Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
20.5K subscribers
2.84K photos
80 videos
13 files
435 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ዋና ዋና አፈጻጸም እና የቀሪ ጊዜያት ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዋና ዋና አፈጻጸም እና የቀሪ ጊዜያት ተግባራት ዙሪያ በተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ደረጃ በዛሬው እለት ውይይት ተካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ቱሉ ሲሆኑ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገቱን ለማሳካት በተለይም የገቢ አሰባሰብ ተግባርን በየጊዜ እየገመገሙ እና ውጤታማ አሰራርን እየተከተሉ መሄድ ይገባል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/rxy8c2
የኤክሳይዝ ቴምብር የሚለጠፍባቸው እቃዎች

- በኤክሳይዝ ቴምብር አስተዳደር ስርዓት መመሪያ ቁጥር 1004/2016 መሰረት የሚከተሉት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሲመረቱ ወይም ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ የተለየ መለያ የያዘ የኤክሳይዝ ቴምብር ሊለጠፍባቸው ይገባል፡-

ሀ) የአልኮል መጠጦች፣
ለ) አልኮል እና አልኮል አልባ ቢራ፣

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/qxjbgw
በጊዜያዊነት ወደ አገር በገባ እቃ ያለአግባብ መገልገል

በጊዜያዊነት ወደ አገር በገባ እቃ ያለአግባብ መገልገል ከሚያስከትላቸው ቅጣቶች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ማንኛውም ሰው ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ ያስገባውን እቃ ተመሳሳይ መብት ለሌለው ሶስተኛ ወገን በኪራይ ወይም በሽያጭ ወይም በሌላ ማንኛውም ሁኔታ ያስተላለፈ እንደሆነ በዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ መከፈል ያለበትን ቀረጥና ታክስ መክፈል አለበት፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/p7od73
ተቋማዊ ውጤታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ሊያረጋግጥ የሚያስችል ረቂቅ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀረበ

ሰኔ 14/10/2016 ዓ,ም( የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴርንና የጉምሩክ ኮሚሽንን ተቋማዊ ውጤታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ሊያረጋግጥ የሚያስችል ረቂቅ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ በዛሬው ዕለት ለውይይት ቀርቧል፡፡

ውይይቱ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴን ጨምሮ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች የሁለቱ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በተገኙብት ተካሂዷል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://rb.gy/q5ojye
ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ስለመሆን

ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ ከመቀጠር ከሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነጻ የሚሆኑባቸው ሁኔታዎች አሉ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-¬

— ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
— በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
— በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/s84gb8