref=embed_post
"ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ያግዛል" - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም(የገቢዎች ሚኒስቴር)

ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ሚናው የላቀ ነው ሲሉ
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለፁ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ገቢዎች ቢሮ ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሃግብር ተከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከግብር ከፋዮች የሚሰበሰበው ሀብት የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በሁለት ዓመታት ውስጥ ገቢን ለመሰብሰብ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል። ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ለግብር ከፋዩ የማመቻቸት ስራ መሰራቱንም አንስተዋል።

ግብርን የሚሰውሩ አንዳንድ ግብር ከፋዮች መኖራቸውንና የግብር ከፋዩ መረጃ አያያዝ አለመዘመን መሠረታዊ ችግር መሆኑን ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ እነዚህን ማረምና ማስተካከል ይገባልም ብለዋል።

ግብራቸውን በታማኝነት በመክፈል ለዕውቅና የበቁትን ተሸላሚዎች በክልሉ መንግስትና በራሳቸው ስም አመስግነዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ ታክስ የመንግስትን ወጪ ፍላጎት ለማሟላት ፣የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ለማስፈን ፣ንግድና ኢንቬስትመንትን ለማበረታታት የሚያገለግል የፊስካል መሳሪያ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተሻለ የተፈጥሮ ጸጋ ያለበት ክልል እንደመሆኑ መጠን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በጨመረ ቁጥር ትልቅ የገቢ እምቅ አቅም ያለበት ክልል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ የክልሉን ገቢ ለማሳካት ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ያሰፈልጋል። ግብርን በፈቃደኝነት አሳውቆ የመክፈል መርህን የሚከተል የታክስ አስተዳደር ስርዓት እየተገነባ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።

በክልሉ 60 ሺህ ግብር ከፋዮች እንደሚገኙና ሚናቸውም ከፍተኛ መሆኑን ተገልጿል።

እያደገ የመጣውን የግብር ከፋይ ቁጥር በማሰልጠን የገቢ ህጎችንና አሰራሮችን ግብር ከፋዩ እንዲረዳ በማድረግ በተሰራው ስራ በ10 ወራት ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

ከክልል ጀምሮ እስከ ታክስ ማዕከላት ከወጣትነት ጀምሮ በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ በጡረታ ከተሰናበቱ ሰራተኞች ወደ ቢሮ የተቀላቀሉ ወጣት ሰራተኞች ከእናንተ ከሙስናና ብልሹ አሰራር ርቆ ማገልገልን ሊማሩ ይገባልም ብለዋል።

በዕለቱም ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች ከክብር እንግዶች እጅ የተዘጋጀላቸውን የእውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል።