ፍቅር ብቻ
55 subscribers
195 photos
4 videos
5 links
አንብብ አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። አንብብ ብታነብ የሚርቅህ ድንቁርና ነው ታድያ በፍቅር

ጥበብን የምንዳስስበት መድረክ
Download Telegram
people who spell

አንተ - anta
ማሬ - mara
ውዴ - wda
እኔ - ena

ከግብፅ በላይ ያበሽቁኛል😭

#Sorry😁
ባለፈው ሳምንት የፍቅረኛዬ 🎂🎂ልደት ነበር።ለልደት ስጦታ ምን ልስጥሽ ብዬ ስጠይቃት። ቢያንስ አመቱን ሙሉ የምጠቀምበት ነገር ብትሰጠኝ ደስ ይለኛል ። አለችኝ። እኔ ያው እንደምታውቁት ጂንየስ 😏😏አይደለሁ። ካላንደር ገዝቼ ሰጠኋት። ከዚያ ጀምሮ ስልኬን📞📞 አታነሳም። እሺ ምን አጠፋሁ??

@mnteb 🤷‍♂😂😂😉
ዳቦ 75 ሳንቲም
ሻይ 5 ብር
.
.
.
.
ያላቻ ጋብቻ ሚባለው ይሄ አይደል😏😏😂

@mnteb
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።‼️⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው “ውድ ህይወት አጥተናል” ብለዋል።

“የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሀዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁም” ነው ያሉት ።

የዚህን ክፉ ድርጊት ሙሉ የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት እየተጠባበቅን እንገኛለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የድርጊቱን መጠን በመረዳት በሀገራችን ውስጥ ስለሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ሀዘናችንን ራሳችንን በመጠበቅ እና ተጨማሪ ወንጀልን በመከላከል እንግለፅ ሲሉም አሳስበዋል።

@mnteb
ለቀደሙት አትግደል እንደ ተባለ ስምታችኃል የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል:: ማቴ 5:-21
እግዚአብሔር የሰው ልጆች ሕይወት ጠባቂ ስለሆን ነው ይህንን ሕግ የሰጠን በዚህ ጉዳይ እጃችሁን ያስገባችሁ የእነዚህ ምንም የማያውቁ የልጆች አምላክ እርሱ ፍርድን ይስጣችሁ ነብሱን ይማርልን ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጥልን::

@mnteb
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 1 month. If it remains inactive in the next 9 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.
Corona VIRUS Defensiv
።።።።
በሆስፒታሎች (በለይቶ ማከሚያ ) እየተወሰዱ ያሉ መድሀኒቶች
1.ቪታሚን c 1000
2.ቪታሚን E
3.ለ 10...11 ሰአታት ለ,15ደቂቃዎች የፀሃይ ብርሃን ላይ መቀመጥ
4 እንቁላል መመገብ
5. እረፍት መውሰድ (ከ7..8 ሰአታት መተኛት )
6.1.5 ሊትር ውሃ በየቀኑ መጠጣት
7.ሁሉም ምግቦች ሞቃት መሆን አለባቸው (ቀዝቃዛ አደለም )
በሆስፒታል ውስጥ የሰውነትን የመከላከል አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ይሄ ነው።
# የኮሮና ቫይረስ ph
ከ 5.5....8.5 ድረስ ተለዋዋጭ ነው
ስለዚህም ቫይረሱን ለመግደል ከቫይረሱ አሲድነት በላይ የሆኑ የበለጠ የ አልካላይን ይዘት ያላቸውን ምግቦች መመገብ ነው
ለምሳሌ
አረንጓዴ ሎሚ....9.9 ph
ቢጫ ሎሚ......8.2 ph
አቮካዶ...15.6 ph
ጋሪክ...13.2ph
ማንጎ...8.7ph
ታንግራይን...8.5ph
ፓይን አፕል ....12.7 ph
ወተር ክረስ...22.7ph
ብርትኳን ....9.2ph
የቫይረሱ ምልክቶች
1.የጉሮሮ ማሳከክ(መቁሰል)
2.የጉሮሮ መድረቅ
3.ደረቅ ሳል
4.ከፍተኛ የሆነ ሙቀት
5.ለመተንፈስ መቸገር
6.ለማሽተት መቸገር
እና ሎሚ በሞቀ ውሀ መጠጣት ቫይረሱ ገና ሲጀምር ሳንባ ጋር ሳይደርስ እንዲገለው ይረዳል ።
ይሄንን መረጃ ለራሳችሁ አታስቀሩት
ለቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁ አጋሩት።
ጥሩ ጤና እና ረጅም እድሜ እመኝላችኋለሁ።

@mnteb
#አንድ_ወንድን_ለስምንት !!

ከቀኑ 12 ሰአት አካባቢ ከባለቤቴ ጋር አቅራቢያችን ወደሚገኝ
መናፈሻ አቅንተን በለምለም ሳሮች መሃል ቁጭ ብለን እየተጫወትን
ከየት መጣ ሳይባል የሚስቴን አንገት መጥቶ ያዛት እሷም ጩኸቷን
ለቀቀችው

ላስጥላት ከተቀመጥኩበት ስነሳ ከስምንት በላይ የሚሆኑ ወጥረው
ያዙኝ ዞር ብዬ ስመለከት በጣም ብዙ ናቸው ለእኔና ለባለቤቴ ይሄ ሁላ
ሰራዊት የሚላክብን በምን ወንጀላችን ነው ስል ለራሴው ጠየኩ !!!

አንገቴን የያዘኝን እንደምንም አስለቅቄ ጣልኩት እሱን ከጣልኩት
በውሃላ ወደ ሰባት የሚጠጉት ወጥረው ያዙኝ በተለይ ብልቴ አካባቢ
የያዘኝን ልቋቋመው አልቻልኩም መጮኽ አቃጣኝ ግን እንዴት ወንድ
ነው ብላ ያገባችኝ ሚስቴ ፊት እንደ ሴት ልጩኽ ?? ዋጥ
አደረኩት !!
.
.
.
.
.
.
ወዳጄ ጉንዳን ክፉ ነው !!
በተለይ ብልትህን ሲይዝህ !!

አሌክስ አብርሀም አይዞህ

Join us👇
@mnteb
​​#ልብ_በል 👇

💛የሆነ ሰዉ መልእክት ልከህለት ካልመለሰልህ ለምን አልመለሰልኝም ብለህ ሌላ አተካራ ዉስጥ አትግባ፡፡ በግድ የሆነ ጓደኝነትና የፍቅር ግንኙነት የትም አይደርስም።

🤍ለነገሮች ትንተና አትስጥ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ሰአት ብቻ እንጂ ስለእያንዳንዱ ነገር ገለፃ የምታደርግ ከሆነ እራስህን ታደክማለህ
ሰዎችን መቼም ቢሆን ለመለወጥ አትነሳ፡፡ ማንም ቢሆን ላንተ ብሎ እራሱን አይቀይርም፡፡ ሲጋራ የሚያጨስን ሰዉ 'አታጭስ' ስላልከዉ ማጨሱን አያቆምም ይልቅስ ለምን ማጨስ እንደማያስፈልገዉ የሚረዳበትን ፍንጭ አሳየዉ...እምቢ ካለ አፈግፍግ

❤️ከራስህና ከሚቀርቡህ ሰዎች ምረጥ ብትባል እራስህን ምረጥ፡፡ ይሄ እራስ ወዳድ መሆን ሳይሆን በከባዱ የህይወትህ ሰአት የራስ ማንነትህ ከሌሎቹ በተለየ መንገድ እንዴት እንዳሳለፈ ያዉቀዋል

❤️አንተ ጋር ብቻ ያለ ፍቅር ከምትወደዉ ሰዉ ዉስጥ ከሌለ እራስህን እያጎሳቆልክ ነዉና አሁኑኑ አቁም
የመጥፎ ባህሪ ድግግሞሽ የህይወት መርዝ ነዉ
ለማንም ቢሆን እራስህን ግልጥልጥ አድርገህ አታሳይ ምክንያቱም 90 ፐርሰንት የሚሆነዉ ሰዉ ማንነትህን እስከጥጉ ካወቀ በደካማዉ ጎንህ መጫወት ይጀምራል

❤️ሰዎች እንደሚወዱህ ቢነግሩህና ጥሩ ለመሆን ብትሞክርም አንተ ላይ መፍረዳቸዉን አያቆሙም

👇ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@mnteb
𝐓𝐡𝐞 𝐝𝐚𝐲 𝐨𝐟 𝐟𝐫𝐢𝐞𝐧𝐝𝐬 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ በህይወትህ ውስጥ የማትረሳቸው (19) ጓደኞችህ እነማን ናቸው?? ለነዚህ (19) ብቻ ይሄንን መልዕክት ላክ እኔ እንዳደረኩት ስንት ሰው መልሶ እንደሚልክልህ እናያለን!!!! በታማኝነት መላክ ጀምር ለ(19) ብቻ !! ምክንያቱም ዛሬ የአለም የጓደኛሞች ቀን ነው ። ጀምር እኔም ከእነሱ መካከል ከሆንኩ ላክልኝ ከ1 ሰው 6መልዕክት በተደጋጋሚ ከደረሰህ/ሽ የምር አንተ በዛ ሰው ተወደሃል ማለት ነው አትጠራጠር @mnteb
#አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ
"እኔ ካህን ነኝ መግደል አልችልም:: በግድ ዝመት ካላችሁኝ ደግሞ ከጦር ሜዳ ውሰዱኝ:: የቆሰሉትን እረዳለሁ:: ለሞቱት ጸሎት አደርጋለሁ:: የወደቁትን አነሣለሁ:: መሞትን አልፈራም:: መግደልን ግን እፈራለሁ"
በዘመነ ሰማዕታት የነበረ ሕጽው ካህን
"የምንቆጥረው ሬሳዎችን አይደለም:: ሰማዕታትን ነው:: ሙታንን ሳይሆን ሙሽሮችን ነው:: ሰማዕታት ሆይ ስለ እኛ ማልዱ" ከአኃው አንዱ
"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ
"ገድዬ እጸድቃለሁ ብሎ ክርስቲያኖችን የሚገድል ሰው የተሳሳተ ቢሆንም ያደረገው ያጸድቀኛል ብሎ ያመነበትን ነው:: እኛ የምናምንበት መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ" ይላል:: ነፍሰ ገዳይ ለሚያምንበት ነገር ከታዘዘ እኛም ለምናምንበት ይቅር ባይነት መታዘዝ አለብን” አቡነ አትናቴዎስ እስክንድር
"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)
"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD)
"የእኛ መሣሪያ ወደ ላይ የምንረጨው ዕንባ ነው:: ፈርዖንን ከነፈረሶቹ ያሰጠመው የኤርትራ ባሕር ሳይሆን የራሔል የጸሎት ዕንባ ነው" ከአኃው አንዱ


@mnteb
ሰው ሆይ
ዛሬ ላይ ምንም ቆንጆ ብትሆን ነገ ልክ እንደዚ አስቀያሚ ነክ፤
ዛሬ ላይ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ ትባላለክ፤
ዛሬ ላይ ምንም ሃብታም ብትሆን ነገ ግን 1ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ፤
ዛሬ ላይ ምንም እንኩዋን በቤተሰብ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን
ትቀራለክ፤
ዛሬ ላይ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፤
ዛሬ ምንም በዘርና በጎሳ ብትመካ ነገ አንተ ብቸኛ ነህ፤
ዛሬ ላይ ምንም ሁን ምን ነገ አንተ ሬሳ ነህ ሬሳ።
ዛሬ ብትናፈቅ ነገ እንዳትሸታቸው ሰዋች ቶሎ ይጥሉካል ፤
ስለዚህ ዛሬ ላይ ለዘለአለም ህይወት የሚጠቅመንን ስራ ብንሰራ መልካም
ነው።
ወደ አምላክ እንመለስ መንገዱንም እሱ ያቅናልን አሜን።



@mnteb
«መፈላሰፍም ሆነ የፍልስፍና ድርሰት ማንበብ ለእብደት አይዳርግም! አንድ ሰው የፍልስፍና መፅሐፍ አንብቦ ካበደ፣ ግለሰቡ ቀድሞውኑ ለማበድ የተዘጋጀበት እርሾ በውስጡ አለ ማለት ነው»
ጋሽ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር

@mnteb

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊