አያቴ ያ ብርቱ !
ላዲስ ትዳር መሻት ፣ ሲቃኝ ልጃገረድ
ህንጣ ሲያስገነባ ፣ ሲያደላድል መንገድ
አቀቡን ቁልቁል ፣ ሲወጣና ሲወርድ
ለፊቱ ሀያ ዓመት ፣ የፖም ዛፍ ሲተክል
እኔ የርሱ ፍሬ ፣ የዘመን ቅምጥል
አዳም በቆመበት ፣ ሶስት አስር ድምሬ
ከቦሌ ሩዋንዳ ፣ እርምጃ ጀምሬ
ታክሲ አስቆማለሁ ፣ መጓዝ ታክቶኝ በግ’ሬ።
:
ብርቱ ሰው አያቴ
ቆሞ ፊት ለፊቴ
ጥቁር ኮፍያ ስር ፣ ሪቫን ለመድገም
ለሶስተኛው ዲግሪ ፣ በሂሳብ ሲጠበብ
እኔ የርሱ ፍሬ
በጓንት እጎርሳለሁ ፣ እጄን ላለማጠብ።
:
አያቴ ያ ብርቱ
ተጨንቆ ለፊቱ
ታሪክ ሲያገላብጥ ፣
መጽሀፍ ሲገልጥ ፣
ኋላውን ሲመዝን ፣ መጪውን ሲለካ
እንቅልፋን ሲገብር ፣ ለዚህ ፖለቲካ
እኔ የርሱ ቅጣይ
የረገፍኩት ዋርካ
የጫቴን ከቻልኩኝ
:
እኔክሽ እኔካ ✌️
(ሚካኤል አ)https://t.me/mk219s
ላዲስ ትዳር መሻት ፣ ሲቃኝ ልጃገረድ
ህንጣ ሲያስገነባ ፣ ሲያደላድል መንገድ
አቀቡን ቁልቁል ፣ ሲወጣና ሲወርድ
ለፊቱ ሀያ ዓመት ፣ የፖም ዛፍ ሲተክል
እኔ የርሱ ፍሬ ፣ የዘመን ቅምጥል
አዳም በቆመበት ፣ ሶስት አስር ድምሬ
ከቦሌ ሩዋንዳ ፣ እርምጃ ጀምሬ
ታክሲ አስቆማለሁ ፣ መጓዝ ታክቶኝ በግ’ሬ።
:
ብርቱ ሰው አያቴ
ቆሞ ፊት ለፊቴ
ጥቁር ኮፍያ ስር ፣ ሪቫን ለመድገም
ለሶስተኛው ዲግሪ ፣ በሂሳብ ሲጠበብ
እኔ የርሱ ፍሬ
በጓንት እጎርሳለሁ ፣ እጄን ላለማጠብ።
:
አያቴ ያ ብርቱ
ተጨንቆ ለፊቱ
ታሪክ ሲያገላብጥ ፣
መጽሀፍ ሲገልጥ ፣
ኋላውን ሲመዝን ፣ መጪውን ሲለካ
እንቅልፋን ሲገብር ፣ ለዚህ ፖለቲካ
እኔ የርሱ ቅጣይ
የረገፍኩት ዋርካ
የጫቴን ከቻልኩኝ
:
እኔክሽ እኔካ ✌️
(ሚካኤል አ)https://t.me/mk219s
Telegram
እንሳቅ እንወቅ እንዝናና
በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ አስተማሪ፣ አዝናኝና ቁብ ነገር አዘል ጽሑፎች ይቀርባሉ።
Mesi Baheru
መዳን የምትጀምረው "እኔ" ስትል ነው። ካንተ ውጪ ስላለው ሰው ስትል እድሜህን፣ገንዘብህን፣ ልጅነትህንና ንፅህናህን ብትሰዋም ትርፍ የለውም። ሁሉም ነገር ልክ መሆን የሚጀምረው "እኔ" ማለት ስትጀምር ነው።
"እኔ" ላይ ሁን። "እኔ" ስትል ልጅነትህን ታስመልሳለህ። "እኔ" ስትል ለልጆችህ ጊዜ፣ደስታና ሴኩሪቲ ትሰጣለህ፣"እኔ"ስትል በዙሪያህ ያለ ሰው ከደስታህ በረከት ይካፈላል።
"እኔ" ስትል ሰውን እስካልጎዳህ ድረስ በግል ህይወትህ ስለማንም ደንታ አይኖርህም። እኔ ላይ ምርጫህ ሲመሰረት መስመርህ ሌላ ሰውን አለመጉዳት ብቻ ይሆናል። አንተ ስትደሰት የሚከፋው ካለ፣ አንተን የተመቸህ ምርጫ ያልተመቸው ካለ፣ ቆመህ እየሳቅክ መሄድህ የሚያቃጥለው ካለ እመነኝ "እኔ"ን ብቻ አጥብቀህ ይዘህ ተጓዝ።
ከፈጣሪ በታች ከዲፕረሽን፣ ከእብደት፣ ራስን ከመጣል፣ ራስን ከመጥላት የሚታደግህ "እኔ" ማለት ነው። አንተ ከሌለህ ማንም የለም።ለራሱ ያልሆነ ሰው ለማንም አይሆንም።
እኔ ብዘገይም አሁን "እኔ" ላይ ነኝ። እንደመሰለኝ፣ደስታና እረፍትን እፎይታና ፋታን በማገኝበት መንገድ እኖራለሁ።ማንንም አልሰማም። እናንተስ?https://t.me/mk219s

Ephrem Jemal Abdu
አንድ የማስታወቂያ ድርጅት (Agency) በአንድ አረብኛ ቋንቋ በሚናገር ሀገር ውስጥ አዲስ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ማስተዋወቅ ፈለገ። ለዚህም በማስተዋወቂያ ሰሌዳ (Billboard) ላይ የሚለጠፍ፣ ሶስት ክፍል ያለው የታሪክ ስዕል (Comic strip) አዘጋጁ።
በግራ በኩል ያለው ስዕል፦ የቆሸሸ ሸሚዝ የለበሰ እና የተከፋ ሰው ያሳያል።
በመሃል ያለው ስዕል፦ የልብስ ማጠቢያ ሳሙናውን ካርቶን ያሳያል።
በቀኝ በኩል ያለው ስዕል፦ ያው ሰውዬ ንፁህና የሚያብረቀርቅ ሸሚዝ ለብሶ እየፈገገ ያሳያል።
በልብሱ እጥበት እረክቶ እንደማለት ነው።ነገር ግን የማስተዋወቂያ ቡድኑ አንድ በጣም ወሳኝ ነገር ዘነጋ አረብኛ የሚነበበው ከቀኝ ወደ ግራ ነው።
የምባፔ የሰሞኑ ጭቅጭቅ ቢያስታውሰኝ ነው ይህንን የቆየ ታሪክ።ሁሉም ነገር በተለይ በሁለት ወሰኖች (constraints)ይወሰናል ግዜና ቦታ!
የሃገሩን ባሕል እምነት ግንዛቤ ....ባንተ ኖርም ስትመነዝረው ነው ችግሩ የሚመጣው። እግር ከጣለህ የሃገሬውን ዘዬ አክብረህ ቀጥል when in Rome,do as the Romans do.
አንድ ሁለት ቀን ከነከስክም ቤትህ ስትመለስ ጨዋ ጨዋ ትጫወታለህ ምን ችግር!what's done in Vegas,stays in Vegas ይላሉ ነጮቹ!
ደብረብርሃን ቁጭ ብለህ ሱማሌውን ልትመክረው ነው ወይስ እሱ ሊዘክርህ!
አሁን አንዴ ሚላ ወደታች ስትወርድ ምን አለች
"ለእስላሙ ትምባሆውን ተዉለት በኛ እንደ ጠጅ ነው"
ዋኒቷ😏https://t.me/mk219s

ከ20ኛው ክ/ዘ ቁንጮ ደራስያን እና ፍላስፎች አንዱ የሆነው የቦሔምያ(አሁን ቼክ ሪፐብሊክ)ተወላጁ ፍራንዝ ካፍካ አላገባም ልጅም አልወለደም አንድ እለት በስቲግሊትዝ ባቡር ጣብያ በእግሩ እየተዘዋወረ ሳለ አንዲት በለቅሶ ፊቷ ያባበጠ ህፃን አግኝቶ ምን እንዳጋጠማት ጠየቃት አሻንጉሊቴ ጠፍታብኝ ነው ብላው ያለ ውጤት አብረው ሲፈልጉ ዋሉ አሻንጉሊቷ ልትገኝ አልቻለችም።
ፍራንዝ በማግስቱ ተገናኝተው እንደሚፈልጓት ነግሮ ልጅቷን ሸኛት።በማግስቱም ተገናኝተው ብዙ ፈለጉ
አሻንጉሊቷ ጠፋች በቃ! ይህን ግዜ ፍራንዝ ኪሱ ውስጥ
በጥንቃቄ ፅፎ ያስቀመጠውን ደብዳቤ አውጥቶ ልክ በዛ ሰአት ሰው እንደመጣለት አድርጎ ለህፃኗ አነበበላት
ደብዳቤውን ለልጅቱ የፃፈችው አሻንጉሊቷ ነበረች
"አታልቅሽ አለምን ዞሬ ለማየት ወደሩሩሩሩቅ ሃገር ሄጃለሁ ስለምጎበኛቸው ሃገራት እና ስላጋጠሙኝ ሁኔታዎች በዝርዝር እፅፍልሻለሁ"
እንዲህ ባለ ሁኔታ ነበር እስከ ካፍካ የህይወት ፍፃሜ የቆየው ግንኙነታቸው የጀመረው በሚገናኙበት ግዜያት ሁሉ ካፍካ ተጠንተው ተመርጠው ተመጥነው በ"አሻንጉሊቷ"የተፃፉ ደብዳቤዎችን ለልጅቷ ያነብላታል አብረው ይደሰታሉ!በመጨረሻም የአሻንጉሊቷ ወደ በርሊን የመመለስ ብስራት ነጋሪ የነበረው ደብዳቤ ደረሰ!የገዛላትንም አዲስ አሻንጉሊት ለልጅቷ ሰጣት"ግንኮ ምኗም የድሮ አሻንጉሊቴን አትመስልም?"ስትል ልጅቷ ጠየቀች ይሄን ግዜ ካፍካ አዘጋጅቶ ያስቀመጠውን ሌላ ደብዳቤ አውጥቶ ሰጣት "የተጓዝኳቸው መንገዶች እና ያየኋቸው ሃገራት እኔን ቀይረውኛል አድጌያለሁ"ይላል ልጅት ደስ ብሏት አሻንጉሊቷን ይዛ ወደ ቤቷ ሄደች!
ከአንድ አመት በኋላ ካፍካ ሞተ!
ብዙ ዘመናት ቆይቶ ልጅቷ አድጋ አዲስ የነበረችው አሻንጉሊትም አርጅታ ስትቀዳደድ ከሆዷ አንድ ደብዳቤ ወጣ!
"የምትወጂው ነገር ሁሉ መጥፋቱ ባይቀርም ግን በስተመጨረሻ ፍቅር በሌላ መልኩ ተመልሶ ይመጣል"
ፊርማ ፍራንዝ ካፍካ!https://t.me/mk219s

War and Peace ታላቅ የሪያሊዝም ልብወለድ ነው። የቶልስቶይ የአመታት ጥረት ውጤት ነው። የሩስያ ብሎም የአለም ስነፅሁፍ አብይ ስራ ነው።
ልብወለዱ 1500 ገጾች አሉት። ከ200 በላይ ገፀባሕርያት አሉት። ግማሾቹ የእውነት ሰዎች ሲሆኑ የተቀሩት ፈጠራ ናቸው—ታሪካዊ ልብወለድም አይደል።
ታዲያ ለዚህ ልብወለድ መታተም ቶልስቶይ ብቻ አልበቃም—ሚስቱ ሶፊያም ተጨምርበታለች። ቶልስቶይ የድንቅ ደራሲነቱን ያህል እጅ ፅሁፉ ለማንበብ የማይመች አሰቸጋሪ ነበር።
ታዲያ ቶልስቶይ የቸከቸከውን ወደ የሚያምር የእጅ ፅሁፍ የምትቀይረው ሶፊያ ነበረች። ሁሌ ማታ ራት ተበልቶ፣ ሁሉም ወደ እንቅልፍ ከሄደ በኋላ አለም ሁሉ ሲያንቀላፋ ሶፊያ ትነቃለች። በአጉሊመነፅር ጭምር እየታገዘች ዋር ኤንድ ፒስን ትገለብጣለች። ቢያንስ 7 ግዜ ሙሉውን ገልብጣለች። ከ10,000 ገፆች በላይ ነው—ከባድ መስዋእትነት።
በነገራችን ላይ ይሄ ድንቅ ልብወለድ ተፅፎ፣ ታትሞ፣ ተነቦ አለምአቀፍ ተወዳጅነት ከማግኘቱ በፊት 20 ግዜ ያህል አይረባም፣ አንቀበልም፣ አናሳትምም የሚል መልእከት ደርሶታል። ሶፊያም 7 ግዜ ደጋግማ በእጇ ለመገልበጥ የተገደደችው፣ ወደ ተለያዩ አሳታሚዎች ረቂቁን ለመላክ ነው። በነገራችን ላይ ቶልስቶይ እና ሚስቱ ሶፊያ በጣም የሚዋደዱ ነበሩ። ሶፊያ 10000 ገፅ ለመገልበጥ ያልከበዳት፣ ከልቧ ስለገለበጠች ሳይሆን ይቀራል።
https://t.me/mk219s

.ቅቅል ፍልስፍና ነው
.ቅቅል በሽሮና በክትፎ መሃል ያለ
ተማዝኖ(equilibrium)ነው
.ቅቅል የእኛነታችን ብጥቃት የመኖራችን
ሚስጥር ነው
.ቅቅል ከዓለም ጋር ያለንን መስተጋብር
ማስመርያ ሁባሬ ነው
.ቅቅል በእኔ ውስጥ ህያው ነው፤እኔም በቅቅል ውስጥ ህያው ነኝ
.ከቅቅል ጋር ያለኝ ወዳጅነት ከ2.50 ዱቃ
ቤት የጀመረ እስከ 250 ቴራስ ቪው ድረስ
ዘልቋል
.ከአንድ ጠብሰቅ ካለ ወደል መፅሐፍ ይልቅ በአንድ ሳህን የቅቅል መረቅ ውስጥ የሚታይ የሚጠጣ የሚገነጠል
ፍልስፍና አለ
.ቅቅል እውነት ነው
.ቅቅል እምነት ነው
.ቅቅል ታሪክ ነው.....ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል
በጥንታዊት ቻይና የ7ኛው የቂንግ ስርወ መንግስት ንጉሥ የነበረው ፑዪ በግዛቱ ውስጥ አመፅ ተስፋፍቶ ነበር።አመፀኞቹ በጥብቅ ቁጥጥሩ ስር ወዳለችው አንድ የግዛቱ ከተማ በመዝለቅ የንጉሡን አባት አግተውያመልጣሉ።ቆይተው ከበርሃ ለንጉሥ ፑዪ ደብዳቤ ይልካሉ
አባትህ እኛ ጋር ነው መታደግያ (ransom) እንዲሆንእንዲህ እንዲህ ያል ወርቅና ጌጣጌጦች ፈረሶች ..ወዘተ ጨምረህ ላክ አለበለዚያ ግን አባትህን ቀቅለን ሾርባውን ልንጠጣው ነው!!!
ንጉሡም በደብዳቤ ምላሽ ሰጠ
አደራ ከመረቁ ላኩልኝ!
አባቱን ፈተው ሰደዱለታ!
ከዚህ በላይ ታሪክ አለ????https://t.me/mk219s

Nani Adonai
Reposted
ጠላትህን የምትበቀልበት ምርጡ መንገድ፣ እንደ እርሱ ባለመሆን ነው' !
"የሆኑ ሰዎች አሉ፤ አስቀይማችኋቸው፣ በድላችኋቸውና አዋርዳችኋቸው—ለማስቀየም፣ ለመዝለፍና ለማዋረድ ምክንያት እያላቸው፣ ለመጉዳትም አቅም እያላቸው—ብዙ ነገር እያዩና እየሰሙ 'ባልሰማ ባላየ' ችል የሚሏችሁ። ዞር ብለው እንኳ የማያዩዋችሁ።
ለጊዜው ያሸነፋችኋቸው ይመስላችኋል፤ ጭንቅላት ካላችሁ ግን ጊዜ ወስዳችሁ ስታስቡ_ለምን ዝም አሉኝ? ለምን ምላሽ አልሰጡም? ይሄን ያህል ንቀውኝ ነው?' ብላችሁ ትቆጫላችሁ። በራሳችሁ ታፍራላችሁ፤ ትናደዳላችሁ። ከእናንተ ጥፋት በላይ የነሱ ዝምታ ይገዝፋል።
ሰዎች እንደ 'ችል መባል' የሚጠሉት ነገር የለም። ሁሉም ሰው አይደለም በርግጥ፤ ተንቆ እንደተተወ የማይገባው፣ እንደ ውሻ በወጪ በወራጁ የሚጮህ ብዙ ከንቱ አለ። ነገር ግን አንድ ሰው ችል ሲላችሁ፣ ንቋችሁ ለፀብና ለሙግት የማይመርጣችሁ 'ሰው' እንኳ ሆናችሁ ባለመገኘታችሁ የሚሰማችሁ ስሜት ከባድ ነው።
በሌላ መንገድ፤ ይህ ሰው በብዙ ምክንያትና መንገድ ምላሽ መስጠት እየቻለ ዝምታን መርጦ፣ በጊዜ ሂደት በድርጊታችሁ እንድትፀፀቱና በራሳችሁ እንድታፍሩ ሲያደርጋችሁ ያለው ስሜት..."
ስቶይሲዝም Stoicism — "የውስጥ ሉዓላዊነት"
የዚህ ፍልስፍና ቁልፍ መሪ ቃል "ሰዎች የሚጎዱን በድርጊታቸው ሳይሆን፣ እኛ ለድርጊታቸው በምንሰጠው ትርጉም ነው" የሚል ነው።
አንድ ሰው ሲሰድብህ ወይም ሲያዋርድህ ፣ ምላሽ ባለመስጠት ያ ግለሰብ በአንተ ስሜት ላይ ስልጣን እንዳይኖረው ታደርጋለህ።
ማርከስ ኦሬሊየስ የተባለው የሮም ንጉሥና ፈላስፋ እንዲህ ብሏል_"ጠላትህን የምትበቀልበት ምርጡ መንገድ፣ እንደ እርሱ አለመሆን ነው።"
ብዙ ጊዜ ትልቅ "ድል" የሚመስለን ተሳድቦ መርታት፣ አዋርዶ ማሸነፍ ወይም ተበቅሎ እኩል መሆን ነው። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ በላይ "ንቁ ዝምታ" Active Silence ወይም "ችል ማለት" ትልቁ የድል እና የቅጣት መሣሪያ ነው።
"በርግጥ፤ እንዲህ አይነት ሰብዕናን መላበስም ሆነ ድርጊቱን በትክክል ተረድቶ ራስን መታዘብ ከፍተኛ የሆነ "Emotional Intelligence" እና ስማርትነትን ይጠይቃል።
በፖለቲካውም ሆነ በማህበራዊ ህይወት፣ Maturty ያለው ሰው "ስማርትነቱን" የሚያሳየው በሚናገረው ብቻ ሳይሆን በማይናገረውም ጭምር ነው!
"ዛሬ ጊዜ ስለነበረኝ፣ አእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱትን ሁሉ መጻፍ ወደድኩ።"https://t.me/mk219s

"እንግሊዝ ከቀናት በፊት ዜጎቿ ለሦስት ቀናት የሚሆን ምግብ እንዲያከማቹ ጠይቃ ነበር፤ ሆኖም አሁን የተለያዩ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ እና እስያ ሀገራት ለመጪው ወራት ምግብ እና አስፈላጊ ነገሮች ማከማቸት ጀምረዋል። ዓለም ላይ ምን እየተፈጠረ ነው? ሊፈጠርስ ነው?
'አሜሪካ ከምርጫው በኋላ ኢራንን ልታጠቃ ትችላለች' የሚሉ የፖለቲካ ትንተናዎች ቢኖሩም፣ ከፖለቲካ ባለፈ ሌላ ክስተት ይፈጠራል የሚሉ__ኮንስፒራሲ ቲዎሪዎች አሉ።
ከቀናት በፊት በአንድ የፖለቲካ ትንተና ላይ እንደተገለጸው፤ የቻይና የሕዝብ ነፃ አውጪ ሠራዊቷን PLA በነሐሴ 1927 የመሠረተች ሲሆን፣ በፈረንጆቹ 2027 የሠራዊቱ የ100ኛ ዓመት Centenary ይከበራል። ይሄን ምክንያት አድርጋ ታይዋንን ትወራለች ተብሎ ይገመታል። የአሜሪካ ወታደራዊ መሪዎች ጭምር ቻይና ታይዋንን በኃይል ለመቆጣጠር እስከ 2027 ድረስ ዝግጅቷን ታጠናቅቃለች የሚል ግምት አስቀምጠዋል።
አሜሪካ ደግሞ ለታይዋን የምታደርገው ድጋፍ ግጭት ሊያስነሳ ይችላል ተብሎ ይሰጋል።
እንዲሁም ራሽያን ጨምሮ __ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካከተመ ወዲህ ወታደራዊ እንቅስቃሴን ውስጥ ሳትገባ የቆየችው ጀርመን፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ታሪካዊ የሚባል የመከላከያ በጀት ጭማሪ አድርጓል። ፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጅት ላይ ናቸው።
ካታርን ጨምሮ የቀጠናው ሀገራት በኢራን ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፤ የካታር__ መንግስት ዜጎችም ሆኑ ነዋሪዎች ለመጪው ጊዜያት ከካላስፈላጊ ወጪዎች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።
ዓለም ላይ ምን ሊፈጠር ይችላል? አንዳንዶች ጉዳዩን ከኤሊኖች እና ከሃይማኖት ጋርም የሚያገናኙት አሉ።
"እኛም የዚህ ዓለም አንዱ አካል ነን፤ ምን እየተፈጠረ እና ሊፈጠር ይመስላችኋል?https://t.me/mk219s

ዞሮ ዞሮ ተመልሶ ይመጣል“ የሚባል ራስን ማታለያ አለ። ዞረው ዞረው የሚመጡት እናተን መርጠው ሳይሆን—አንድ ሰው ሲመለስ፣ ዘግይቶም ቢሆን—የሚመለሰው እናተን __ መርጦና ፈቅዶ አይደለም፤ ይልቁንም ውጭ ላይ ፈልጎ ያላገኘው ዓለም፣ የገነባው ሕይወት ወይም የሞከረው መንገድ ሲከሽፍበት፣ ወይንም አዲስ ዓለም ለመገንባት ድፍረት፣ ጉልበትና አቅም ሳይኖረው ቀርቶ፣ በየትኛውም ሁኔታ የሚቀበላቸውን፣ የሚጠብቃቸውን ዓለም መርጦ ነው።
ሰዎች የለመዱትን ዓለም ጥላ በቀላሉ ማፍረስ ስለሚቸገሩ፣ ባይመችም እንኳ እዚያ ጥላ ሥር መቆየትን ይመርጣሉ። ያኔ ከእናተ ጋር የሚኖረው—ትክክለኛ መስሎ የተሰማቸው ምርጫ እንጂ—እነሱ አይደሉም።
እንዲሁም ከናተ ጋር ያላቸውን ማህበራዊ__ኃላፊነትና ግዴታ ለመወጣት ብቻ ይሆናል፤ ይህ ማለት ግን እውነተኛ ስሜት አላቸው ማለት አይደለም። ልባቸውና ፍላጎታቸው ሌላ ቦታ ሆኖ ሳለ፣ በድናቸው ከእናተ ጋር ይኖራል! በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ—እነሱ እንደመረጣቹ ይሰማቹዋል፣ ወይም እንዲሰማቹ ያደርጋሉ።https://t.me/mk219s

ሰዎች የተለያየ የፍቅር ግንኙነት አሳልፈው ሊሆን ይችላል፤ አላሳለፉምም ይሆናል። ትክክለኛ ሰው የሚሉትን ሰው ሲመርጡ ቆይተውም ይሆናል፤ ግን የሆነ ጊዜ ላይ ማግባት ቤተሰብ__መመስረት እንዳለባቸው ያምናሉ! በእድሜ ወይም በተለያየ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ያኔ ግን የትዳር መስፈርታቸው ፊት ለፊታቸው ያለ ሰው ሳይሆን፣ ውስጣቸው ያለ ፍላጎታቸው ይሆናል፤ __ሰዎች ዕድሜ ሲገፋ ወይም ሕይወት የተወሰነ አቅጣጫ ሲይዝ፣ ከዚህ ቀደም ይፈልጓቸው የነበሩትን ብዙ መሥፈርቶች Standards በመተው "ለወቅቱ ሁኔታ የሚስማማውን_ሰው በመምረጥ ትዳር ይመሥርታሉ።
ታዲያ በዚህ ጊዜ አንደኛው አካል ከሰው ሁሉ ተመርጦ ይመስለዋል፤ እውነታው ግን __በትክክለኛው ሰዓት ላይ የመገኘት Right timing ውጤትነው!
አንዳንዴ __አግብተህው የምትኖረው ሰው ያላንተ ሕይወቱን ማሰብ የማይችልበት የፍቅር ስሜት ውስጥ ሆኖ ሳይሆን፣ ትክክለኛ ሰው እንኳን ባትሆን በትክክለኛ ሰዓት ተገኝተህ ይሆናል።
የፈለግነውን መኖር ወይም ማግኘት አንችልም። አንዳንዴ ለቤተሰብ፣ ለኅብረተሰብ ወይም ለራሳችን ስንል "ግዴታ" የሆነውን መንገድ እንመርጣለን።
አንዳንዴ የምንፈልገውን ሳይሆን፣ መሆን ያለበትን እናደርጋለን።https://t.me/mk219s

ቢዚ ሆኜ ነው የማላገኝሽ፣ የማልደውለው ሲልሽ ቢዚ መሆኑን እመኚው፤ የማይደውልና የማያገኝሽ ግን ስለማይፈልግ ነው! https://t.me/mk219s

Monster is not born, it is built by society !
"የሰው ልጅ በአንድ ጀምበር አይቀየርም። ውስጡ የሚያዳፍነው፣ የሚገራው፣ ጊዜ ጠብቆ የሚያወጣው አውሬ አለው፤ ይሄን አውሬ የሚያዳፍነውም፣ የሚገራውም፣ የሚያወጣውም አስተዳደጋችን እና ማህበረሰባችን ነው። ማንም መጥፎ ሆኖ አይወለድም!
you don't have to be perfect, you can be good!https://t.me/mk219s

Assaf Hailu
የኤርትራ ህልም!
_____
/ጸሐፊ፦ አፈንዲ ሙተቂ/
የፖለቲካው ታሪክ እና የህልማችን ተስፋ
~~~~
ኤርትራ ዛሬ ራሷን የቻለች ሀገር ናት፡፡ ትናንት ግን የኛው አካል ነበረች፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሤ ብልጥ የሆኑ መስሎአቸው ለሁላችንም አስፈላጊ የነበረውን የፌዴሬሽን ፎርሙላ ሰረዙትና ህዝቡን አስቀየሙት፡፡
ደርግ ደግሞ የራሳችንን ህዝብ እንደ ባዕድ እየቆጠረ በመትረየስ አጨደው፤ በታንክ ደመሰሰው፡፡ በዚህም የተነሳ ወጣቱ “አደይ ኤሪቲሪያ”ን እየዘመረ ወደ ባርካና ሳህል ነጎደ፤ ራሱን አደራጅቶ ጀብሃና ሻዕቢያ ሆኖ መጣ፡፡ ውጤቱም 1983 ላይ ታየ፡፡
የደርግና የኃይለ ሥላሤ መንግሥታት ያደረጓቸው ነገሮች ሲገርሙን በጣም ግራ የሚያጋባው ሶስተኛው መንግሥታችን መጣ፡፡ ይህ የኛ መንግሥት “የተበላሸውን ሁሉ አስተካክለን አብረን መኖር እንችላለን” ብሎ መከራከር ሲገባው ጭራሹኑ “ኤርትራ ካልተገነጠለች ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም” ባይ ሆኖ ተገኘ፡፡
ክፍለ ሀገሩ “ሓርነት ወጣ” ከተባለ በኋላ ደግሞ መንግሥቱ ከሚከተለው ግልጽነት የጎደለው አሰራር የተነሳ በ1990 ሺዎችን ያረገፈ ግዙፍ ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ህዝቦች ተጋደሉ፤ እነሆ ዛሬም ድረስ ነገሩ ሳይለይለት በጨለማ ውስጥ ነው ያለነው፡፡
እኛ ግን ተስፋ አንቆርጥም! በአያያዝ ጉድለት የተለየንን ወገናችንን መመለስ እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ለጊዜው ሪፈረንደም አድርጎ ነጻነቱን ማወጁን እናደግፋለን፡፡ ቢሆንም ህልም አይከለከለምና አንድ ቀን ተቀራርበን በጋራ ስለመስራት እንወያይ ይሆናል ብለን እናልማለን፡፡
የኛ ልጆች ደግሞ በኮንፌዴሬሽን ስለመስራት ያስቡ ይሆናል፤ የልጅ ልጆቻችን በፈቃደኝነት ስለመዋሃድ ያስቡ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜም አሁን የምንመኘው በአንድነት ውብ የመሆን ሚስጢራችን ይመለስልናል ብለን እንመኛለን፡፡ ምን ይታወቃል? ለፈጣሪ የማይሳነው ነገር የለም፡፡
ወገኖቼ ደጉን ነው የተመኘሁት፡፡ በቅን ልቦና በርትተን ከጸለይንና ከኛ የሚጠበቀውን ካደረግን ሁሉንም የሚችለው ፈጣሪ ህልማችንን እውነት ያደርግልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የናፍቆትና የህዝቦች ቁርኝት
~~~~~~
ምን እንደጣለብኝ እንጃ! ያንን ምድር እጅግ ሲበዛ እወደዋለሁ፡፡ እኔ ለተወለድኩበትና አብዛኛውን ዕድሜዬን ለጨረስኩበት የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ጎረቤት ከሆነችው ሶማሊያ ይልቅ በ1600 ኪ.ሜ. የምትርቀው አስመራ ናት የምትናፍቀኝ፡፡ ስለ ሶማሊያ የተጻፈ መጽሐፍ ማንበብ ብዙም አይማርከኝም፤ ስለ ኤርትራ የተጻፈ መጽሐፍ ካጋጠመኝ ግን ሳላየው አላልፍም (ይህ ግን ሶማሊያን ከመጥላት እንደማይቆጠርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ)፡፡
ታዲያ በርካቶቻችሁም እንደኔው ትመስሉኛላችሁ፡፡ ለምሳሌ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ሲታተም የቆየው የቤኒ አምሩን ወጣት የሚያሳየው ፖስተር ዛሬም ድረስ ከኛ ጋር ተሳስሮ ነው ያለው፡፡ አሁንም ድረስ በበርካታ ስፍራዎች ተለጥፎ አይቼዋለሁ፤ በፌስቡክም እርሱን እንደ ፕሮፋይል ፒክቸር የሚጠቀም ኢትዮጵያዊ ሞልቷል፡፡
በሌላ በኩል የኤርትራን ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዎች በሽ ናቸው፡፡ ደራሲ መሐመድ ሳልማን መቐለ ሄዶ ያየው ነገር ቢያስገርመው “በኤርትራ ሙዚቃ የምትጨፍር ከተማ” የሚል አስደናቂ ወግ ጽፎ እውነቱን አስረድቶናል፡፡ መንግሥታት ቢጣሉ እንኳ ህዝቦች ምንጊዜም እንደሚነፋፈቁ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ዋቢ ያለ አይመስለኝም፡፡
የማርታ ሀይሉ ዜማና የጋራ ማንነታችን
~~~~~~~
ማርታ ሀይሉን አስታወሳችኋት? አዎን! ማርታን “ብራ… ነው… ብራ ነው”፤ “አዘዞ”፤ “ሎጋ ..ና እናውጋ” በተሰኙት ዘፈኖቿ እናውቃታለን፡፡ ከማርታ ዘፈኖች ዘወትር ቀልቤን ይገዛ የነበረው ግን የትግርኛ ዜማዋ ነው፡፡ አዝማቹ እንዲህ ይመስለኛል፡፡
ካብ አስመራ ድንገት ርእዮ
ምጽዋ ገባሁ ልበይ ሕብዮ፡፡
እንተርጉመው እንዴ? ግድ የለም ማርታ ራሷ እንዲህ እያለች በአማርኛ ተርጉማዋለች፡፡
“ከአስመራ ድንገት አይቼው
ምጽዋ ገባሁ ልቤን ሰጥቼው”፡፡
አዎን! ትናንት የኛ ናት ስንላት ለነበረችው ኤርትራ ነው እንዲህ የዘመርንላት፡፡ ዛሬም ብንዘምርላት እንከበራለን እንጂ አንወቀስም፡፡ ምክንያቱም በመንግሥት ደረጃ ነው የተለያየነው፤ ሁለት ፓስፖርት እንዲኖረን ነው የተደረግነው፡፡ ሁለታችንም ግን አንድ ህዝቦች ነን፡፡ በደምም ሆነ በባህል በጣም የተዋሃድን የአንድ መሬት ብቃዮች ነን፡፡
ሁለታችንም የተዋብን የሴምና የኩሽ ህዝቦች ውቅር ነን፡፡ እንደኛ የሚያምር ህዝብ በትኛውም ዓለም የለም፡፡ የጀበና ቡና፣ ዶሮ ወጥ፣ ድፎ ዳቦ፣ የስጋ ፍትፍት፣ አምባሻ፣ ወዘተ ሁለታችን ዘንድ ብቻ ነው ያለው፡፡
የኤርትራ ታሪክ፣ ጀግኖችና የጥበብ ከዋክብት
~~~~~~~
በርግጥ እላችኋለሁ፡፡ በምንባብና በወሬ እንጂ በአካል የማላውቃት ኤርትራ ትናፍቀኛለች! ያ በታሪክ ምዕራፎች “ምድሪ ባህረ ነጋሽ” እየተባለ ሲጠራ የኖረው ጀግና መሬትና ህዝብ ይናፍቀኛል፡፡ ያ የሰሜኑ በረኛ እያልን ስንመካበት የነበረው ህዝባችን ይናፍቃል፡፡
እውነትም ኤርትራ ! የዳማት ታሪክ ውቅር! የመጠራ አብያተ መንግሥታት ከርስ! የሀውልቲ ፍርስራሾች ቀብር! የአዱሊስና የዙላ ወደቦች መዘክር! የሱዋኪምና የዳህላክ ሱልጣኖች ደብር!
ኤርትራ የአብረሃ ደቦጭ ሀገር! የሞገሥ አስገዶም ሀገር! የዘርዓይ ደረስ ሀገር! የሎሬንዞ ታዕዛዝ ሀገር! የደጃች ሀረጎት ሀገር! በአይበገሬ ጀግንነታቸው ድፍን አፍሪቃን ያኮሩ አርበኞች የበቀሉበት ምድር!
ኤርትራ የበረከት መንግሥተ አብ ሀገር! የፀሐይቱ ባራኪ ሀገር! የአብረሃም አፈወርቂ ሀገር! የአሕመድ ሼኽ ሀገር! የሄለን መለስ ሀገር! የየማነ ባሪያው ሀገር! የሄለን ጳውሎስ ሀገር! በስርቅርቅ ድምጻቸው የሰውን ልብ እየሰረሰሩ የመግባት ሀይል ያላቸው የጥበብ ከዋክብት የወጡበት መንደር!
ኤርትራ የፊያሜታ ጊላይ ሀገር! የስዕላይ በራኺ ሀገር! የኦቦይ ተኽሌ ሀገር! የተክላይ ዘድንግል ሀገር! የሆቴል ፓራዲዞ ሀገር! የዕቁባይ ሲላ ሀገር! የምንወደው ደራሲያችን በዓሉ ግርማ በ“ኦሮማይ” መጽሐፉ እንደ ፊልም ግልጥልጥ አድርጎ እየተረከልን ዝንተ-ዓለም እንድንወዳት ያደረገን የቀይ ኮከብ ትዝታ ወመዘክር!
ኤርትራ የፊዮሪ ሀገር! የሳባ ሀገር! የማርቲና ሀገር! የብርኽቲ ሀገር! ፊያሜታ ጊላይን የመሳሰሉ “ሽኮሪናዎች”ን ያበቀለች ውብ የውቦች እመቤት!
አስመራ እና የህጻናት ትዝታ
~~~~~~
ኤርትራን ስንጠራ በቅድሚያ ወደ አዕምሮአችን የምትመጣው አስመራ ናት፡፡ የአስመራ ናፍቆት ይገድላል፡፡ አስመሪና፣ አስመሪቲ፣ አቲ ጽብቕቲ!...
ውይ ስታምር! “ቀሽቲ እኮ ናት፡፡ ያኔ በልጅ አዕምሮአችን በዘምባባ ጥላዋ ተሸክፋ በፖስትካርድ ስትቀርብልን “የኛ ውቢት” እያልን እንመጻደቅባት ነበር፡፡ እንቆቅልሽ ስንጫወትና መልሱ ጠፍቶን “ሀገር ስጠኝ” ስንባል እርሷን ለመስጠት እንሰስት ነበር፡፡ ጠያቂውም የዋዛ ስላልሆነ “አስመራ” ካላልነው ለጠየቀን ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ አይነግረንም ነበር፡፡
ከማናውቃቸው “ዋሽንግተን እና ሮማ” ይልቅ አስመራ ነበር የምትበልጥብን፡፡ በትምህርት ቤት መዝሙራችንም እንዲህ እንል ነበር፡፡
ኦኬ ኦኬ ኦኬ ስራ
ሰላም ሰላም ወደ አስመራ
አዲስ አስተማሪ ከጃፓን የመጣ
ማስተማሩን ትቶ በቦክስ የሚማታ
አናግረኝና አናግርሃለሁ
በአሜሪካ ሽጉጥ አዳፍንሃለሁ፡፡
አማርኛም አልችል ትግርኛም አልሰማ
ሰተት ብዬ ልግባ አስመራ ከተማ፡፡

ግጥሙ “አንታራም” የሚሉት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን አስመራ ከልባችን እንዳትጠፋ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ዛሬም በልባችን ነግሳለች አስመሪና!
አስመሪና! እቲ ሽኮሪና! ሰሜናይት ጽብቕቲ! በዓሉ ግርማ ላንቺ ክብር የጻፈው ትዝ ይልሻል? እስቲ እናስታውሰው!
አስመሪና አስመራዬ
ካብ ሐንቲ ንግሥቲ ይበልፅ መልክእኪ
አማአድዬ ክርእየኪ ከሎኹ ኽአ
አብ ኢደይ ዘሎ ነገር ይወድቕ፡፡
(አስመራ አስመራዬ)
(ከአንድ ንግሥት ይበልጣል መልክሽ)
(በሩቅ ሲያይሽ በውበቷ ስለተማረሽ)
(በእጄ ያለ ነገር ሳይታወቀኝ ይወድቃል)
የአስመራ ሰፈሮች እና የእግር ኳስ አስማተኛ (አማኑኤል እያሱ)
~~~~~~~~~
ጸጸራት፤ ፎርቶ፣ ሐዝሐዝ፣ አርበእተ አስመራ፣ እምባጋሊያኖ፣ ኮምቢሽታቶ፣ አዲ ጓእዳድ፣ ቃኘው፣ ማይተመናይ፣ ሰምበላይ፣ ጎዳይፍ፣ ገጀረት፣ ወዘተ… በጽሑፍ የማውቃቸው የአስመራ ሰፈሮች ናቸው፡፡ አንድ ቀን በሆነልኝና ባየኋቸው እያልኩ አልማሁ፡፡
እነዚህ አስገራሚ የአስመሪና ሰፈሮች ብዙ ባለታሪኮችን አብቅለዋል፡፡ ብዙዎች ገድላቸው እየተደጋገመ ሲነገርላቸው እሰማለሁ፤ አነባለሁ፡፡ ለኛ ቅርብ የነበረ አንድ ውድ ልጅ እየተረሳ በመሆኑ ግን አዝኛለሁ፡፡
አማኑኤል እያሱ ይባላል! አስታወሳችሁት አይደል? አዎን! አማኑኤል በኛ ዕድሜ ዘመን ኢትዮጵያ ዋንጫ መብላት እንደምትችል ያስመሰከረው የታላቁ የ1980 የእግር ኳስ ቡድናችን ቋሚ ተሰላፊ ነበረ፡፡ የማሊያ ቁጥሩ 2 ይመስለኛል፡፡
አማኑኤል የያኔው ቡድናችን ባደረጋቸው ሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፏል፡፡ ቡድኑ ዋንጫውን ሲበላም ከጓደኞቹ ጋር ቤተመንግሥት ድረስ ተጋብዞ ተሸልሟል፡፡ አማኑኤልን ያስገኘው ከዚያ ዘመን ዝነኛ ቡድኖቻችን መካከል አንዱ የነበረው የኤርትራ ጫማ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የኤርትራ አንደኛ ዲቪዚዮን ዋንጫን በተደጋጋሚ ያሸነፈ ነው፡፡
አማኑኤል እያሱ በኢትዮጵያ ትቅደም አንደኛ ደረጃ ዋንጫም ለኤርትራ ክፍለ ሀገር ምርጥ ቡድንም ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ባልሳሳት የ1981 የኢትዮጵያ ዋንጫን ያሸነፈው እነ አማኑኤል የነበሩበት የኤርትራ ክፍለ ሀገር ቡድን ነው፡፡
የአማኑኤል እያሱን ወሬ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበብኩት በ1988 ለወዳጅነት ጨዋታ አዲስ አበባ መምጣቱን በማስመልከት በርካታ የግል ጋዜጦች ቃለ-መጠይቅ ባደረጉለት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም፡፡ እስቲ የአስመራ ልጆች ወሬው ካላችሁ ስለአማኑኤል እያሱ አንድ ነገር በሉን፡፡
የምዕራብ ኤርትራ ህዝቦች እና የትግረ ቋንቋ
~~~~~~
አሁን ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት ቆላማ አውራጃዎች እዚህ ነው ያሉት፡፡ አቆርዳት፣ ተሰነይ፣ አሊጊደር፣ ኡምሐጀር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞች በቆላው ምድር ውስጥ ተዘርግተዋል፡፡
ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ የሚባሉት ብሄረሰቦች እዚህ ነው የሚኖሩት፡፡ የአካባቢው ዋነኛው ህዝብ ግን ለኛ በጣም ቅርብ የሆነውን ሳቂታውን የቤኒ አምር ወጣት ያስገኘው የትግረ ህዝብ ነው፡፡
የትግረ ህዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች አሉት፡፡ ከሁሉም የሚበረክተው ግን የቤኒ አምር ጎሳ ነው፡፡ ህዝቡ የሚነጋገርበት የትግረ ቋንቋ ከሴማዊ ቤተሰብ ነው የሚመደበው፡፡ ለዚህ ቋንቋ በጣም የሚቀርበው በደጋው ኤርትራና በኛዋ የትግራይ ክልል የሚነገረው ትግርኛ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ከጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ ነው የተወለዱት፡፡ የትግረ ቋንቋን ከ35 በመቶ የማያንሰው የኤርትራ ህዝብ ይናገረዋል፡፡ “ትግረ” ከኤርትራ ሌላ በሱዳንም (ከሰላ አካባቢ) በስፋት ይነገራል፡፡
ትግረና ትግርኛ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንግዳ ለሆነ ሰው አንድ ዓይነት ቋንቋዎች ሊመስሉት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለትግርኛ ተናጋሪዎች የትግረ ቋንቋን መልመድ በጣም ቀላል ነው ይባላል፤ የትግረ ተናጋሪም ትግርኛን በቶሎ መልመድ ይቀለዋል፡፡
በመሆኑም ከጠቅላላው የኤርትራ ህዝብ 50% የሚሆነው ሁለቱንም ቋንቋዎች መናገር ይችላል (ይህ ቁጥር ትግርኛ ብቻ የሚናገሩትን፣ ወይንም “ትግረ” ብቻ የሚናገሩትን አይጨምርም)፡፡
ምዕራባዊው ቆላ ኤርትራዊያን በጣም የሚያደንቋቸውን እንደ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ፣ ሙሐመድ ኢድሪስ እና ኢድሪስ ገላውዴዎስን ያፈራ መሬት ነው፡፡ በዚህ ሰሞን ልቤን ያሸፈተው የትግረ ልጅ ግን “አሕመድ ሼክ” ነው፡፡ አሕመድ ሼክን አወቃችሁት አይደል?
አዎን! “ባቡሬይ”፣ “ኢላ ሰርጎ” ወዘተ.. እያለ በማይጠገበው የትግረ ምት የሚያዜመው ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡ አንድ ኤርትራዊ ወዳጃችን “ኤላ ሰርጎ”ን ሲፈታልን “ከጀርባው ፌሎሶፊ አለው” ነው ያለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
የትግረ ሴት ለምትወደው አንድ ሰው (ለባሏ) እንጂ ለማንም ጸጉሯን አትገልጠውም፡፡ ስለዚህ ጉብሊቷን ልጅ የወደደው አሕመድ ሼክ በተዋቡ ግጥሞች እያወደሳት ዘፈነላትና ፍቅሩ ልቧ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ለማረጋገጥ ጸጉሯን ማየት ጀመረ፡፡
እርሷም ግጥሞቹን ከሰማችለት በኋላ ጸጉሯን ገልጣ አሳየችው፡፡ ድል አድራጊው ወዲ ሼክም ይዟት በረረ፡፡ “ኤላ ሰርጎ! ኤላ ሰርጎ” እያለ ነጎደ!
ሰሜን ኤርትራ፡ የከረን ውበት እና የቢለን ታሪክ
~~~~~~~
ሰሜን ኤርትራ! ተወዳጇ የከረን ከተማ እዚህ ነው ያለችው! የሀረርጌዋ የድሬ ዳዋ ከተማ መንትያ እህት የምትመስለው ውቢቷ የሰሜን ፈርጥ! በቪዲዮ አይቻት ውበቷን አደነቅኩላት! አበቦቹ! ቤቶቹ! መንገዶቹ ሁሉም ውብ ናቸው፡፡
ከትግራይ የተገኘው ዝነኛው ብርሃነ ሃይለ አንድ ላይ በነበርነበት ዘመን ለከረኗ ጉብል እንዲህ ብሎላታል፡፡
ሸው በሊ ብለነይ ብለነይ
ዝለሊ ብለነይ ብለነይ
አሊሊ ብለነይ ብለነይ
አቲ ጓል ከረነይ ብለነይ
አዎን! ቢለን ከከረን ከተማ ጋር ስሙ የሚጠቀስ ብሄረሰብ ነው፡፡ ቋንቋው ከኛው የአገው ቋንቋ ጋር አንድ ዐይነት ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው አንባቢ ሊመራመር የሚገባው፡፡ በወሎና በጎጃም የሚኖረው አገው ምን ሊያደርግ እዚያ ሄደ?... መቼ ነው እዚያ የሄደው?..…
መላምት ከመዘብዘብ በስተቀር ማንም ሰው ይህንን እንቆቅልሽ በሚያመረቃ ሁኔታ ሊፈታው አልቻለም፡፡ ኤርትራና እኛ አንድ ነን የሚያሰኘኝ እንዲህ ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ስላለን ነው፡፡
ቢለን ውብ ባህል ያለው ህዝብ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ ባህል መሰረት ሴቶቹ ካገቡ በኋላ ጸጉራቸውን መሰተር ግድ ነው፡፡ ህዝቡ የቢለን ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም የትግረ ቋንቋንም ይጠቀማል፤ ትግርኛም በስፋት ይነገራል፡፡ በጣም ታዋቂ የሆነው የቢለን ተወላጅ “ዑመር እዛዝ” ነው፡፡ የጀብሃ ጦር ከመፍረክረኩ በፊት የሁለተኛው ዞን አዛዥ እንደነበረ ከዚህ በፊት ጽፌ ነበር፡፡
አፋቤት፣ ሳህል እና የረሺዳ ህዝቦች ታሪክ
~~~~~
ከከረን ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናመራ ታሪካዊቷ አፋቤት አለች፡፡ ጄኔራል ታሪኩ አይኔ የሚመራው ናደው እዝ እዚህ ነበር የሰፈረው፤ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዋና አምባም ይህ ነበር፡፡ ከአፋቤት ወደ ሰሜን ስንበር ንዳዳማውና አስቸጋሪው የሳህል መሬት አለ፡፡
በሳህል እምብርት ላይ የኤርትራ ገንዘብ መጠሪያ ለመሆን የበቃችው “ናቅፋ” አለች፡፡ በዓሉ ግርማ እንደተረከልን ከሆነ ሳህል ማለት እሳት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይኖሩበታል፤ ከብቶች ይሰማሩበታል፤ ተከልም ይበቅልበታል፡፡
እዚህ አካባቢ በብዛት የሚኖረው ህዝብ “ረሺዳ” ይባላል (አንዳንዶች “ራሻይዳ” ይሉታል፤ ስህተት ነው፤ ትክክለኛው አጠራር “ረሺዳ” ነው)፡፡

የ“ረሺዳ” ህዝብ ከሌላው የኤርትራ ህዝብ የሚለይበት በርካታ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ይህ ህዝብ ከሳዑዲ ዐረቢያ ተነስቶ ወደ ኤርትራ የገባው በቅርብ ዘመን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ) ነው፡፡
በዚያ ወቅት የአሁኗ ሳዑዲ ዐረቢያ አልነበረችም፤ ሀገሩ ሁሉ በጎሳዎች የተከፋፈለ በረሃማ ምድር ነበር፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ አል-ረሺድ ይባላል፡፡ ይህ የአል-ረሺድ ህዝብ የአካባቢው የበላይ እንዲሆን በኦቶማን ቱርክ ተወሰነ፡፡ አብዛኛው ህዝብም ለነርሱ አደረ፡፡
“አል-ሱዑድ” የሚባለው ቤተሰብ ግን “አሻፈረኝ” አለ፡፡ “ራሴ በረሃውን ጠቅልዬ መግዛት ስችል ለምን በአል-ረሺድ ጎሳ የበላይነት አድራለሁ” በማለት አንገራገረ፡፡ በሁለቱ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ በመጀመሪያው ላይ የአል-ረሺድ ጎሳ አሸነፈ፤ አል-ሱዑዲዎች ወደ ኢራቅ ሸሹ፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የአል-ሱዑድ ቤተሰብ በእንግሊዞች ደጋፊነት ራሱን አጠናክሮ መጣ፤ በአል-ረሺድ ጎሳ ላይም ድልን ተቀዳጀ፡፡ በዚህም የተነሳ የዐረቢያ በረሃ ለአል-ረሺድ ጎሳ አባላት ሲኦል ሆነ፡፡ ረሺዳዎች እየተያዙ በጅምላ ታረዱ፤ ንብረታቸው ተዘረፈ፡፡
በፊት ይረዳቸው የነበረው የቱርኮች መንግሥት በራሱ ችግር በመወጠሩ ምንም ሊያደርግላቸው አልቻለም፡፡ በመሆኑም ከእልቂቱ ለመዳን ሲሉ ባህር እያቋረጡ ወደ አፍሪቃ ምድር ተሰደዱ፤ በሱዳንና በኤርትራ መኖሪያቸውን ቀለሱ፡፡
እንግዲህ ረሺዳዎች ከዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸሽ ወደ ኤርትራ የመጡ ተፈናቃዮች ናቸው ማለት ነው፡፡ በኤርትራ ውስጥ ንጹህ የዐረብ ዝሪያ የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውም ዐረብኛ ነው፡፡
በዚህ ህዝብ ባህል መሰረት ለአካለ መጠን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ፊቷንም ሆነ ጸጉሯን መሸፈን ግዴታዋ ነው፡፡ በዓሉ ግርማ በኦሮማይ ውስጥ ሲተርክልን “ማንኛውም የረሺዳ ባል የሚስቱን ፊት ገልጦ የሚያይበትን ሰው አይፈልግም” በማለት የተናገረውም የባህላቸው አንድ አካል ነው፡፡
ምስራቅ ኤርትራ እና የታሪካዊቷ ምጽዋ ትዝታ
~~~~~~
አሁን ወደ ምስራቅ ኤርትራ ተሻግረናል፡፡ ብርኽቲ የሆነችው ምጽዋ እዚህ ነው ያለችው፡፡ ብርሃነ ሃይለ “ሸው በሊ ብለነይ” የተሰኘውን ዘፈን ሲቀጥል ምጽዋን እንዲህ ይላታል፡፡
“አብ ዋሊድ ማሳዋ
ኩለ ሊየን ሒልዋ”
ትርጉሙን በትክክል ባላውቀውም “የምጽዋ ልጆች ሁሉም ጣፋጭ ናቸው” የሚል መልዕክት እንዳዘለ ይገባኛል፡፡ የምጽዋ ልጆች ቆንጆ ናቸው ተብሎ እየተደጋገመ ተነግሮላቸዋል፡፡ ከወደብ ከተማ የተገኙ በመሆናቸው ዓለም አቀፍ ስልጣኔና ልዩ ልዩ ባህሎች በነርሱ ላይ ሲነፍስ ይታያል፡፡
ምጽዋ በጣም ውብ ናት፡፡ በተለይም ኪነ-ህንጻዋ ብዙ ተብሎለታል፡፡ ከዑስማናዊያን ቱርኮች ዘመን ጀምሮ ብዙ ገዥዎች ሲፈራረቁባት የነበረች መሆኗ በከተማዋ የሚታየውን ኪነ-ህንጻ እንዳሳመረው ምሁራን ያስረዳሉ፡፡
ኤርትራዊያን ምጽዋን ይወዷታል፤ እኛም እንወዳታለን፡፡ ነገር ግን ወደዚያ ለመድረስ የሚሻ ሰው እንደ እሳት የሚፋጀውን ሙቀቷን መቻል አለበት-ከተማዋ በዓለም ላይ ከፍተኛ ሙቀት ካላቸው ስፍራቸው አንዷ ናትና፡፡
የዚህች ከተማ ህዝብ ኑሮውን ከአየር ጸባዩ ጋር እንዲጣጣም አድርጎ ቀይሶታል፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወነው ከምሽት እስከ እኩለ ሌሊት ባለው ጊዜ ነው፡፡
ታዲያ ከተማዋ ለዘወትር እንደጋለች አትቀርም፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ ሙቀቱ ጋብ ይልና ጤናማው አየር ይነፍስባታል፡፡ ይህም ከጥር-የካቲት ባለው ጊዜ እና በሀምሌ ወር ነው፡፡ በነዚህ ወራት ከተማዋን የሚጎበኘው ቱሪስት በጣም ይጨምራል፡፡
በቀድሞው ዘመን ቀዳማዊ ኃይለሥላሤም ከተማዋን ለመጎብኘት የሚመጡት በነዚህ ወራት ነው (እርሳቸው ያሰሩት ቤተ-መንግሥት እስከ አሁን ድረስ አለ)፡፡
የምጽዋ የወደብ ታሪክ እና የጦርነት ውድመቶች
~~~~~~~~
ምጽዋ በወደብነት አገልግሎት መስጠት የጀመረችበት ዘመን በትክክል አይታወቅም፡፡ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከተማ ቀመስ ሰፈራ ነበር፡፡ ይሁንና እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ወደብ ሲያገለግሉ የነበሩት ከምጽዋ አጠገብ የነበሩት ጥንታዊያኑ “ዙላ” እና “አዱሊስ” ነበሩ፡፡
የምጽዋ ተፈላጊነት ጉልህ ሆኖ የተከሰተው የባህር መደቡ በ1508 በዑሥማናዊያን ቱርኮች (Ottoman Turks) በተያዘበት ወቅት ነው፡፡ ከቱርኮቹ በማስከተልም ግብጾችና የኢጣሊያ ወራሪዎች ተፈራርቀውባታል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌዴሬሽን ከተዋሃዱ በኋላ ምጽዋ ከፍተኛ እመርታ ማሳየት ጀምራ ነበር፡፡ ከ1970ዎቹ መግቢያ ጀምሮ ግን የጦርነት ቀጣና ሆነች፡፡ የሻዕቢያ ሀይሎችና የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ እልቂት የተፈጸመባቸውን ጦርነቶች አካሂደውባታል፡፡
በተለይም በ1982 (እ.ኤ.አ. 1990) በተካሄደው ጦርነት ከሁለቱም ወገን በአስር ሺህ የሚቆጠር ሰራዊት መርገፉን ሁኔታውን በቅርበት የተከታተሉ ወገኖችና የዐይን ምስክሮች ገልጸዋል (የሀምሳ አለቃ ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖን “አይ ምጽዋ” አስታውሱት)፡፡
የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምም “ለከፍተኛ ሽንፈትና ኪሳራ የዳረገን ውድቀት ያጋጠመን በምጽዋ ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡
የድሮው ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) የአሁኑ “ህዝባዊ ግንባር ንዴሞክራሲን ንፍትሒን” (ህግዴፍ) ምጽዋን የተቆጣጠረበትን ዘመቻ “ኦፕሬሽን ፈንቅል” በማለት ይጠራዋል፡፡ ምጽዋ የተያዘችበት ዕለትም (የካቲት 20) በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በርካታ ህዝብ ወደ ምጽዋ ከሚጎርፉባቸው ዕለታት መካከልም አንዱ ይህ “የኦፕሬሽን ፈንቅል” መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን ነው፡፡
ምጽዋ የብዙ ህዝቦች መኖሪያ ናት፡፡ ዋነኞቹ ነዋሪዎች ግን የአሳውርታ፣ ሳሆ፤ እና አፋር ብሄረሰቦች ተወላጆች ናቸው፡፡ በከተማዋ በዋናነት የሚነገረው ቋንቋ ዐረብኛ ነው፡፡
የሻዕቢያ መስራች ተብሎ የሚታወቀው ዑሥማን ሳልህ ሳቤ የተወለደው በምጽዋ አጠገብ ካለችው ሂርጊጎ የተባለች አነስተኛ መንደር ነው፡፡ ኢብራሂም አፋ፣ ረመዳን መሐመድ ኑር እና ዓሊ ሰዒድ አብደላን የመሳሰሉት የህግሓኤ (ሻዕቢያ) እውቅ ኮማንደሮችም የምጽዋ ልጆች ናቸው፡፡
አዱሊስ፣ የሳሆ ህዝብ እና የማዕከላዊ ደጋው ክፍሎች
~~~~~~
ከምጽዋ ወደብ ዝቅ ብሎ ጥንታዊቷ የአዱሊስ ወደብ ትገኛለች፡፡ ይህች የወደብ ከተማ ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የተጓዦች መግቢያና መውጪያ ነበረች፡፡ የጥንቱ ሮማዊያንና ግሪኮችም በደንብ ያውቋታል፡፡
አጼ ካሌብ ወደ ደቡብ ዐረቢያ ሲዘምት ወታደሮቹን በመርከብ ያስጫነው ከዚህች የወደብ ከተማ ነው፡፡ በሀገራቸው ከፍተኛ በደል ያጋጠማቸው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች ከጥቃቱ ለመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በአዱሊስ በኩል ነበር ያለፉት፡፡ ሌላም ብዙ ታሪክ ተስተናግዶአል-በአዱሊስ፡፡
ከምጽዋ ወደ መሀል ኤርትራ ለመጓዝ መንገዱን ስንጀምር በቅድሚያ የምናገኘው የሳሆ ህዝብን ነው፡፡ ይህ ህዝብ በስተደቡብ በኩል ከሚጎራበተው የአፋር ህዝብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ መሰረት አለው፡፡ ሁለቱም በከብት እርባታ ነው የሚተዳደሩት፤ ሁለቱም ኩሻዊ ቋንቋ ነው የሚናገሩት፡፡
በአለባበስ ግን ሳሆን ከአፋር በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የሳሆ ተወላጅ የሆነ ሰው አፋሮች የሚታጠቁትን “ጊሌ” የሚባለውን ረጅም ቢላዋ አይታጠቅም፡፡ የሳሆ ሰው የሚያሸርጠው ሽርጥም ከአፋር ሽርጥ ረዘም ይላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሳሆ ብዙ ጊዜ ከእጁ ጦር አያጣም፡፡

ታዲያ የሳሆ ቋንቋ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚኖረው የኢሮብ ህዝብ ከሚናገረው ቋንቋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢሮብና ሳሆ የሚለያዩት በሚከተሉት እምነትና በኢኮኖሚ መሰረታቸው ነው፡፡
ሳሆ ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው፤ ኢሮብ ግን በአብዛኛው ክርስቲያን ነው (ከዚህ ውስጥ የሚበዙትም ካቶሊኮች ናቸው)፡፡ በሌላም በኩል የኢሮብ ህዝብ አራሽ ገበሬ ይበዛዋል፤ ከላይ እንደተገለጸው የሳሆ ህዝብ በከብት እርባታ ነው የሚተዳደረው፡፡
ሳሆን ስናልፍ ደግሞ ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ በስፋት የሚኖርባቸውን የአከለ ጉዛይ፣ ሰራዬ እና ሐማሴን አውራጃዎችን እናገኛቸዋለን፡፡ በኤርትራ ውስጥ ካሉት ብሄረሰቦች መካከል ብዙ ቁጥር ያለው (50 % የሚሆነው) ይህ ትግርኛ ተናጋሪ ህዝብ ነው፡፡
ይህ ህዝብ በባህሉም ሆነ በቋንቋው ከኛው የትግራይ ህዝብ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ህዝቡ በአብዛኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ መሆኑም ከትግራይ ህዝብ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይሁንና ቋንቋው ባለፉት በርካታ ዘመናት ከጣሊያንኛ፣ ከዐረብኛ እና ከትግረ ቋንቋዎች ጋር በመወራረሱ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚነገረው ትግርኛ የተለየ ዘዬ ሊሆን በቅቷል፡፡
እጅግ በርካታ የሆኑ የኤርትራ ከተሞች ያሉት በዚህ ክልል ነው፡፡ ጊንዳዕ፣ ሐሙሲት፣ ሰገነይቲ፣ ደቀምሐረ፣ መንደፈራ (አዲ ዑግሪ)፣ አዲኳላ፣ ሰንዓፈ፣ ደባሩዋ ወዘተ.. እዚህ ነው የሚገኙት፡፡ በመሀከላቸው ደግሞ አስመራ ጉብ ብላ ትታያለች፡፡ ከከተሞቹ መካከል የሚበዙት በጣሊያን ዘመን የተቆረቆሩ ናቸው፡፡
በሰራዬና በአከለ ጉዛይ አውራጃ ውስጥ ግን የጥንቱ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ታዋቂ ከተሞች የነበሩትን እንደ “ሀውልቲ” እና “መጠራ” የመሳሰሉ መንደሮችን ማግኘት ይቻላል፡፡
በነዚህ ከተሞች ፍርስራሾች ስር ገና ያልተነካ ድልብ የአርኪዮሎጂ ሀብት አለ፡፡ ወደፊት ቆፈረን የምናወጣቸውን ማቴሪያሎች የህዝቦቻችንን አንድነት የሚመሰክሩ ቋሚ ቅርሶች አድርገን ልጆቻችንን እናስተምራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ኤርትራን በኢትኖግራፊ ጉዞ እንዲህ ቃኝተናታል፡፡ ነገር ግን በዚሁ አናበቃም፤ ወደፊትም በተሻለ ዝግጅት ተመልሰን እንዘይራታለን፡፡ ለአሁኑ በዚሁ ይብቃን!!
ሰላም!!
አፈንዲ ሙተቂ
ነሐሴ 30/2006 ዓ/ም °
________
° ለፌስቡክ ንባብ እንዲመች ለማድረግ ከከፋፈልኳቸው አንቀፆችና በየመሐሉ ከጨመርኩበት ገላጭ ንዑስ-ርዕሶች በቀር፣ ጽሑፉ ሙሉ በሙሉ የአፈንዲ ሙተቂ ነው። ለጸሐፊውም ይህን ረዥም ጽሑፍ በትዕግሥት ለዘለቃችሁ የፌስቡክ አንባብያንም ከልብ አመሠገንኩ። መልካም ትዝታ። ሰናይ ጊዜ!🙏🏿https://t.me/mk219s

ህልማችሁን ነው እየኖራችሁ ያላችሁት ከህይወት ምን እንደምትፈልጉ ታውቃላቹ
በምትወዱት ስራ ላይ ነው የተሰማራችሁት የምትወዱትን ስራ ነው እየሰራቹ ያላችሁት ወይስ የገቢ ምንጫቹ ብቻ ነው
ከምትወዷቸው ሰዎች ጋር ነው ማህበራዊ ህይወታቹ ነው እንደነገሩ ነው ማህበራዊ ህይወት ግዴታችሁን እየተወጣቹ ነው በጥርስ የምትሸኟቸው ናቸው
የምትፈልጉትን ትዳር ነው እየመራቹ ያላችሁት ደስተኞች ናቹ ህልማቹ ከሆነ ሰው ጋር ነው እየኖራቹ ያላችሁት ምርጫቹ ልክ ነበር ወይስ በግዜ ሂደት ልክ እንዳልሆናቹ የተሳሳተ ምርጫ እንደነበር ተረድታቹ አንዴ ገብቼበታለሁ ብላቹ ሃላፊነታችሁን እየተወጣቹ ነው
ጓደኞቻቹ የናተ ወዳጅነት የሚገባቸው ናቸው እንደሚወዷቹ እርግጠኞች ናቹ እናተስ ትወዷቸው ይሆን ወይስ
ፍቅረኞቻቹ ውድ ግዜያችሁን ስሜታችሁን የምታባክኑባቸው ሰዎች ይገባቸዋል የደስታቹ ምክንያት ናቸው ያለነሱ ህይወታችሁን የማታስቡት ሰዎች ይሆኑ እውነት ትወዷቸዋላቹ ወይስ መላመድ ነው በፍቅርና በመላመድ ውስጥ ትልቅ ልዩነት አለ
ለምን እንደምትኖሩ በህይወት ድርሻቹ ምን እንደሆነ ታውቃላቹ የምትኖሩለት አላማ አላቹ ለነሱ ነው የምኖረው የምትሏቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን በህይወታቹ
ብታጧቸው ቢያጧቹ የሚጎልባቹ የሚጎልባቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን
ለመኖር የሚያጓጓቹ በቂ ምክንያት አላቹ
ህይወታችሁን ባግባቡ እየመራቹ ይሆን
ህይወታችሁን መስመር ማስያዝ ችላቹ ይሆን
እንዲ ብላቹ እራሳችሁን ጠይቃቹ ታውቁ ይሆን
ለዚ ሁሉ መልስ አግኝታቹ ይሆን ኧhttps://t.me/mk219s

ሱፊዎች ሰይጣንን አልጠላውም ምክንያቱም ከፈጣሪ ፍቅር ላይ የምቀንሰው ጊዜ ስለሌለኝ ይላሉ
ሱፊዝም መሰረቱ የእስልምና ሃይማኖት ይሁን እንጂ ለማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ የሚጠቅም የህይወት ፍልስፍና አስተምሮ አላቸው በነሱ ዘንድ ትልቁ ነገር ፍቅር ነው ፍቅር sexual ብቻ አደለም
ጥላቻ ከፍቅር በላይ ኢነርጂ ይጠይቃል ከምትወዳቸው ሰዎች በላይ የምትጠላቸው ሰዎች ልብህን አቅልህን ይቆጣጠራሉ ስለዚ ከፍቅር ላይ ቀንሰህ ነው የምትጠላው ስለዚ በምትወዷቸው ሰዎች በፍቅር ላይ ግዜ ኢነርጂያችሁን አጥፉ በመጥላት ለፍቅር ግዜ አትጡ አታባክኑ
I wish ሁልግዜ ልደቴ ቢሆን እና በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች ምን ያህል እንደሚወዱኝ ለኔ ያላቸውን ፍቅር ሲገልፁልኝ ስሰማ ብኖር
በርግጥ አልዋሽም ከዚ በፊትም እንደቀልድ ፖስቼ አስተውላቹ ይሆናል ፎቶ እየፖሰታቹ እከልዬ እከልዬ ሳክስ ነው የሚመስለኝ ለምን ደውላቹ ወይም በመልክት አትነግሯቸውም ለነዛ ሰዎች ያላችሁን ስሜት እላለሁ
እኔ በተፈጥሮዬ ተንከባካቢ ትኩረት ሰጪ ነኝ በተቃራኒው ችልተኛ ሰው እጠላለሁ ሆኖም በማወቅም ባለማወቅም ብዙ ችላ ብዬ የማልፋቸው ነገሮች አሉ ከነሱ አንዱ ለምወዳቸው ሰዎች እንደምወዳቸው መንገር ይሄ ልማድ አልነበረኝም ፍቅር በድርጊት ብቻ እንደሚገለፅ ከሚያምኑ አንዷ ነበርኩ ሆኖም በግዜ ሂደት ስህተት እንደሆነ ተገንዝቢያለሁ
ፍቅር ድርጊት ብቻ አደለም አንዳንዴ ወይም ብዙ ግዜ የምንወዳቸው ሰዎች ምን ያህል እንደምንወዳቸው በህይወታችን ያላቸውንም ቦታ ስንነግራቸው መስማት ይፈልጋሉ አንዳንዴ ከሰዎች መስማት የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉ ፍቅራቸውን ለኛ ያላቸውን ቦታ አክብሮት ውደሳ
ይሄን ያስተዋልኩት ዘግይቼ ነው አንድ በጣም የምወደው ጓደኛ ነበረኝ በህይወቴ ትልቅ ቦታ አስተዋፆ ያለው እንደማንኛውም ጓደኛሞች እንጣላለን ወይኔ ወይሱ ይቅርታ ጠይቀን ካቆምንበት ምንም እንዳልተፈጠረ እንቀጥላለን አንድ ቀን ተኮራርፈን ሲደውል ስልኩን ሳላነሳ በስንተኛው ቀን አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል እንደሆነ ነግረውኝ ልጠይቀው ሄድኩ oxygen ተደርጎለት እራሱን ስቶ አየሁት
የዛኔ ነው አንዲትም ቀን ምን ያህል እንደምወደው በህይወቴ ያለውን ቦታ ነግሬው እንደማላውቅ ያስተዋልኩት I can’t say I love you it’s too late to tell you but I really need you to know that I’ll never forget you I’ll never let you out of my heart አልኩት ሰምቶኝ ቢሆን ደስ ባለኝ ግን ዘግይቻለሁ
ብዙ ሰዎች በህይወቴ አሉ ግን ብቸኝነት ይሰማኛል የሱን ቦታ ማንም አይተካም
እኔ ሁሌም ከስህተቴ ነው የምማረው ዛሬ በህይወቴ ላሉ ሰዎች ባገኘሁት አጋጣሚ እንደምወዳቸው በህይወቴ ያላቸውን ቦታ በነፃነት መንገርን ልምድ አድርጌያለሁ tomorrow isn’t promise ነገ ዋስትና የለውም ዛሬን በህይወታቹ ላሉ ሰዎች ምን ያህል እንደምትወዷቸው በህይወታቹ ያላቸውን ቦታ ንገሯቸው
ሳጠቃልል እግዚአብሔር ያክብርልኝ ለመልካም ምኞታቹ ለምታሳዩኝ ፍቅር ክብር ስለማይገባኝ ብዬ ወሬ አላጣፍጥም ይገባኛል ፍቅር ክብር የማይገባው የለም በምትሰጡት ልክ በምላሹ ስለምታገኙት ብዙ የሃሳብ ልዩነት ኖሮን የምንናቆር የማንመቻች እንኖራለን ያ እንድንጠላላ ግን ምክንያት አይሆንም ሁላችሁንም እወዳችኋለው በመጥላት ኢነርጂዬን የማጠፋበት አንድም ሰው እንዳይኖር ነው ጥረት የማደርገው
አንዳንዴም እየተናቆርን እንጂ ወገን ኧhttps://t.me/mk219s

Nani Adonai.
Letting go of someone you truly love is one of the most difficult things in the world. Unfortunately, sometimes it’s necessary
አንዳንዴ ስለምንጠላቸው፣ ስለማንፈልጋቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከምንም ነገር በላይ ስለምንፈልጋቸው፣ ስለምንወዳቸው ከህይወታቸው ልንወጣ፣ ልናስወጣቸው የሚገባን ሰዎች አሉ።
አንዳንድ ጊዜ ለእኛም፣ ለነዛ ሰዎችም ደህንነት ከልብ ስለምንጨነቅ፤ ከባድ ውሳኔዎችን መወሰን ይጠበቅብናል። አንድን ሰው ለራሱ፣ ለራስም ጥቅም መተው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የፍቅር ተግባር ሊሆን ይችላል!
where staying together might be harmful or unhealthy በተለይም አብሮ መኖር ጎጂ ወይም ጤናማ ያልሆነ ሁኔታን የሚያካትት ሲሆን፤ አንድን ሰው እየወደዱት መተው፣ ለአንድ ሰው ደስታ ቅድሚያ ለመስጠት ብዙ ድፍረት እና ርህራሄ ይጠይቃል። በተለይ እነዚ ሰዎች ደስተኛ የሚሆኑት ከእናንተ እርቀው ከሌላ ሰው ጋር ቢሆንም እንኳን፤ ለምርጫቸው መተው፣ ፍቅር ሁል ጊዜ አብሮ የመቆየት ሳይሆን ለእያንዳንዳችን መልካምን መፈለግ ነው።
ፍቅር የራስ ንብረት ማድረግ ብቻ አይደለም!https://t.me/mk219s

አላህ ይባእድ አኒክ አውላደል ሃራም_አላህ ከመጥፎ ነገር ወይም ከክፉ ሰው ያርቅሽ ማለት ነው፤አላህ ከፍ ያድርግሽ፤ ብድርሽን ይከፍልሽ!ዛሬ የተመረቅኩት ምርቃት ነው፤ አሜን ብዬ ሄድኩ።
“ጠራችኝና እኔም አንድ ቀን ኢንሻ አላህ ብድርሽን እከፍላለሁ አለችኝ።
አረ ምን ሆነሽ ነው? ትልቅ ነገር አይደለም፤ አንቺም ማንም ሰው ቢሆን በኔ ቦታ የሚያደርገው ነገር ነው! ከዛ በኋላ ሁለቴ ተገናኝተን እንዴት ሆንሽ? ብዬ ያልጠየቅኩሽ ማስታወስ ይሆናል፣ ሊደብርሽ ይችላል ብዬ ነው አልኳት።
በፍፁም! አንቺ ስለሆንሽ እንጂ ማንም ሰው ቢሆን የሚያደርገው ነገር አይደለም አለች።
"እኔ የሆነ ሰው ድንገት የሚያስጨንቀውን፣ ያስከፋውን፣ ያለበትን ችግር፣ ሚስጥሩን ካጋራኝ፣ ደካማ ጨለማ ፓርቱን ካሳየኝ—ያንን ነገር ድጋሚ ራሱ ግለሰቡ ካላነሳልኝ—"እንዴት ሆንክ? ተሳካልህ? ተስተካከለልህ? ተረጋጋህ? ችግርህን ፈታህ? ብሎ መጠየቅ ጤናማ ቢሆንም፣ እኔ ግን ያንን ሰው ማስታወስ፣ "ለኛ ማጋራቱን እንዲቆጭ ማድረግ፣ ሚስጥርህን፣ ደካማ ጎንህን አውቃለሁ ማለት ነው__መስሎ የሚሰማኝ፤ እና ከራሳቸው መጥቶ ድጋሚ ሊያወሩልኝ ካልፈለጉ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ነው የምለው።
"አንዳንዴ ሰዎች ካቅማቸው በላይ የሆነ ስሜት ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ ለሌሎች ማጋራት የማይፈልጉትን ነገር ያጋራሉ፤ ሲያልፍ ይቆጩበታል! አንተ ደግሞ መጥተህ በቅንነትም ቢሆን "እንዴት ሆናችሁ? ስትላቸው ይበልጥ ሊቆጩ፣ ስጋት ሊገባቸው ይችላል። እንደዛ ነው የምረዳው። ስለዚህ ከራሳቸው ካልመጣ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምሆነው—ኮምፎርት እንዲሰማቸው።
ሆኖም በተቃራኒው—የነሱን ኮምፎርት እና privacy__ለመጠበቅ ያደረኩት የጨዋነት ምግባር ሳይሆን—ለነሱም ሆነ ላጋሩኝ ጉዳያቸው ግድ የሌለኝ፣ ትኩረት ያልሰጠሁት ሆኖ ይተረጎምብኝና ሲቀየሙኝ ራሴን አገኘዋለሁ!
ላወራላችሁ የፈለኩት ግን ስለኔ የህይወት ፍልስፍናም አልነበር።
"አንቺ ስለሆንሽ ነው__አዎ፣ እኔ ስለሆንኩ የማደርጋቸው ነገሮች አሉ። መጥፎም ጥሩም ነገር ይሆናል፤ ምንም ሊሆን ቢችል "እይ! እሱ ስለሆነ ነው እንጂ ሌላ ሰው ይሄን እንዲህ አያደርግም መባል—የራሳችሁ ቀለም አላችሁ፣ የራሳችሁ ሐሳብ ምክንያት አላችሁ ማለት ነው።
መጥፎ ነገር እንኳን ቢሆን እናንተ ስለሆናችሁ የምታደርጉት ይሁን፤ የራሳችሁ ፍርጃ፣ ጥላቻ፣ አድናቆት፣ ትችት፣ ጥሩ መጥፎ ድርጊት ይኑራችሁ፤ የማንንም አትጋሩ! ብትሳሳቱ እንኳን የራሳችሁን ስህተት ተሳሳቱ።
እኔ ፍጹም አይደለሁም፤ ጥሩ ሰውም መጥፎም አይደለሁም! የተሳሳቱ ውሳኔዎችንና ምርጫዎችን አድርጌያለሁ፣ አደርጋለሁም።
የተሳሳቱ ነገሮችን ተናግሬአለሁ፤ ትክክለኛ ነገሮችንም ተናግሬአለሁ—የተሳሳቱ ሰዎችን ወድጃለሁ፤ የተሳሳቱ ሰዎችንም አምኛለሁ፤ ጥሩ መልካም ነገሮችን፣ ከኔ ሊመጡ የማይገባቸውን፣ ከኔ የማይጠበቁ መጥፎ ነገሮችንም አድርጌያለሁ።
ያደረግኳቸውን ነገሮች በሙሉ አልወዳቸውም፤ አልኮራባቸውም፤ ነገር ግን ያደረግኳቸው እኔው ስለሆንኩ ነው።
እንደገና ለመጀመር፣ እራሴን ለመቀየር እድል ባገኝ እንኳን፣ ምንም ነገር አልቀይርም ነበር!
I am the best version of myself that I can be. I am simply myself!https://t.me/mk219s